Translation is not possible.

የአህባሾች እምነትና ስህተቶቻ

ክፍል ሁለት

ሽርክ

አህባሾች በመግቢያችን ላይ እንዳየነው እስልምና ውስጥ ከተፈጠሩ ቡድኖች ሲሆኑ ራሳቸውን አንዳንዴ ኧኽለሱና በማለት የሚሰይሙ አንዳንዴ አሻዕሪያና ማቱሪዲያ መንገድ ነው የምንከተለው የሚሉ አንዳንዴ የጥንት የመሰረቱ እስልምና የኛ ነው የሚሉ ንግግር ከንግግራቸው፣ ተግባር ከተግባራቸው እንዲሁም ንግግርና ተግባራቸው እርስ በእራሱ የሚጋጭ ቁራዓን በማንበብና በመሀፈዝ፣ የአረብኛ ቋንቋን፣ ሰዋሰውንና የተወሰኑ አመክንዮችን በመማር ሰዎች የሚያታልሉ ነገር ግን በሀቂቃ ስለቁራዓንና ሀዲስ በጥቅሉ ደግሞ የዲን ግንዛቤ የሌላቸው ቡዱኖች ሲሆን ከስህተቶቻቸው መካከል ደግሞ ሽርክ በዋነኝነት ይጠቀሳል ።

አህባሾች በኪታቦቻቸው፣ በአስተምህሮታቸውና ብዙ ጊዜ እንደሚሰማው ከአላህ ውጭ በሞተም ይሁን እሩቅ በሆነ አካል እርዳታን መጠየቅ ድረስልኝ ማለት ጠብቀኝ ማለት ነብዩን እጄን ያዙኝ ማለት ወንጀልን ይምራሉ ብሎ ማመንና እሳቸውን መለመን እና ሌሎች የሽርክ ተግባራትን ሲፈቅዱና እነርሱም ሲሰሩት ይስተዋላል።

ሽርክ ማለት አሏህ ብቻ የተነጠለበትና ለአሏህ ብቻ የሚገቡ ነገሮችን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ሲሆን ከተግባር ከንግግር እንደዚሁ በልብ በሚቋጥረር ነገር ይገኛል የፈፀመው ግለሰብ አሏህ የሰማይና የምድር ፈጣሪ መሆኑ፣የሚፈጥርና የሚገድል፣ የሚያበላና የሚያጠጣና ምድር የሚቆጣጣረ መሆኑን ቢያውቅም-(ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ ) አንከቡት፡61 አሏህ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እኔ መሆኔን ካውቁ የማይጎዳቸውና የማይጠቅማቸውን መጠየቅና መለመን ተትተው የምጠቅማቸውና የምጎዳቸውን በሁሉም ነገር ቻይ ወደሆንኩት ወደ እኔ ለምን አይመለሱም? ይጠይቃልደ

የመካ ሙሽሪኮች የአለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ መሆኑን እያወቁ በመካ ዙሪያ በቀደምት ደጋግ ናቸው ብለው በሚያስቧቸው ሰዎች ስም 360 ጣዎታትን ሰይመው ቀን ከፋፍለው ከአሏህ ጋር ያቃርቡናል ብለው ለአሏህ ብቻ የሚገባውን የአምልኮ ዘርፍ አንስተው በመስጠታቸው አልጠቀማቸውም አሏህ ተግባራቸው ሽርክ ብሎ ነው ብሎ መልሶባቸዋል፦(ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡)ዩኑስ፡18

ከአሏህ ውጭ ይጠቅመኛል ይጎዳኛል ብሎ መጥራትም ሆነ ወደ እነርሱ በተለያዩ ተግባራት መቃርብ መገዛት ወይም ማምለክ ነው።

ይህን አስመልክቶ ደግሞ አሏህ እንደዚህ ይላል፦

(ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡) ዩኑስ፡ 18

እዚህ ቦታ ላይ ይገዛሉ ነው ያለው።ሰዎች የአሏህ ሀቅ ብቻ በሆነው ነገር ከእሱ ውጭ ያሉ አካለትን ይጠራሉ ወደ እርሱም እንዲያቃርቡን በሚል ምክንያት ድረስልን፣ ጠብቀን፣ እርዳን ጉዳያችንፈፅምልን፣ ሀጃችን ሙላልን በማለት ይለምነታል፣ይዋደቃሉለታል፣ ስለት ይሳሉለታል ስለታቸው ያቀርቡለታል፣ በስሙም ሶደቃን ይሰጡለታል፣ ይወዱታል፣ ስለሚወዱትም በስሙ እንጂ አይምሉም፣ ከተማለላቸው አምነምነው ይቀበላሉ የእርሱን ቀን ብለው ቆርጠው ያከብራሉ።

የተሰጠው አካል መላይካም ቢሆን ነብይም፣ ወልይም ቢሆን ተራ ግለሰብም፣ ጠንቋይም ቢሆን ጅን፣ እንጨትም ቢሆን ድንጋይ፣ ጀበናም ቢሆን ሲኒ፣ቄጤማም ቢሆን ጉዝጋዝ ሌላም ሌላም ቢሆን ከ ቀልቡ ካንጠለጠሉበት ተግባራቸው ውድቅ እንደሆነና ይህን ተግባራቸውን አሏህ አምልኮ ብሎ ጠርቶታል ።አምልኮ ወይም ኢባዳዕ ደግሞ ከአሏህ ውጭ አሳልፎ መስጠት ሽርክ እንደሆነ ጥርጥር የለውም ይህን የፈፀመ ሰው ደግሞ ጠማማ ነው ይላል፦(እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡)አህቃፍ፡5

ይህ ደግሞ በድሮ ህዝቦችና በነብዩ ዘመን የነበሩ ሙሽሪኮች እምነት ሲሆን ነብዩምና ቀደምት ነቢያቶች የተላኩበት አላማ ነው።፦( በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡.......) አነህል፡36 አሏህን በብቸኝነት ለማምለክ ነው የሰውልጅና ጅን የተፈጠረው የጂሀድ ሜዳ የተቋቋመው ልዩነቶች የተስፋፉት ደሞች የፈሰሱት ስደት የተከሰተው ይህን ከአሏህ ውጪ የሚደረጉ ተግባራትን ለማስቀረት ነው።

በዚህ ርዕስ ይቀጥላል.......

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group