Kedija Ahmed Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Kedija Ahmed shared a
Translation is not possible.

በጋዛ እና ፍልስጤም እየሆነ ባለው ነገር አትደነቁ❗️

ሰርቢያዎች በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ ያደረጉትን የዘር ማጥፋት  ጦርነት አስታውሱ በጦርነቱም  300 ሺህ ሙስሊሞች ሰማዕት መሆናቸው ተጠቅሷል።

  60,000 ሴቶች እና ህጻናት ተደፍረዋል.

አንድ ሚሊዮን ተኩል ተፈናቅለዋል።

  እናስታውሰዋለን?

ወይስ ረሳነው??

የሲ ኤን ኤን መልህቅ ስለ ቦስኒያ ጭፍጨፋ ትዝታ ተናግሮ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፡- (ክሪስቲና አማንፑርን ) ታዋቂዋ ጋዜጠኛ ነች፡-

ታሪክ ራሱን ይደግማል?

- ክሪስቲና ስለ ቦስኒያ ሲ ኤን ኤን ላይ ይህን አስፍራ ነበር።

- የመካከለኛው ዘመን ጦርነት፣ የሙስሊሞች ግድያ፣ ከበባ እና ረሃብ ነበር። አውሮፓም ጣልቃ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም እንዲህ አለች፡-

ይህ የእርስ በርስ ጦርነት ነው። ነገር ግን ይህ ተረት ነበር..!

እልቂቱ ለ 4 ዓመታት ያህል የዘለቀ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሰርቦች ከ 800 በላይ መስጊዶችን አወደሙ ።

የሳራዬቮ ታሪካዊ ቤተ መጻሕፍትንም አቃጠሉ።

የተባበሩት መንግስታት ጣልቃ በመግባት ወደ እስላማዊ ከተማዎቹ መግቢያ በሮች ላይ ጠባቂዎችን አስቀምጧል።

እንደ ጎራጋ፣ ስሬብሬኒካ እና ዚፓ ያሉ ማለት ነው።

ነገር ግን ዙሪያዋ ተከቦ እና በእሳት ታጥሮ ነበር የነሱ ጥበቃ ምንም ጥቅም አልነበረውም።

ሰርቦች በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን በማጎሪያ ካምፖች አስገብተው በረሃብ አፅም እስኪሆኑ ደረስ  አሰቃዩአቸው።

አንድ የሰርቢያ አዛዥ፡ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ ሲባል?

እርሱም፡- አሳማ አይበሉማ አለ።

  ዘ ጋርዲያን የቦስኒያን የጅምላ ጭፍጨፋን ቀናቶች አሳትሟል፣ በገጹ ላይ ያለው ካርታ ሙሉ በሙሉ፣ ሙስሊም ሴቶች የሚደፈሩበትን ካምፖች ያሳያል።

17 ግዙፍ ካምፖች ነበሩ አንዳንዶቹ ሰርቢያ ውስጥም  ይገኛሉ።

- ሰርቦች ህፃናት ልጆቹን ደፈሩ ... የ 4 አመት ሴት ልጅ ከእግሮቿ መሀል ደም ይፈስ ነበር ።

ዘ ጋርዲያን “በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ አሳትሟል።

ሙስሊም ስለሆነች የተበደለችው ህፃን  ልጅ በሚል ..

ጨፍጫፊው ምላዲች የዚፓን የሙስሊሞች መሪን ለስብሰባ ጠርቶ. ሲጋራ አቀረበለትና አጠገቡ አድርጎ ትንሽ ሳቀበት፣ ከዚያም ወረወረው እና አረደው።

በሲባና በቤተሰቧም ላይ የተለያዩ ክፉ ነገራቶችን  አደረጉ።

ነገር ግን በጣም ታዋቂው ወንጀል የስሬብሬኒካ ከበባ ነበር።

(ከሸይኽ አብድል ገንይ) ገፅ ተወስዶ የተተረጎመ

   ይቀጥላል…

https://t.me/AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪና አነቃቂ የሆኑ ትምህሮችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Kedija Ahmed shared a
Translation is not possible.

ጠላትህን እወቅ

ጀርመን

ሰላም የሚገኘው በጦርነት ብቻ ነው። በጋዛ የተኩስ አቁሙን አንቀበልም።

አሜሪካ

በጋዛ ያለው ውጊያ ቆሞ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግ የፍልስጤም አንጃዎችን ይጠቅማልና ጦርነቱ መቆም የለበትም።

ካናዳ

በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንቃወማለን። ለዓለም አስጊ ናቸውና ሐማሶች መወገድ አለባቸው

ብሪታኒያ

እስራኤል ህግን ጥሳለች ብለን አናምንም። የተኩስ አቁም ስምምነትም መደረግ የለበትም።

ጃፓን

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በወራሪዋ እስራኤልና በፍልስጤም መካከል ያለውን ግጭት ስለማያስቆም አንቀበልም።

ከዚህ በፊትም የሆነው ይህ ነው። ሁሉም መስቀላዊያን ሙስሊሙን ለማጥፋት ያለምንም ልዩነት በሶሪያ በኢራቅና በአፍጋኒስታን በአንድነት ተነስተው ሞክረውት ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል። ከተማውን ወደ ፍርስራሽነት ለውጠዋል። ግና ተዋርደውና ተስፋ ቆርጠው ተመልሰዋል። አሁንም ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Kedija Ahmed shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_____

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_____

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_____

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_____

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_____

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_____

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Kedija Ahmed shared a
Translation is not possible.

" ሀማስ የማይችለውን ጦርነት ከፍቶ ፍልስጤሞችን አስጨረሳቸው "

ይህ የፈሪዎቹ ወቀሳ ነው ! ይህ የደንታቢሶቹ ክስ ነው ! ይህ የኢስላም ልቅናም የሙስሊሞች ክብርና ህልውናም የማያሳስባቸው የግደለሾች ክስ ነው !!

ሀማስ የተመሰረተው በ 1987 ነው ከዛሬ 36 አመት በፊት ። እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ካለአንዳች መከላከል እንደፈለገች ስትጨፈጭፍ ህይወታቸውን ሰውተው ህዝባቸውን ለማዳን የኢስላም ሸአኢሮችን ለመጠበቅ ሞትን ላይፈሩ ተማምለው የመሰረቱት የሙጃሂዶች ስብስብ ነው ። ይህ የነ ሸይኽ አህመድ ያሲን የነ አብዱአዚዝ አልረንቲሲ የህይወት መስዋእትነት ውጤት ነው ።

ሀማስ ባይኖር በአሁኑ ሰአት አንድም ፍልስጤማዊ በፍልስጤም ምድር አይገኝም ነበር ። ጋዛ ዌስት ባንክ የሚባሉ የፍልስጤም መኖሪያዎችንም አናይም ነበር ። የእስራኤልን እጅግ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የሚታገል ብቸኛው የሙጃሂድ ቡድን ሀማስ ብቻ እንጅ ሌላ አይደሉም ።

ሀማሶች ከላይ ሚሳኤሉ ቢዘንብባቸው ከታች ታንክና መድፉ ቢያጓራባቸው እንኳን የሚፈራ የሚደነግጥ ልብ የሌላቸው ተዋርዶ ከመኖር በክብር ሸሂድ መሆንን የሚናፍቁ ሙጃሂዶች ፤ መላው አረብ ተንቦቅቡቆ ከእስራኤልና ምእራባውያን ጋር ሲሽለጠለጥ እነርሱ ግን ከተራራ በገዘፈ ኢማናቸው ተመክተው እነዚህን የገጠሙ የሶሀቦች ትውስታ ትክክለኛ ኸሊፋዎቻቼው ናቸው ። ሀማሶች አንድም ቀን ተመችቷቸው ኖረው አያውቁም ። ሁሌም ከምድር በታች እየቆፈሩ ከምድር በታች እየኖሩ አፈር ለብሰው ድንጋይ ተንተርሰው ይሄንን የሞተ ኡማ ሩህ አለው የሚያስብሉ የኡማውን ቀንደኛ ጠላት እስራኤልን እያቃዡ የሚያስጨንቁ እነርሱ የሙሀጅርና አንሷሮች ኩትኩት የውዱ ነብያቸውም ፈለግ እውነተኛ ተከታይ ፤ ኢስላምን በቃል ሸንገላ ሳይሆን በተግባር የሚኖሩት ፤ ጅሀድን በቂርአት ሳይሆን በህይወትና ንብረታቸው የሚማሩት የወቃሽን ወቀሳ ሳይሰሙ ስለኢስላማቸው ስለህዝባቸው ፍግም የሚሉ እነርሱ ህያዋን ናቸው ።

የፈሪ ፈሪዎቹ ግን አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ እስራኤልን ሲፈሩ ሀማስን ይወቅሳሉ ! ሀማስን ያወግዛሉ !  ይህ ንፍቅና ነው ! ይሄን በቃል መግለፅ አልችልም !!

እነዚህ ደንታቢሶች ሀማስን " ካለአቅሙ እስራኤልን እየተዋጋ " ብለው ጀግኖቹን ለማውገዝ ሲሞክሩ አይሰቀጥጣቸውምን ? በአቅምማ ቢሆን የሳኡዳ አረቢያ የኢኮኖሚ አቅም የእስራኤልን ሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የግብፅ ወታደር ብዛት የእስራኤልን ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የቱርክና የፓኪስታን ወታደራዊ አቅም ከእስራኤል ይልቅ ነበረ !

ግና ከነርሱ ጋር የኢኮኖሚና ወታደራዊ አቅም እንጅ የሀማሶች ሪጃልነት የለም !! ሪጃልነትን አላህ መርጦ የሰጠው ለሀማሶች ናቸውና ! የእርሱን ጅሀድ ይዋደቁ ዘንዳ የተመረጡት ሀማሶች ናቸውና !!

ሌላውማ መይት ነው ! ኢራንና ሂዝቦላህ ለሙስሊሞች ክብር ያላቸውን መቆጨት ለምእራባዊያን ያላቸውን ትግል 1% እንኳ የላቸውም !!

አህሉል ሩዞችና አህላል ፊራሾች አህለል ጅሀዶችን ሲያንጓጥጡ እንደማየት የሚያሳፍር የለም !

ሀማስ ይህንን ጦርነት የጀመረው እስራኤል መስጅደል አቅሷን ጨርሳ ጠቅልላ ለመውሰድ እየተዘጋጀች ባለችበት ነበር ። እናም የአይሁድ አማኞች መስጅዱን ሊረከቡ ዝግጅታቸውን እየጨረሱ ሳሉ ነበር ሀማስ እኛ በህይወት እያለን ይህንን አንፈቅድም በማለት ጦርነት ያወጀው ።

ሀማስ ጦርነቱን ሲከፍት እስራኤል በወረራ በያዘቻቼው የጋዛ ድንበሮች ላይ ምእራባውያን ሙጅሪሞችን ጨምሮ የእስራኤል ሰፋሪዎች በጋዛ ድንበር ተሰባስበው እየጠጡ እየጨፈሩ ነበር ። ሀማስ እንደ መብረቅ ወረደባቸው ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮችንም ወደ ጀሀነም ላካቸው ። ከዚያ በሗላ ይሄው ጦርነቱ ተፋፍሞ ቀጥሏል ።

እስራኤል አቅሟ ንፁሀን ላይ ነውና ንፁሀንን በአየር እየጨረሰች ነው ። ይህንን ከምስረታዋ ጀምሮ የምታደርገው ነው ። ሀማስ ስለመጣ እስራኤል ጦርነት የከፈተች የሚመስላቸውን ገልቱዎች ማስረዳት ከባድ ነው ።

አላህ ድልን ለሙጃሂዶቹ ያጎናፅፋል !

ቃሉንም ይሞላል !

ያኔ መናፍቃንም አዱወሎሆችም ያፍራሉ ይሸማቀቃሉ ኢንሻአላህ !!!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group