UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

➲ፆመኛ ሲያፈጥር የሚለው ዱኣ!

▬ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

ዘሀበ ዞመኡ ወበተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አላህ

,               ትርጉም፦

►ጥም ተወገደ የደም ሥር ተብላላ በአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳውም ፀደቀ ማለት ነው።

▬اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ.

አላሁመ ኢኒ አሰአሉከ ቢረህመቲከ ለቲ ወሲዓት ኩለ ሸይኢን አን ተግፊረሊ

,         ትርጉም፦

አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ።

📚📚📚📚📚📚📚📚📚

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንኳን ለተከበረው የረመዷን ወር በሰላም አደረሰን፤ ወሩን በአግባቡ ከሚጠቀሙበት ሰዎች አሏህ ያድርገን!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በህመም ምክንያት ማፍጠር

~

ጥያቄ: የደም ማነስ ህመምተኛ ነኝ። ሃኪም "ረመዷን አትፁም። የግድ መብላት መጠጣት አለብህ" እያለኝ ነው። ምን ላድርግ?

መልስ:– ፆም የሚጎዳህ ከሆነ አፍጥርና ከዚያ ታካክሳለህ (ቀዷእ ታወጣለህ።) ምክንያቱም ይሄ ህመም በአላህ ዐዘ ወጀል ፍቃድ ይወገዳል። የደም ማነሱ ህክምና የሌለውና ሁሌም አብሮህ የሚቆይ ከሆነ ግን ለእያንዳንዱ ቀን ምስኪን አብላ።"

[ፈታዋ ሱኣሉን ዐለል ሃቲፍ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን: ቁጥር: 1633]

© Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከሙስሊም የሚጠበቀው እድሜው በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወደ አላህ የቀረበ ሊሆን፣ ይበልጥ ለአላህ የሚያደርገው ዒባዳ የጨመረ ሊሆን ነው። ከአላህ ጋር መገናኛው እየቀረበ እንደሆነ ሊያስብ ይገባል። መቼስ ማንም ሰው ቢሆን ሞት መቼ እንደሚያስደነግጠው አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ አንግቶ፣ የሞት ሃሳብ አንድ ከመቶ ያክል እንኳ አእምሮው ላይ ውል ሳይልበት ከዚያ ግን ከሞት ጋር ያመሸ ስንት ሰው አለ?! እና ሙስሊም የሆነ ሰው ዝግጁ ሊሆንና የተቅዋ ስንቅ ሊሰንቅ ይገባል።

ሸይኽ አልኸሥላን

=

© Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰዎችን ተዋቸው!!

ነገ ግርዶሹ ይነሳል፣ የተደበቁ ነገሮችም በሙሉ ይወጣሉ፣ ምስጥሮችም ይጋለጣሉ።

ወንጀልህን ከምትደብቀው በላይ መልካም ስራህን ደብቅ

ብቻህን እንደተወለድከው ሁሉ የምትሞተውም ብቻህን እንደሆነ እወቅ

ሰዎችን ተዋቸው

አይደለም ላንተ አላህ ከቀደረላቸው ውጪ ለራሳቸውም ምንም ማድረግ አይችሉም

ሁሌም ህያው በሆነው በአርሹ ባለቤት ተመካ

ከጭቃ የተፈጠሩና ነገም ወደዛው የሚመለሱ ደካማ የሰው ልጆችን ተስፋ አታድርግ፣የነርሱ መራቅና መቅረብ መውደድና መጥላታቸውም አንተ ዘንድ እኩል ይሁኑ

ለዲንህና ለዱኒያህ የሚበጅህን ነገር አውቀህ እዛ ላይ ፅና!

ጨለማው ሲወገድ ያለቀሱት ካለቃቀሱት ይለያሉ፣

ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ዓላማ ቢስ የሆኑ ሰዎች ካሰቡት ለመድረስ ቀን ከሌሊት ይለፉ የነበሩ ሰዎችን ተሳክቶላቸው ሲያዩ በቁጭት አለንጋ እራሳቸውን ይገርፋሉ

የሙእሚን ግቡ አላህን ማስደሰትና ጀነትን መውረስ ነውና ሳትደርስ የደረሰክ መስሎህ ከመንገድ እንዳትቀር፣

ከወዳጅ ነጥሎ ከሰፊው ቤት አውጥቶ ጨለማና ጠባቡ ጉርጓድ ላይ ወስዶ ሊጥልህ በድንገት የሚመጣውን ሞት ዘወትር በልብህ አስታውስ

በዚህ በጣም ከባድና አስቸጋሪ በሆነው የጘርጘራ ሰዓት ላይና ከዛም በኋላ የሚጠቅምህ ስራህ ነውና መልካም ስራ ላይ በርታ ፣የምትሰራው ስራም ኢኽላስ ይኑረው፣

ሰው ምን ይለኛል ብለህ መልካምን ስራ አትተው፣ ወንጀልንም አትዳፈር

ሰዎችን ተዋቸው!!

(ኡስታዝ አህመድ አደም)

Send as a message
Share on my page
Share in the group