UMMA TOKEN INVESTOR

About me

★Electrical and Computer Engineer from AAiT,AAU ★M. Sc Candidate in AI ★MA in Leadership ★Software Developer ★Programmer ★Former Memebership Coordinator @ESSS ★Ethical Hacker ★Founder and CEO

Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…

(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዶ/ር ሙሐመድ ዿዊ አል-ዑሶይሚ ዛሬ ከነ ዶ/ር ኸሊልና ዶ/ር ሳሊም ጋር በነበረው ነድዋ ላይ ካነሳው ነጥብ መካከል፤ አንድ የሚያውቀው ሸይኽ MBC ላይ ፕሮግራም እንዲኖረው እንዳመቻቹለት ሲነግረው «እንደት ሙዚቃና ፊልም በቋሚነት በሚሰራጭበት ቲቪ ላይ ትቀርባለህ?» ስለው፤ «እነርሱ 24 ሰዓት የሚበክሉትን፤ አጋጣሞውን ካገኘኸው በ1 ሰዓት ባፈራርሰው አይሻልም ወይ?» አለኝ የሚል ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፏል።

ባገኘኽበት አጋጣሚ ሁሉ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራ። እንዳውም ብዙዎቹ የጠመሙ ሰዎች እንዲህ አይነት ቦታ ላይ እንጂ መስጅድና መድረሳ አታገኛቸውምና በጎዳናውም፣ በየቲቪውም፣ በየ ማኅበራዊ ሚዲያውም ተጣራ።

በተጨማሪም ዳዕዋ ስናደርግ ጥበብና አዘኔታ የተላበስን መሆን እንዳለብን ሲናገር፤ እዛው በሃገረ ኩዌይት የሚያውቀውን አንድ አጋጣሚ አወሳ።

አንድ ሰው አባቱ ይሞትበትና በጣም ስላዘነ ለአባቱ መልካም የዋለ መስሎት ፎቶውን አሳትሞ 2 ሜትር በ1 ሜትር አድርጎ ውጭ ላይ ለጠፈው። ቤቱ ውስጥም ሳሎን ላይ በትልቁ ለጠፈው።

ከዚያ አንዱ ሊያስተዛዝነው ቤቱ ሲገባ ያንን ፎቶ አየ። ወዳውም ምንድን ነው ይህ? ሐራም! (لا تدخل الملائكة بيت فيه كلب ولا صورة) እያለ ጮኸበት። ይህን ሐዲሥ ሲናገር "ውሻና ምስል ባለበት ቤት መላኢኮች አይገቡም!" ሲል ምስል የምትለዋን ቃል ሲናገር ወደዛ ወደተለጠፈው የሰውየው አባት ምስል በእጁ እየጠቆመ ነበር።

በመጨረሻም «እኔም የእኔን አባት የጠላ መላኢካ እጠላለሁ!» የሚል ይዘት ያለው መጥፎ ንግግር ተናገረ።

ለዚህ ሰቅጣጭ ንግግር የዳረገው የዚያ የሰው የአነጋገር ለዛና ጥበብ ማጣት ነው። ይህ ሰው አባቱ ሞቶበታል፣ እንባው አልደረቀም። መልካም የሠራ መስሎት ፎቶ ለጥፏል። ይህኛው ያንን ሲያይ «ወንድሜ ሆይ! ለአባትህ መልካም ለመሥራት የምታደርገው ጥረት ጥሩ ነው። ማሻ አላህ! እርሳቸውንም አላህ ይዘንላቸው። ግን ይህ ፎቷቸውን የለጠፍከው ነገር ላንተም ለርሳቸውም አይጠቅምም። እንዳውም ወንጀል ይሆንብሃል።…» ብሎ በለዘብተኛ አገላለፅ አስረድቶት፤ ከዚህ ሥራው ይልቅ ሸሪዓው በፈቀደው መልኩ ከአንድ መልካም ልጅ ለሞቱ ወላጆቹ የሚጠበቁበትን ነገሮች ጠቁሞት ቢያልፍ፤ ሐቂቃ ሰውየው ወዲያውኑ ያንን ምስል አንስቶ ከቻለ የተባለውን ሌላ መልካም ሥራ በሠራ ነበር።

ብቻ! የምንናገረው ነገር ሐቅ መሆኑን ብቻ አንመልከት። ያንን ሐቅ ሰዎች በሚቀበሉን መልኩና ወደ ቀልባቸው በቀላሉ እንዲንቆረቆር በሚያደርግ መልኩ ማቅረባችንንም እናስተውል። አላህ ዕውቀትን፣ ጥበብን፣ እዝነትንና አስተዋይነትን ያድለን።

||

t.me/MuradTadesse

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ባለፈ ሐዋሳ ላይ ሐምዛ መስጅድ አጠገብ በግለሰብ ቤት ሳቢያ ለቸርች ብለው መንገዱን ሁሉ አጥረውባቸው ነበር።

ከፊል ሙስሊሞችንም አስረዋቸዋል።

ነገር ግን ዛሬ እዛው ሐምዛ መስጅድ 3 ወንድሞቻችን ሸሃዳ ተቀብለዋል። አል-ሐምዱ ሊላህ!

ኢስላም ሰላም ነው፤ የተስፋፋውም በሰላም ነው። ሲነኩን እንበዛለን፣ አስተዋዮችም ነገሩን ታዝበው ትክክለኛውን መንገድ ይመርጣሉ።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼

==================

✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ።

ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል።

https://t.me/MuradTadesse/35708

*

ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት።

https://t.me/MuradTadesse/35742

ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር!

አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር።

የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል።

https://t.me/MuradTadesse/35632?single

ከተቋማችንም ጎን እንቁም።

የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ‼

===============

የመንግስት እና ሃይማኖት ግንኙነት በኢትዮጵያ፤ ትናንት ዛሬ እና ነገ

አዘጋጅ፦ የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት

የሶፍት ኮፒ (PDF) መገኛ ሊንክ፦ https://t.me/MuradTadesse/35708

እያንዳንዷን መስመር ምን ታሲዛለች፣ ምን ትርጉም አላት፣ ምን ተፈልጎባት ነው ብላችሁ በጥንቃቄና በጥሞና አንብቡት። በተለይም ከኡማው ጥቅምና ጉዳት አንፃር!

||

t.me/MuradTadesse

x.com/MuradTadesse

fb.com/MuradTadesse

ummalife.com/MuradTadesse

tiktok.com/@MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በተለይ ሐጅ የምታደርጉ ሰዎች ይህንን ወሳኝ ነጥብ ሳታዳምጡ እንዳትሄዱ!

እውነት ለመናገር እጃቸውን ወደ ላይ በማንሳት ዱዓእ እንደሚያደርግ ሰው አክት አድርገው ፎቶ የሚነሱ አጋጥመውኛል። ይህቺ እጅ የተነሳችው አላህን ለመለመን ሳይሆን ፎቶ ለመነሳት ነው። ጭራሽ በድፍረት በዚያ መልክ የተነሱትን ፎቶ ይሄው ዱዓእ እያደረግኩ ብለው ለሌሎች ሊያሰራጩትም ይችላሉ።

ምን ይህ ብቻ፤ ተመስጦ ዱዓእ የሚያደርግን ሰው አንድ ጊዜ ፈቀቅ በልልኝ'ማ ብለው ወደ ካዕባ ዙረው ፎቶ የሚነሱ ነበሩ።

በአጭሩ የፎቶ ጉዳይ በተለይም ሐጅና ሶደቃ ላይ የዘመኑ ፊትና ሆኗል ቢባል ማካበድ አይሆንም።

አዳምጧቸው'ማ ሸይኽ ዐብዱ-ር'ረዛቅ አል-በድርን!

||

t.me/MuradTadesse

4 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group