Çeviri imkansız.

" ምእራባውያንን የፍልስጤሞች መገደል የማያሳስባቸው የሚገደሉት ሙስሊሞች ስለሆኑ ነው "

ፕሬዝዳንት ረጄብ ጦይብ ኤርዶጋን

ኤርዶጋን ላለፉት 20 አመታት ከምእራባውያን ጋር ባደረጉት እልህ አስጨራሽ የፖለቲካ የድፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትግል ቱርክን ከፍተኛ ዋጋ ስላስከፈላት የአረቦች ከምእራባውያን ጋር አብረው በቱርክ ላይ ማደምም ብዙ ተፅዕኖ ስለፈጠረባት ከዚያ ጫና እፎይታ ለመውሰድ ኤርዶጋን ባለፉት ወራት ለዘብ ማለትን መርጦ ነበረ ። ግና በፍልስጤም ጉዳይ ሁሌም ስሜታዊ የሆነው ኤርዶጋን የፍልስጤማውያን በወራሪዋ ሀገርና ግብረአበሮቿ መጨፍጨፍ ዳግም ከምእራባውያን ጋር ትግትግ እንዲገጥም አስገድዶታል ።

ኤርዶጋን አሁን ከምእራባውያንና ከእስራኤል ጋር የቃላት ጦርነት ላይ ነው ።

በኢኮኖሚና በማህበራዊ ድጋፍ የጋዛ የጀርባ አጥንት ከሆኑ ሀገሮች አንዷ የሆነቺው ቱርክ አሁን ዳግም ከምእራባውያን ጋር ያገረሸ ንትርክ ውስጥ ገብታለች ምክንያቱ ደግሞ የፍልስጤማውያን እልቂት ነው ።

ኤርዶጋን ዛሬ በሰጠው መግለጫ " ምእራባውያን ስለምን ለሚገደሉት ንፁሀን ያዝናሉ የሚሞቱትኮ ሙስሊሞች ናቸው የሙስሊሞች መሞት ደግሞ ለምእራባዊያን የሚያስደስት እንጅ የሚያሳዝን አይደለም " በማለት የምእራባውያን ይህ ሁሉ ፍርደገምድልነት ዋነኛው ምክንያት ኢስላም ጠልነት ሙስሊም ጠልነት ነው በማለት አውግዘዋቸዋል ።

ኤርዶጋን ለፍልስጥኤም ድጋፍ ሀገራትን ለማስተባበር እየሞከረ ቢሆንም ከሙስሊም ሀገራት የሚሰጠው ምላሽ ግን አሳዛኝ ነው ።

ቱርክና ኢራን ስለፍልስጤም በጋራ በሚቆሙበት ጉዳይ ላይ ከትላንት በስቲያ ሙምከራቸው የሚታወቅ ነው ።

ኤርዶጋን ሀማስን ሀገሩንና ህዝቡን ከወራሪዎች ነፃ ለማውጣት የሚታገል አርበኛ በማለት መግለፁ እስራኤልን ክፉኛ አስቆጥቷት የውግዘት መግለጫ እንድታወጣ መሆኑ ይታወሳል ። ኤርዶጋን አክሎም እስራኤልን " ህፃናትና ንፁሀንን ኢላማ አድርጎ የሚዋጋ ቤተእምነቶችን የሚያደወድም ብቸኛ ጦር ያላት ሀገር " በማለት ማውገዛቸው ይታወቃል።

ቱርክ እስራኤል ወደ አውሮፓ በቱርክ ግዛት ለማስተላለፍ ያሰበቺውን የጋዝ መስመርም እንድታቋርጥ አዛለች ።

#seid_mohammed_alhabeshiy

Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş