Translation is not possible.

አህባሾች ከተሳሳቱባቸው ነጥቦች መካከል ሌላኛው በአሏህ ስምና ባህሪያት በተመለከተ በግልፅ የመጡ የቁራዓንና የሀዲስ ማስረጃዎች በማዞር መተርጎሙና አዞሮ መረዳቱ ግዴታና አስፈላጊ ነው ብለው ማመናቸው ሲሆን ይህ ከቁርዓን ከሱና የወጣና ከሰሀቦችና ከታቢዕዮች እንደዚሁም ከእነርሱ በዃላ የመጡና እነርሱን የተከተሉ ሙስሊሞች መንገዳቸውን መቃወምና መንገዳቸውን ስምምነታቸው ሲሆን ሙስሊሞች ደግሞ የአሏህ ስምና ባህሪያት በቁራዓንና በሀዲስ በመጣው መልኩ ያለማንሻፈፍ፣ ያለማራቆት፣ ያለማመሳሰልና ትርጉም አልባ ሳያደርጉ ይቀበላሉ ማመኑን ግዴታ ነው ብለው ያምናሉ።

አሏህ ከማንም ይበልጥ ስለራሱ አዋቂ በመሆኑና ከፍጡራኖቹ ውስጥ ኑብዩ ከሁሉም በላይ አዋቂ በመሆናቸው ሙዕሚኖች ነብዩ ስለአሏህ የገለፁበትና ያፀደቁትለት እንደዚሁም አሏህ ስለራሱ የገለፀበትና ያፀደቀውን ነገር አያጣጥሉም ውድቅ አያደርጉም አያርቁም፣ ሌላ ትርጉም አይሰጡም፣ ትርጉም አልባ አያደርጉም፣ አይክዱም ለአሏህ ብጤን አያደርጉም።

በሁሉም ሙስሊም ላይ ማመኑ ግድ ሆኖ በቁራዓንና በሀዲስ ከመጡ ለጌታችን አሏህ ፊት እንዳለው ማመን ነው።

(በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡(26)

የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡(27)አረረህማን)

(ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከእርሱ ፊቱ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡አልቀሰስ 88)

በሶሂህ ሙስሊም እንደመጣው ነብዩ ( "የአሏህ ሂጃቡ ኑር ነው ቢገልጠው የፊቱ ጨረር ከፍጥረቶቹ አይኑ የደረሰበት ቦታ ደረስ ያቃጥላቸው ነበር።") ።

ነቢዩ በሌላ ሀዲሳቸው (ጀነቶች አሉ ከብር የተሰሩ መጠቃቀሚያቸውም ከብር የሆኑ፤ ከወርቅም የተሰሩ መጠቃቀሚያቸው ከወርቅ የሆነ በሰዎችና በጌታቸው ፊት መካከል መመልከታቸው የክብር ጋቢ ቢጨምርላቸው እንጂ።)

አህባሾች ስህተት ውስጥ እንዲወድቁ ከአደረጋቸው አንዱና ዋነኛው ነገር ለአሏህ ፊት እንዳለው ካረጋገጥን ለፍጡራኖችም ፊት ስላላቸው አሏህ ደግሞ ከማንም ጋር ስለማይመሳሰል ከፍጡራኖቹ ጋር ይመሳሰልብናል ብለው ማሰባቸው ሲሆን በስም መመሳሰል ብቻ አንድ ነው ማለት የማያስችል ጉዳይ ሲሆን ለምሳሌ ያክል ለሰው ልጅ ፊት እንደለው ሁሉ ለበሬም ፊት አለውና ለሰው ፊት አለው ካልን የሰው ልጅ ከበሬ ጋር ማመሳሰል ስለሆነ ለሰው ልጅ ፊት የለውም ብለን እንደማይባል ሁሉ ይህን እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ምክንያት ተደርጎ አሏህ ለራሱ አለኝ ያለውና ነብዩ ለአሏህ ያረጋገጡለትን ነገር ማስተባበል ትልቅ ስህተት ሲሆን ሙስሊም ነኝ ከሚል አካል የማይጠበቅም ተግባር ነው።

ሙስሊሞች በቁራዓንና በሀዲስ እንደመጣው ለአሏህ ከማንም ጋር የማይመሳሰል እራሱ ብቻ የሚያውቀው ፊት እንዳለው ያምናሉ ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group