UMMA TOKEN INVESTOR

SalahabuUmair shared a
6 month Translate
Translation is not possible.

የእስራኤልን ጉድ ስሙልኝማ

9 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

from the river to the sea, Palestine will be free

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
SalahabuUmair Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
SalahabuUmair shared a
Translation is not possible.

እስራኤሎች ፍልስጤምን በሂደት ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ሲጀምሩ የነበረውን ሁኔታ አንድ ፍልስጤማዊ አዛውንት እንዲህ ሲል አውግቷል ፦ " አንድ አይሁድ መጣን መሬቴን እንድሸጥለት ጠየቀኝ። እምቢ አልኩት!!! መሬቴን ለመውሰድ ሲል የፈለግኩትን ያህል ገንዘብ እንደሚከፍለኝ ነገረኝ። እኔ ግን አልተቀበልኩትም!! "ባዶ ቼክ ልስጥህና የፈለግከውን ያህል ገንዘብ ቁጥር ፃፍበት" አለኝ። ሆኖም አሻፈረኝ አልኩት።

"ይህቺን መሬትህን እንድትተውልኝ ምን ማድረግ አለብኝ? " ሲል ጠየቀኝ።

እንዲህ አልኩት ፦ " ባዶ ወረቀት ልስጥህና ዓለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በሙሉ ፍልስጤም ላይ ያላቸውን ድርሻ እንዲተዉልህ እያንዳንዳቸውን አስፈርመህ ና !! ከዚያ በኋላ እኔም እተውልሃለሁ። ፍልስጤም የኔ አይደለችም ፤ የሁሉም ሙስሊሞች እንጂ !! የሙስሊሞችን ሁሉ ፊርማ ካመጣህልኝ በነፃ እለቅልሃለሁ" አልኩት!!

አዎ ፍልስጤም የሁላችንም ናት!!

🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ገለፁ

ጉንፋን መሰል ህመም ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣ ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶክተሩ ገለፃ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡ ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፈሳሽ መውሰድ፣ ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣ መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣ በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ፡፡

በሌላ በኩል በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ዶክተሩ አክለውም፤ማህበረሰቡ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣ በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣ የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በ2 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ ባደረገው ምርመራ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የዝናብ ወራት ማለፉን ተከትሎ በጥቅምትና ህዳር ወቅት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ይከሰታል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ-ሃይል ዋና አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ተከስቷል፡፡

እጅን በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈን በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል፡፡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቂ እረፍት በመውሰድ፣ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች በመጠቀምና ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር፣ በርና መስኮቶችን በመክፈት፤ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ መከላከል እንደሚቻል ነው የገለፁት፡፡

በፋንታነሽ ተፈራ

Send as a message
Share on my page
Share in the group