Translation is not possible.

የሚዲያን ነገር ወደ ሃገራችን ስናመጣው በርካታ ሙስሊሞች በሪፖርተርነት፣ በፕሮግራም እና ዘጋቢ ፊልም በማዘጋጀት፣ በመፅሄት አምደኝነት፣ ዋና አዘጋጅነት በሌሎች የቲቪ ሆስት አይነቶች ያገለግላሉ። ሴኩላር በሆነም ባልሆነም መንገድ።

ብዙዎቻችን እንተዋወቃለን። በአንድም በሌላ መንገድ ስራው ያገናኘናል። ፌስ የምናደርገውን ነገር እንነጋገራለን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻል ቢኖረውም በተለያየ ጉዳይ ለማነጋገር የምንደውልላቸው ሙስሊም ዶክተሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን፣ መምህራንና ሌሎቹም ስንደውልላቸው ፍቃደኛ የሚሆኑት ካሉን ምሁራን አንፃር ጥቂቶች ናቸው።

በተለይም ሴኩላር በሆነው ሚዲያ ለመቅረብ ዝግጁ አይደሉም። ምሁራን እንደሌሉን፣ በርካታ ባለሃብቶች እንደሌሉን ሁሉ ሚዲያው ጥቂት ሙስሊም ምሁራንን ነው የሚያውቀው። በሃይማኖታዊ ሚዲያዎቻችንም ተመሳሳይ ችግር ይከሰታል። እርስ በርስ ያለን መተሳሰር የላላ በመሆኑ ተፈራርጀን ተራርቀናል።

የዓለምም ሆነ የሃገር ፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያው ሜዳ ሚዲያ ነው። ውሃ ዋና የሚለመደው ውሃ ውስጥ በመግባት ብቻ ነው። ስላየኸው እና ስለሰማኸው አትለምድም።

ምሁራኖቻችን፣ ሃኪሞቻችን፣ መምህራን፣ ባለሃብቶቻችን፣ የየትኛውም የሙያ ባለቤቶች እባካችሁ ገፅታችን እንዲቃና፣ "አሉ" እንድንባል ደፍረን እንውጣ። እንተጋገዝ!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group