UMMA TOKEN INVESTOR

Abuna Ibrahim shared a
Табасаранан алхьа кха дац.

«ያላዩት ሀገር አይናፍቅም።» የሚለው ትርክት መሰረተ ቢስ መሆኑን ምትረዳው ባላየኸው አላህ ናፍቆት ስትከንፍ ነው።

ሰዎቹ ናፍቆት ባሰመጣቸው ግዜ ተክዘዋል፣ ዋልለዋል፣ አልቅሰዋል፣ ከዋሻዎች እና ከባህር ዳርቻዎች ጎጆአቸውን ቀልሰዋል።

የአላህ ናፍቆት!

_________________________________________

ዒሳ ዐሰ 3 ሰዎችን ተመለከተ። ፊታቸው ተጨናብሷል፣ ሰውነታቸው ከስቷል፦ «ምንድነው እማየው! ምን ሁናችሁ ነው?» ብሎ ጠየቃቸው።

«ስለ ጀሀነም ሰምተን ፈርተን ነው» አሉት።

«አላህም ፈሪዎችን ሊያተርፍ ይገባል» ብሎ ትቶ አለፈ።

ሌላ 3 ሰዎችን ከመንገዱ አገኛቸው። ከመጀመርያዎቹ በላይ የሰውነት ገፅታቸው ተጎሳቅሏል፦ «ምን ሁናችሁ ነው! ምንድነው ገፅታችሁን እንዲህ የቀየረው? » ብሎ ጠየቃቸው።

«ጀነት ናፍቃን ነው» ብለው መለሱለት።

«አላህም ለተስፈኞች ምኞታቸውን ይሰጣል» ብሎ ትቷቸው አለፈ።

አሁንም 3 ሰዎችን አገኘ። ከመጀመርያዎቹ በባሰ መልኩ ሰውነታቸው ተጎሳቅሏል፣ እጅግ ከስተዋል፦ «ምን ሁናችሁ ነው እንዲህ የተጎሳቆላችሁትና የከሳችሁት?» ብሎ ጠየቃቸው።

«አላህን እንወደወለን/አላህ ናፍቆናል» አሉት።

«አንቱሙል ሙቀረቡን አንቱሙል ሙቀረቡን» ብሎ ያላህን ጉርብትና አበሰራቸው።

የአላህ ናፍቆት!

_________________________________________

«ያ አባ ማሕፉዝ! ምንድነው እንዲህ ከአምልኮ ጋር አቆራኝቶ ከሰው መቀላቀል የከለከለህ?» ብለው ጓደኞቹ ጠየቁት።

ዝም፤ መልስ አልሰጣቸውም።

«ሞትን አስታውሰህ ፈርተህ ነው?» ብለው ደገሙለት።

«ሞት! ሞት ደሞ ምንድነው?» አለ፤ በአግራሞት እያያቸው።

«ታድያ የቀብር እና የበርዘክ ፍራቻ ነው?» አሉት።

«ቀብር እና በርዘክ ደግሞ ምንድነው?» ብሎ አሳነሳቸው።

«ታድያ የጀነት ክጀላ እና የእሳት ፍራቻ ነው?» ብለው ጠየቁት።

«ስለምንድነው ቆይ ምታወሩት!!! ይኼ ሁሉ በእጁ የሆነውን ጌታ ስትወደው እኮ ያን ሁሉ ዝርዝር ያስረሳሀል። ቀድመህ ከተዋወቅከውም ለዚህ ሁሉ ፈተና እሱ በቂህ ነው።»

የአላህ ናፍቆት!

https://ummalife.com/Mohammed_jelal

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group