UMMA TOKEN INVESTOR

Ezu Ha shared a
Translation is not possible.

አዳዲስ መረጃዎች:-

የዕብራይስጡ ጋዜጣ “እስራኤል ሃዮም”፡- ያህያ ሲንዋር፣ መሐመድ አል-ደይፍ እና መርዋን ኢሳን ጨምሮ መላው የሐማስ አመራር አሁንም በሕይወት አሉ በስራ ላይ ናቸውም፣ ይህም ለ“እስራኤል” ትልቅ ውድቀት ነው ብሏል።

የዕብራይስጡ ጋዜጣ “እስራኤል ሃዮም”፡ በ “የእስራኤል” መንግሥት ለተፈናቃይ ህዝቦቹ ቃል በገባው መሠረት በሰሜን ከሊባኖስ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ ያለው ረሠላም ሁኔታ እንዴት ሊሻሻል እንደሚችል ግልጽ አይደለም መቼ እንደሚሆንም ግልጽ አይደለም ሲል የኔታንያሁን መንግስት ወቅሷል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ezu Ha shared a
Translation is not possible.

አስቸኳይ | አል-ቃሳም፡ ከጋዛ በስተደቡብ በስተደቡብ ምስራቅ ከካን ዩኒስ ሰሜናዊ ምስራቅ አቅጣጫ በሚገኘው አል-ማርሪ አካባቢ ፀረ-ሰው በርሜል ቦምብ ለማፈንዳት በተካሄደው ዘመቻ 15 የጽዮናውያን ወታደሮች ተገድለዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ezu Ha shared a
Translation is not possible.

#ኑ እነዚህን እንተዋወስ ከመኝታ በፊት አትርሱ

#ኑ_ተፈደሉ//ውድ እህት ወንድሞቼ ከምኝታ በፊት//

🌹ተጋበዙልኝ ባረከሏሁ ፊኩም መልካም አዳር።🌹

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ezu Ha shared a
Translation is not possible.

👉 የሰውን ሐቅ ያለአግባብ መብላት

ኢስላም በጣም ካወገዛቸው እኩይ ተግባራት አንዱ የሰውን ሐቅ ያለ አግባብ መብላት ነው ። የሰውን ሐቅ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ያለአግባብ መብላት ክልክል የሆነው ፀያፍ ወንጀል በመሆኑ ነው ። ይህ በእምነት ሰዎች ላይ ሲሆን እኩይነቱ ይበረታል ። ምክንያቱም የእምነት ሰዎች ሰው ዘንድ የሚታመኑ በመሆናቸውና ስለማይጠነቀቁዋቸው ነው ።

ሶሞኑን አንድ ወደ እስልምና የገባ የቤተክርስቲያን አገልጋይ እስልምና ውስጥ እንዴት እንደገባ ስሰማ በጣም ደስ አለኝም አስደነገጠኝም ። የሰለመበት ምክንያት የሚከተለው የአላህ ቃል ነበር : –

« يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ كَثِيرًا مِّنَ الْأَحْبَارِ وَالرُّهْبَانِ لَيَأْكُلُونَ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۗ وَالَّذِينَ يَكْنِزُونَ الذَّهَبَ وَالْفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ »

التوبة ( 34 )

" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸት በእርግጥ ይበላሉ ፡፡ ከአላህም መንገድ ያግዳሉ ፡፡ እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ

ቅጣት አብስራቸው ፡፡"

ይህ የቤተክርስቲያን አገልጋይ የነበረው አዲሱ ሰለምቴ ይህን አንቀፅ ከወንድሞች ጋር እየተወያየ ሳለ ወንድሞች እዛ አካባቢ ያሉ ከእምነቱ አገልጋዮች ውስጥ የሰውን ሐቅ ያለአግባብ የሚበሉ እንዳሉ አላህ ነገሮናል ብለው አንቀፁን ሲያሰሙት አልቅሶ ይህማ ስለኛ ነው የሚናገረው ብሎ ነው ሸሀዳ የያዘው ። !!!!!!

ተመልከቱ ይህ ወንድማችን በመሰረታዊ የእምነት ጉዳዮች ( በዐቂዳ ) ላይ ያሉ ክህደቶችና ትላልቅ የሽርክ አይነቶች ትክክል ናቸው ብሎ እየተከራከረ ( ያደገበት ስለሆነ) የሰውን ሐቅ ያለአግባብ መብላት ግን ወዲያው ውስጡ ገብቶ ልቡን ለሐቅ ክፍት እንዲሆን ሰበብ ሆኖለታል ።

በዚህ አንቀፅ ምክንያት ሂዳያ ማግኘቱ ሲያስደስተኝ ያስደነገጠኝ ደግሞ ምናልባት እስልምና ውስጥ ያሉ የዲን አስተማሪ ወይም ዳዒ የሚባሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሰውን ሐቅ ያለ አግባብ የሚበሉ መብዛታቸው ለሰዎች ከሐቅ መንገድ መውጣት ሰበብ እንዳይሆን የሚለው ነው ።

ይህ የሰውን ሐቅ በዲን ስም የሚበላበት አንዱ ገፅታ ሲሆን አላህ ከከለከላቸው የሰውን ሐቅ ያለ አግባብ ከሚበላበት መንገድ ሌላው የጉቦ ጉዳይ ነው ። ጉቦ ዛሬ አለመስጠቱና አለመብላቱ ሐራም የተደረገ ነው የሚመስለው ። በሌላ አባባል ጉቦ መብላትም ይሁን መስጠት ዋጂብ የተደረገ ነው የሚመስለው ። ዛሬ ብዙ ዲን አላቸው የሚባሉ ሰዎች እንደቀላል ጉቦ ሲሰጡና ሲቀበሉ ይታያል ። ጉቦን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል : –

" وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ وَتُدْلُوا بِهَا إِلَى الْحُكَّامِ لِتَأْكُلُوا فَرِيقًا مِّنْ أَمْوَالِ النَّاسِ بِالْإِثْمِ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ "

البقرة ( 188)

" ገንዘቦቻችሁንም በመካከላችሁ በከንቱ (ያለ አግባብ) አትብሉ ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትኾኑ ከሰዎች ገንዘቦች ከፊልን በኃጢኣት ትበሉ ዘንድ ወደ ዳኞች አትጣሏት ፡፡"

በዚህ ዙሪያ የመጡ ሐዲሶች በጣም ብዙ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን አስፈሪም ጭምር ናቸው ። ከእነዚህ ውስጥ ለአብነት የሚከተለውን እንይ : –

-عَنْ عَبْدِاللَّهِ بْنِ عَمْرٍو – رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا – قَالَ :

" لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ الرَّاشِي وَالْمُرْتَشِي . "

رَوَاهُ أَبُو دَاوُدَ، وَالتِّرْمِذِيُّ وَصَحَّحَهُ

🔹 ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር – ረዲየላሁ ዐንሁማ – እንዲህ ይላል : –

" የአላህ መልእክተኛ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረግመዋል ።"

እነዚህና መሰል መረጃዎች ባጠቃላይ ኢስላም የሰውን ሐቅ ያለአግባብ መብላት አጥብቆ የከለከለ መሆኑን ያመለክታሉ ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group