Translation is not possible.

አሉ ........

በጣም እንደምትወዳቸው ያላወካቸው እንደሚያስፈልጉህ ያልተረዳሀቸው ምናልባት ልብህ እነሱን ማስደሰትና ፈገግታቸውን ማየት አላማዋ ያረገችላቸው ሰዎች አሉ።

ከማንም በላይ ያስቡልሀል አትረዳቸውም። የነሱን ህመም ፣ችግር፣ስቃይ፣ሀዘን ችለህ ቆመህ ልታይ ፈፅሞ አትችልም ። ጉልበትህ ይተናል ልብህ ይደማል አይንህ ያነባል ጨጓራህ ይነዳል።

ከገቡበት እስኪወጡ ከተኙበት እስኪነቁ ከሄዱበት ደርሰው እስከሚመለሱ ብቻህን ትቀራለህ ሀሳብህ ልብህ ሁሉም ነገርህ እነሱ ጋር ይቀራል አንተን ተስፋ አሳቅፈው ይንክፋሉ ..

ልብህ እንዲሁም ሰውህ አብረው እስኪመለሱ እያነባህ በተስፋ መጠበቅ በዱዓህ መገደፍ ረቢን መጨቅጨቅ በቃ ህፃን መሆን!

ከጥልቅ ስሜት ጋር የተፃፈ ✍️ የታመሙትን ያሽርላቹ (ግልባጭ ለእህቶችም ነው...)

Send as a message
Share on my page
Share in the group