UMMA TOKEN INVESTOR

About me

አላህ ሆይ የበደለኞችን መጨረሻ አሳየን !

ሪድዋን ኢብኑ የሕያ Сhanged his profile picture
5 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፍለስጢኖች ላይ አይሁ'''ዳዎችና ምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆኑ የጨከኑባቸው እኛ ሙስሊሞችም ጨክነንባቸዋል።

የሆነ ሰሞን ግማሾቻችን አለቀስን ከንፈራችንን መጠጥን። አሁን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በምያስደፍር ሁኔታ ስለነሱ አናወራም አንፅፍም።

ብያንስ ዱዓ አድርጉ ብሎ የሚያስታውስ እንኳ ጠፋኮ።ቅድሚያ ራሴን ነው ምወቅሰው። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ እንደምንሰማው ንፁሃኑን መጨፍጨፉ እንደቀጠለ ነው ።

እኛም ዱዓ ማድረጋችንን መቀጠል ነው ያለብን። ለምን እንሰላቻለን ? እነሱ እኮ እድሜ ልካቸውን በጦርነት ነው የኖሩት።

ልጆችን "ስታድግ ምን መሆን ነው የምትፈልገው ሲባል እኛኮ አናድግም፣ሳናድግ ነው የምንሞተው" እያሉ ግን አይሰለቹም። እኛ የምንችላትን ዱዓ ማድረግን ለምን እንሰላቻለን።

ወረተኛ አንሁን ለማለት ነው !

t.me/alaqsatube

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሞት የህይወት መጨረሻ ሳይሆን የፀጋ ጅምርት ነው፣ አሊያም የስቃይና የዘላለማዊ ቅጣት ጅምርት ነው ጉዞህን ወዴት ማድረግ እንዳለብህ በማትፀፀትበት መልኩ አሁኑኑ ወስንና ተዘጋጅተህ ጠብቀው ‥

(كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَنْ زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ)

" ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው. ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ

ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም ፡፡"

[ዒምራን 185]

ዱንያ በፀጋዎቿ አታላህ ዛሬ ነገ እያለችህ እያዘናጋችህ ዘላለምህን ልትወጣበት በማትችለው ወጥመድ ውስጥ እንዳትከትህ ተጠንቀቅ !!

https://t.me/abumuazhusenedris

Telegram: Contact @abumuazhusenedris

Telegram: Contact @abumuazhusenedris

ወደ ቻናሉ⬇ መግባት⬇ ከፈለጉ http:https://t.me/abumuazhusenedris አሰተያየትና⬇ጥያቄዎች ⬇ካለዎት https://t.me/abumuazhusen_bot ይጠቀሙበት
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፍለስጢን ላይ ያሉ ወንድሞቻችንን በዱዓ እናስባቸው።

የማን ዱዓ ተቀባይነትን እንደምያገኝ አናውቅምና ሁላችንም በዱዓ እንበርታ። ለዚህ ማሳያ አንድ ታሪክ ላጋራችሁ።👇👇👇

በታብዒዮች ዘመን ነው ።

ዐብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ለግላቸው ጉዳይ ወደሆነ ሀገር ሄድኩ ይላሉ። የሄዱበት ሀገር በዝናብ እጦትና በድርቅ የተመታ ሀገር ነውና ህዝቡ በአምስት ወቅት ሰላት ላይ ቁኑት ያደርጋል ምንም ጠብ አይልም ። አንድ ቀን ህዝቡ ሰላቱን ሰግዶ እንደተለመደው ዱዓ አድርጎ ወደየ ቤቱ ተበተነ። እሳቸው ደግሞ ከዒሻ በኋላ መስጂድ ለማደር ገባሁ ይላሉ ። መስጂዱ ውስጥ አንድ ሰው ጥግ ላይ በሱጁድ አላህን እየለመነ አገኙት። እሱ ግን አላገኛቸውም ።

ይህ ባሪያ እንዲህ ይላል:-

" አላህ ሆይ ባሪያዎችህ ባንተ ተስፋ ቆርጠዋል በዝናብ እጦት ሰውና እንሰሳት አለቁ " በማለት እያለቀሰ ዱዓ አድረገ። ከመስጅድ ሳይወጣ ዝናብ ዘነበ። ሰውዬ በጭቃ እየተራመደ ሄደ ።

ኢብኑ ሙባረክ ተከትዬው ወጣሁ ይላሉ ። ዱካውን እየተከታተልኩት የሆነ ቤት በመስኮት ዘሎ ገባ ይላሉ። የገባበትን ቤት ጠጋ ብዬ ሳይ ጥቋቁር የተጎሳቆሉ ሰዎች በብዛት አሉበት። ይህ ቤት የባርያ መሸጫ እንደሆነ ተነገራቸው። በነጋታው ባለቤቱን ፈልገው አገኙትና ባሪያ መግዛት እንደሚፈልጉና እዛ ውስጥ ካሉት ይህን ሰውዬ ነው መግዛት ምፈልገው አልኩት ይላሉ። ባለቤቱም እዚህ ውስጥ ካሉት መርጠህ ውሰድ ይሄ ሰውዬ ሲቀር ኣላቸው። ምክንያቱም ከሁሉም ደካማና ለምንም የማይሆን ሰው ነው እሱ አይሆንህም ኣላቸው። እሳቸውም እንደምንም አሳምነው ገዝተው ወሰዱት። ባሪያው ጠየቀኝ ይላሉ "ባለቤቱ እውነታውን እየነገረህ ለምን እኔን መረጥክ"?

እሳቸውም ማታ ዱዓ አድርጎ በሱ ሰበብ ዝናብ እንደዘነበ እና የዚህንም ሚስጥር እንዲነግራቸው ጠየቁት። ከአላህ ጋር ያለህ ሚስጥር ምንድነው ብዬ ጠየኩት ይላሉ።

እሱም አልናገርም አለ። እሳቸውም እንዲነግራቸው ወተወቱት እሱም እሺ ትንሽ ጠብቀኝ ብሎ ሱጁድ ተደፍቶ ረጅም ዱዓ ማድረግ ጀመረ ። ቢጠብቁ አይነሳም። ጠጋ ብለው ሲሰሙት " አላህ ሆይ ሚስጥሬን ግልፅ አውጥተሀዋል ከዚህ በኋላ ምድር ላይ መቆየት አልፈልግም" ብሎ ዱዓ ያደርጋል። እሳቸውም ይነሳል ብለው ሲጠብቁ በዛው ሞተ።

ለአላህ እንዲህ አይነት ባሪያም አለው

✍በኢብኑ የሕያ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group