Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

ፍለስጢኖች ላይ አይሁ'''ዳዎችና ምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆኑ የጨከኑባቸው እኛ ሙስሊሞችም ጨክነንባቸዋል።

የሆነ ሰሞን ግማሾቻችን አለቀስን ከንፈራችንን መጠጥን። አሁን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በምያስደፍር ሁኔታ ስለነሱ አናወራም አንፅፍም።

ብያንስ ዱዓ አድርጉ ብሎ የሚያስታውስ እንኳ ጠፋኮ።ቅድሚያ ራሴን ነው ምወቅሰው። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ እንደምንሰማው ንፁሃኑን መጨፍጨፉ እንደቀጠለ ነው ።

እኛም ዱዓ ማድረጋችንን መቀጠል ነው ያለብን። ለምን እንሰላቻለን ? እነሱ እኮ እድሜ ልካቸውን በጦርነት ነው የኖሩት።

ልጆችን "ስታድግ ምን መሆን ነው የምትፈልገው ሲባል እኛኮ አናድግም፣ሳናድግ ነው የምንሞተው" እያሉ ግን አይሰለቹም። እኛ የምንችላትን ዱዓ ማድረግን ለምን እንሰላቻለን።

ወረተኛ አንሁን ለማለት ነው !

t.me/alaqsatube

Send as a message
Share on my page
Share in the group