UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Economics from Mekelle University and Master of Business Administration from Yardstick International College. Vice M/Director in manufacturing industry.

Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
HussenSiraj shared a
Translation is not possible.

✍️

ስለ አቅሷ ምን ያውቃሉ??

🕌አቅሷ ማለት፦

ነብዩﷺ ከጌታቸው ሰላት ለመቀበል ወደ ሰማይ ሲወጡ ጉዞ ያደረጉባት መስጂድ ናት።

{سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَى بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ}

{ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጂድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ አቅሷ መስጂድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው። ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡}

[አል_ኢስራእ:1]

🕌አቅሷ ማለት፦

ሙስሊሞች ከሂጅራ በኋላ ለአስራ ሰባት ወራት አካባቢ ተቀጣጭተው የሰገዱባት የመጀመሪያዋ ቂብላ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

መካ ከምትገኘው መስጂደል ሓራም እና መዲና ከምትገኘው መስጂደል ነበዊ ቀጥሎ ጓዝ ጠቅልሎ መሄድ የተደነገገላት ሶስተኛዋ መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

ነብዩﷺ ኢስራእ ባረጉበት ሌሊት ሁሉም ነብያቶች ተሰብስበውላቸው ኢማም ሆነው ያሰገዱባት መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

መስጂደል ሓራም እና መስጂደል ነበዊ ሲቀር ሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሰላት እሷ ላይ ሲሰገድ አምስት መቶ እጥፍ በላጭነት ያለው መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

ከመስጂደል ሓራም ቀጥሎ ምድር ላይ የተገነባችው ሁለተኛዋ መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

አላህ እሷንም ዙሪያዋንም በረካ ያደረጋት የሆነች መስጂድ ናት። {…الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ…}

🕌አቅሳ ማለት፦

ነብዩላህ ሙሳﷺ አላህ ወደ እሷ አስጠግቶ እንዲያሞተው እና እዝያው አካባቢ እንዲቀበር የተማፀነው ቦታ ናት።

🕌አቅሷ ማለት

ቡኻሪ በዘገበው ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦

«ነብዩ ሱለይማን መስጂደል አቅሷ ገንብቶ ካጠናቀቀ በኋላ ለአላህ ሶስት ነገር እንዲሰጠው ለመነው። "ፍርዱ የአላህን ፍርድ እንዲገጥም፣ ለማንም ሰው የማይሰጥ የሆነ ንግስና እንዲሰጠው እና ማንኛውም ሰው ሰላትን ለመስገድ ብቻ ፈልጎ ወደዚህ መስጂድ የመጣ እንደሆነ ከመስጂዱ ሲወጣ እናቱ እንደ ወለደችው ቀን ከወንጀሉ የነፃ ሆኖ እንዲወጣ" ነብዩﷺ ሁለቱ እንኳ በእርግጥም ተሰጥቶታል፤ ሶስተኛውም እንደ ተሰጠው እከጅላለሁ» ብለዋል።

🕌አቅሷ ማለት፦

የቂያማ ቀን መቀሽቀሻዋ ምድር ናት። መይሙና ቢንት ሳዕድ አስተላልፋው ኢማሙ አልባኒ ሰኺኽ ብለውታል።

🕌አቅሷ ማለት፦

የሚያረጋግጥ ግልፅ መረጃ ባይገኝም: ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባው ከፊሎች አባታችን ኣደም፣ ከፊሎቹ የነብዩ ኑሕ ልጅ፣ ሌሎቹ ደግሞ ነብዩ ኢብራሂም እንደ ገነቧት ይዘግባሉ። ከዝያም ነብዩላህ ሱለይማን አሳምረው እንደገነቧት ታሪክ ዘጋቢዎች ያወሳሉ።

ይህም የመስጂዷ ትልቅነት ከሚያሳዩ ነጥቦች አንዱ ነው።

ዓለም የካዳት ሙስሊሞች የረሷት አቅሷ እነሆ ዛሬ ውሻ ሆኖ ከመኖር አንበሳ ሆኖ መሞት ምርጫቸው ያደረጉ ጀግና ልጆቿ "ለበይኪ ለበይኪ ያ አቅሷ" ብለው ተነስተዋል።

አላህ የድል ባንዲራ ያስጨብጣቸው!!

ለበይኪ ለበይኪ ለበይኪ ያ አቅሷ

{وَأُخْرَى تُحِبُّونَهَا نَصْرٌ مِّنَ اللَّهِ وَفَتْحٌ قَرِيبٌ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ}

አብሽሩ ኢንሻ አላህ ድሉ ቅርብ ነው!!

🖊️ሐምዱ ቋንጤ

ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

https://t.me/hamdquante

አአአአአቅቅቅሷዬዬዬ አላህ አንቺንና በምድርሽ የሚገኙትን አማኞችን ይጠብቅ☝

https://t

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
HussenSiraj shared a
Translation is not possible.

ልንግርሽ ወይ አቅሷ❗️

አንቺ ክቡር ቦታ

በታላቁ ጌታ

ስሚኛ ልንገርሽ

አሁን ባልደርስልሽ

ቢበዛም ጠላትሽ

ጎራ ቢለዩብሽ

ጠልተው እስልምናሽ

አቅሷ ሆይ እባክሽ

ፍጡር ሊያጠፋሽ

ጦሩ ቢልክብሽ

ጠላት ቢሰዱብሽ

አንቺ የአሏህ ነሽ

አሜሪካ ቻይና

ኔቶም መከሩና

በሰው ሀይል መስሏቸው

ባንቺ መዝመታቸው

አንቺም ንገሪያቸው

ጌታዬ ጌታቹ ከአኔ ነው በያቸው

አማኞች በአለም በዱዓ ተጨንቀው

አንቺን ያስባሉ በያሉበት ሆነው

አቅሷ አትዘኚ መጠጊያሽ ብርቱ ነው

የሁሉ አስጠጊው ታላቁ ጌታ ነው።

ስሚኝ አንቺ ምድር

የፍልፅጤም ሀገር

በረመዷን ክብር

ቢደፋብሽ ባፈር

ፆመኛው ቢሰቃይ አስተናግዶ ችግር

አሁን እጅ አትስጪ በደስታሽ ልሰፈር።

✍ጁሀር ኡመር

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸

https://t.me/httsibnutemamAbumahi114

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group