Translation is not possible.

ከሶስት ሳምንታት ወዲህ የቶክ ቲቪው ፒርስ ሞርጋን በፍልስጤም እና እስራኤል ጉዳይ የተለያዩ ሰዎችን ላይቭ ያቀርባል። በጦርነቱ ላይ ያላቸውን አተያይ ይቃርማል።

በሁለቱም ጽንፍ ያሉ ሰዎችን ያቀርብ እንጂ ሁለቱንም ሃሳቦች የሚያስተናግድበት፤ የሚያዳምጥበት እና የሚረዳበት ሁኔታ እጅግ ይለያያል። ከእስራኤል በኩል የሚመጡ ወይም ፕሮ እስራኤል ለሆኑ ሰዎች የሚጠይቀው ጥያቄ የእሱም ጥያቄ እና ስሜት መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል። "ህመማችሁ ህመሜ ነው" ይላል።

የፍልስጤማዊያን የመብት ጥሰት ለሚከራከሩት ደሞ ንግግራቸውን ቶሎ ቶሎ ያቋርጣል። እሱ በሰነዘረው ሃሳብ እነሱ አድቫንቴጅ እንደያዙበት ሲያውቅ ቶሎ አውዱን ይቀይረዋል። እስራኤል በፍልሰጤማዊያን ላይ ያደረሰችው መከራ፣ ግፍ፣ ስደት “ሽብርተኛ” እንደሚያስብላት ሲነግሩት ቶሎ አጀንዳውን ያለባብሰዋል። ሃሳባቸውን ሳይጨርሱ ያቋርጣቸውን “did you condemn the October 7th Hamas attack?” የሚል ጥያቄ ይሰነዝራል።

ይሁን እንጂ ለአንድም እስራኤላዊ “did you condemn the Israel attack On Gaza?” አልጠየቀም።

ምክንያቱም የምዕራቡ አለም ሚዲያ ሸንጋይ እና ፈንጋይ እንጂ እውነት አይደሉም።

በመጨረሻም በዚህ ፕሮግራም ላይ ቀርበው የፍልስጤምን ጭቆና የሚያስተጋቡ፤ ነጥብ ሊቆጠርባቸው ነጥብ ይዘው ለሚመለሱ ሰዎች አድናቆት አለኝ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group