ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት
~
ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን።
* ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል።
* የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው።
* የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም።
* ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ }
"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10]
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor