UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I am a human being and I am not absolute , so correction precedes before blaming me. This is what Islam teaches us!

Kemal Yasin shared a
Translation is not possible.

✅ በወንጀል ላይ አትዘውትር ✅

📌🔺እንደሚታወቀው የጠላታችን የሸይጧን ዋና አላማ ያለ የሌለ ሀይሉን በመጠቀም እኛን አሳስቶ እሱ የገባበት እሳት ማስገባት ነው። ይህን አላማው እስኪያሳካ ተስፋ አይቆርምጥ ደከመኝ ሰለቸኝ አይልም። ባንዱ በር አልሳካ ወይም አልሸወድ ካልነው በሌላ በር ይመጣብሀል እንጂ መቸም አይተውህም ለምሳሌ፦

🔺ሽርክ እንደማትፈፅምለት ከተረዳ በቃ ልተወው አይልም በቢድአ በር ይመጣና ይሞክርሀል

🔺በዚህም ተስፋ ከቆረጠ ሌላ ከባባድ ወንጀሎች እንድትሰራ ይገፋፋሀል

🔺ካልሆነለት ከኢባዳ ከቁርአን ከሶላት እንድትዘናጋ ያደርጋል

🔺ያም ካልተሳካ እንድትዋሽ፣ እንድታጭበረብር ይገፋፋል ይህም ካልሆነ

🔺በአጅነብይ ሴት ወይም በወንድ በኩል ይመጣል። በመሀከላቸው አላህ የማይወደውን ግኑኝነት እንዲጀምሩ ያደርጋል። 👆ይህ ግን በተለይ በዚህ ዘመን አብዘሀኛው ሰው የሚሸወድበትና በቀላሉ በሸይጧን ወጥመድ የሚገባበት በር ነው።

✅ ነገር ግን ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር

🔺የሰው ልጅ ነንና እንሳሳታለን የማይሳሳት የለም። አላህም የሚጠይቅህ ለምን ተሳሳትክ ሳይሆን ከስህተትህ ባለመመለስ ነው። እንደምንሳሳትማ ቀድሞም ነግሮናል። ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር ከወንጀላችን በቶሎ ወደ አላህ የመመለሉ ጉዳይ ነው። የተውበት በር በቀንም በማታም ክፍት የተደረገውም ወደሱ እንድንመለስም ጭምር ነው። ትልቁ አደጋ ግን ሳንቶብት በዛው ወንጀል ዘውትረን ኻቲማችን እንዳይበላሽ ነው። ሸይጧን ደሞ ይህ ስለማይፈልግ በዛው እንድትቀጥል የተለያየ ኡዝር ያቀርብልሀል። ወንጀልን አሳንሰህ እንድትመለከት የሰደርጋል። አላህ መሀሪ ነው የሚል ማደንዘዣ ወግቶ ቁጭ ያረገኻል።

📌♻️ قال رجلٌ لزهير بن نعيم رحمه الله:- أتوصيني بشيء ؟ قال:- نعم احذر أن يأخذك الله وأنت على غفلة.

✅ አንድ ሰው ወደ ዙበይር ቢን ኑአይም ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው።

🔺በሆነ ነገር ትመክረኛለህ? ምክር እሻለሁ አላቸው። እሳቸውም፦ አዎ እመክርሀለሁ እሱም

🔺በወንጀል ላይ ሆነህ በመዘናጋት አላህ እንዳይዝህ (ሩህህ እንዳይወጣ) ተጠንቀቅ አሉት።

📚(صفة الصفوة ٩/٤)

♻️ መሳሳትህና ወንጀል ላይ መሆንህን ስትረዳ ወዲያው ቆም በል ወደ አላህ ተመለስ። ልብህ እያወቀ ባልሰማ በዛው ወንጀል አትቀጥል። ለተውበት ጊዜ አትስጥ ዛሬ ነገ እያልክ ያንን ወንጀል እየፈፀምክ ባለህበት ወቅት ሳታስበው በድንገት ሞት ሊመጣህ ይችላል። ይህ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለህ? ሞት እኮ በር አያንኳኳም ልግባ ወይ ብሎ አያስፈቅድም። በዛው ወንጀል ላይ ሆነን ኻቲማህ ካለቀ አስበው/አስቢው ነገ የውመልቂያማ በዛው በሞትክበት ሁኔታ ላይ ነው የምትቀሰቀሰው። የዛን ቀን እኮ

👉ቁርአን እየቀራ ሚቀሰቀስ አለ

👉እየሰገደ የሚቀሰቀስ አለ

👉ዳእዋ እያደረገ የሚቀሰቀስ አለ

👉በአላህ መንገድ እየታገለ የሚቀሰቀስ አለ

👉የሀጁ ተልብያ እያደረገ የሚቀሰቀስ አለ

👉ሌሎችም ብዙ ኸይር ላይ ሆነው ሚቀሰቀሱ ሲኖሩ

♻️አንተ ግን ያንን ወንጀል እየሰራህ ልትቀሰቀስ ትችላለህ። አላህ ይጠብቀንና

🔺ወይ እየዋሸህ

🔺ወይ እየሰረቅክ

🔺ወይ እያታለልክ

🔺ወይ ዝሙት እየሰራህም ሊሆን ይችላል።

✅ ተመልከትማ አላህ እነዛ ጀነትን ያዘጋጀላቸውና የደገሰላቸው ሰዎች ባህርይ ሲገልፅ ምን እንዳለ

🔺{{وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا۟ فَٰحِشَةً أَوْ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ فَٱسْتَغْفَرُوا۟ لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلُوا۟ وَهُمْ يَعْلَمُونَ}} آل عمران, 135

🔺{{ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ጀነት ተደግሳለች)፡፡}}

✅ በአጠቃላይ አውቀህም ይሁን ሳታውቅ ለሰራኸው ወንጀል ሁሉ ወደአላህ ተመለስ፣ ተፀፀት፣ እስቲግፋር አብዛ፣ ባንተና በአላህ ወካከል ያለውን ግኑኝነት አስተካክል፣ መልካም ስራን አብዛ፣ በወንጀል ላይ ወንጀል አትደራርብ። ሸርጡን ያሟላ ተውበት አድርግ

1⃣ ከወንጀሉ ራቅ (አቁም)

2⃣ አላህን በማመፅህና በመዳፈርህ ተፀፀት

3⃣ ዳግመኛ ወደዛ ወንጀል ላትመለስ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ይኑርህ

4⃣ የሰው ሀቅ ካለብህም መልስ

🔺በተጨማሪም ዱአ አብዛ

✍ ኢብኑ ኸይሩ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ምንኛ ያማረ ድምፅ ነው!

5 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Kemal Yasin Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group