UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Documentary Expert, Working on Promotional Videos

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

የሚዲያን ነገር ወደ ሃገራችን ስናመጣው በርካታ ሙስሊሞች በሪፖርተርነት፣ በፕሮግራም እና ዘጋቢ ፊልም በማዘጋጀት፣ በመፅሄት አምደኝነት፣ ዋና አዘጋጅነት በሌሎች የቲቪ ሆስት አይነቶች ያገለግላሉ። ሴኩላር በሆነም ባልሆነም መንገድ።

ብዙዎቻችን እንተዋወቃለን። በአንድም በሌላ መንገድ ስራው ያገናኘናል። ፌስ የምናደርገውን ነገር እንነጋገራለን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻል ቢኖረውም በተለያየ ጉዳይ ለማነጋገር የምንደውልላቸው ሙስሊም ዶክተሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን፣ መምህራንና ሌሎቹም ስንደውልላቸው ፍቃደኛ የሚሆኑት ካሉን ምሁራን አንፃር ጥቂቶች ናቸው።

በተለይም ሴኩላር በሆነው ሚዲያ ለመቅረብ ዝግጁ አይደሉም። ምሁራን እንደሌሉን፣ በርካታ ባለሃብቶች እንደሌሉን ሁሉ ሚዲያው ጥቂት ሙስሊም ምሁራንን ነው የሚያውቀው። በሃይማኖታዊ ሚዲያዎቻችንም ተመሳሳይ ችግር ይከሰታል። እርስ በርስ ያለን መተሳሰር የላላ በመሆኑ ተፈራርጀን ተራርቀናል።

የዓለምም ሆነ የሃገር ፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያው ሜዳ ሚዲያ ነው። ውሃ ዋና የሚለመደው ውሃ ውስጥ በመግባት ብቻ ነው። ስላየኸው እና ስለሰማኸው አትለምድም።

ምሁራኖቻችን፣ ሃኪሞቻችን፣ መምህራን፣ ባለሃብቶቻችን፣ የየትኛውም የሙያ ባለቤቶች እባካችሁ ገፅታችን እንዲቃና፣ "አሉ" እንድንባል ደፍረን እንውጣ። እንተጋገዝ!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከሶስት ሳምንታት ወዲህ የቶክ ቲቪው ፒርስ ሞርጋን በፍልስጤም እና እስራኤል ጉዳይ የተለያዩ ሰዎችን ላይቭ ያቀርባል። በጦርነቱ ላይ ያላቸውን አተያይ ይቃርማል።

በሁለቱም ጽንፍ ያሉ ሰዎችን ያቀርብ እንጂ ሁለቱንም ሃሳቦች የሚያስተናግድበት፤ የሚያዳምጥበት እና የሚረዳበት ሁኔታ እጅግ ይለያያል። ከእስራኤል በኩል የሚመጡ ወይም ፕሮ እስራኤል ለሆኑ ሰዎች የሚጠይቀው ጥያቄ የእሱም ጥያቄ እና ስሜት መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል። "ህመማችሁ ህመሜ ነው" ይላል።

የፍልስጤማዊያን የመብት ጥሰት ለሚከራከሩት ደሞ ንግግራቸውን ቶሎ ቶሎ ያቋርጣል። እሱ በሰነዘረው ሃሳብ እነሱ አድቫንቴጅ እንደያዙበት ሲያውቅ ቶሎ አውዱን ይቀይረዋል። እስራኤል በፍልሰጤማዊያን ላይ ያደረሰችው መከራ፣ ግፍ፣ ስደት “ሽብርተኛ” እንደሚያስብላት ሲነግሩት ቶሎ አጀንዳውን ያለባብሰዋል። ሃሳባቸውን ሳይጨርሱ ያቋርጣቸውን “did you condemn the October 7th Hamas attack?” የሚል ጥያቄ ይሰነዝራል።

ይሁን እንጂ ለአንድም እስራኤላዊ “did you condemn the Israel attack On Gaza?” አልጠየቀም።

ምክንያቱም የምዕራቡ አለም ሚዲያ ሸንጋይ እና ፈንጋይ እንጂ እውነት አይደሉም።

በመጨረሻም በዚህ ፕሮግራም ላይ ቀርበው የፍልስጤምን ጭቆና የሚያስተጋቡ፤ ነጥብ ሊቆጠርባቸው ነጥብ ይዘው ለሚመለሱ ሰዎች አድናቆት አለኝ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የCNN ፕሮግራም አቅራቢ የነበረው ማርክ ሌሞንት ሂል በ2018 እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያሳደረችውን ግፍ፣ ሰቆቃ እና ጥቃት እንድታቆም በተባበሩት መንግስታት የፍልስጤማዊያን የህብረት ቀን ላይ ተናገረ። "a free Palestine from the river to the sea" ሲል አስተጋባ። (ይህ መፈክር ከ1964 የፍልስጤማዊያን እንቅስቃሴ የተወሰደ እንደሆን ይታወቃል።)

ማርክ ህመማቸውን ታመመ፤ በስቃያቸው አዘነ። በቁጣ እና በእልህ ተናገረ። እሱ የፍልስጤማዊያን የህይወት ገመድን ለመቀጠል ሲናገር፤ የቢሮ አለቆቹ ግን፤ የምዕራቡ አስመሳይ የሚዲያ. አለቅላቂዎች፣ የዲሞክራሲ ተሽኮርማሚዎቹ ግን ከCNN ጋር የነበረውን ቆይታ እንዲያቋርጥ ደብዳቤ እየፃፉ ነበር።

የምዕራቡ አለም ሚዲያ እንዲህ ነው። ድሃ ፈንጋይ እንጂ አቃፊ አይደሉም። ሸንጋይ እንጂ ሃቅ አይደሉም። ለዚህም ልክ እንደ አልጀዚራ ያሉ ኢዲቶሪያል ፖሊሲያቸው ከምዕራቡ በተቃራኒ የቆሙ፤ ለሙስሊሙ አለም የቆሙ ሚዲያዎች ያስፈልጉናል። የተዛቡ ትርክቶችን የሚያስተካክሉ ሚድያዎች ያስፈልጉናል።

a free Palestine from the river to the sea!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ahmed Mohammed Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group