Translation is not possible.

" በፍፁም ብቻችሁን አትጓዙም ! YOU WILL NEVER WALK ALONE !"

ይህ አሁን የሊቨርፑል ደጋፊዎች ለተጫዋቾቻቼው የሚዘምሩት መዝሙር አይደለም ። ይህ የታላቁ ክለብ የሴልቲክ ደጋፊዎች በስታዲዮማቸው ለፍልስጤማውያን የሚዘምሩት መዝሙር ነው ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እዚያው እስራኤል ሂዶ እስራኤል ብቸኛ የሆነች ይመስል " እስራኤል ሆይ ብቻሽን አይደለሽም " አላት ። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክም እስራኤል ተጉዞ እስራኤልን " ብቻሽን አይደለሽም " አላት ! የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮንም እዚያው ሂዶ " እኔ እዚህ የመጣሁት እስራኤልን ብቻዋን እንዳልሆነች ለማሳየት ነው " አለ ። የጀርመኑ መርሀይተመንግስት ኦላፍ ስኩልዝም እስራኤልን " ጀርመን እያለች ብቻሽን አይደለሽም " አላት ። ብቸኛ ያልሆነቺዋንና መላ ምእራባዊ እንደ ልጁ የሚንከባከባትን እስራኤልን ብቻሽን አይደለሽም እያሉ ሲንቆለጳጵሷት የኔ ነሽ የኔ ነሽ ሲሏት በርግጥ ንፍቅናቸው ግብዝነታቸው ፍርደገምድልነታቸዝ አፍጦ ያገጠጠ መሆኑን ከማረጋገጥም በላይ ምን ያክል የሰብአዊነት ርዝራዥ እንኳ የሌለባቸው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው ።

በሰብአዊነት የተሞሉት ሀቀኞቹ የሴልቲክ ደጋፊዎች ግን ብቸኛዎቹን ፍልስጤማዊያንን " ብቻችሁን አትጓዙም " እያሉ ሲዘምሩላቸው ምናልባት ሰብአዊነት ያለው ሰው እንባውን መገደብ ሀዘኔታውንም መቋቋም ሊያቅተው ይችል ይሆናል ። እነዚህ የሴልቲክ ሰው የሆኑ የሰውነት ውሀ ልኮች የአውሮፓ ኦግርኳስ ማህበር የጣለባቸውን ቅጣት ንቀው ስለሰብአዊነት የዘርና የሀይማኖት ድንበር ሳይገድባቸው ሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ስለፍልስጤማዊያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰሙ ። " ከነፃዋ ፍልስጥኤም ጎን ነን ፍልስጤምም ነፃ ትወጣለች " አሉ ! ፍልስጤማዊያን ሆይ በዚህ የነፃነት ትግልም ውስጥ ብቻችሁን አትጓዙም ሁሌም ከጎናችሁ አለን YOU WILL NEVER WALK ALONE ሲሉ ከአንጀታቸው ከልባቸው አጋርነታቸውን አሳዩ ። በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተከታታይም የአትሌቲኮ ማድሪድንና የሴልታክን ጨዋታ ሊከታተል በቲቪ አፍጥጦ ሳለ የፍልስጤማውያንን የነፃየት የአልገዛም ባይነት ድምፅ በሴልቲክ ደጋፊዎች አማካኝነት ሰማ !!!

የአረብ ሀገራት መሪዎችና ተመሪዎች አፋቸው ተለጉሞ ጆሯቸው ተደፍኖ እጃቸው ተሳስሮ ሳለ እነዚያ የምእራብ አውሮፓ ሰብኦች ግን ሀሳብና ጭንቀታተው በስታዲየሙ የምትንከባለለው ፊኛ ሳትሆን እዚያ በጋዛ ፍርስራሽ ስር ስለነፃነት የሚከፈለው ዋጋ ነው !!!

የሴልቲክ ደጋፊዎችን የማመሰግንበት ቃል የለኝም !!

አንድ ቀን ፍልስጤማዊያን ነፃ ይወጣሉ ያኔ በፍልስጤማውያን ልብ ዘንድ የሴልቲክ ደጋፊዎች ታትሞ ሲወሳ ይኖራል !!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

Send as a message
Share on my page
Share in the group