UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I am Muslim Thanks to Allah.

Translation is not possible.

    መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናትን??

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

አላህ እንዲህ እያለ፦

{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ}

{በዛሬዋ ቀን ዲናችሁ ሞላሁላቹ}

[ المائدة:3 ]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

የአላህ መልዕክተኛﷺ  እንዲህ እያሉ፦

{ቢድዓ በአጠቃላይ ጥመት ነው}

📚[ صحيح سنن ابن ماجه (42) ]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

ኢብኑ ዑመር  እንዲህ ይላሉ፦

{ቢድዓ በአጠቃላይ ጥመት ናት ሰዎች መልካም ብለው ቢያዯትም}

📚[ أصول الاعتقاد (11 /50)]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ይላሉ፦

{(ቀደምቶችን) ተከተሉ (አዲስ ነገር) አትፍጠሩ በእርግጥም (የቀደምቶች መንገድ) በቅቷችኋል። ሁሉም ቢድዓ ጥመት ናት}

📚[ الزهد لأحمد (896) ]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

የአላህ መልዕክተኛ በዲን ላይ ቢድዓ ለፈጠረ ሰው እንዲህ እያሉ፦

{ከእኔ በኋላ ዲን ላይ የቀየረ (የፈጠረ) ሰው አርቁት አርቁት (ይላሉ)}

ከዝያም ከኸውዳቸው የራቀ ሰው ይኾናል።

📚[ متفق عليه ]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

ኢማም አቡ ኸኒፋ እንዲህ ይላሉ፦

{(የቀደምቶችን) መንገድ እና  ፋና በመከተል ላይ አደራህ፣

አጠቃላይ ፈጠራ ከተባለ ነገር ተጠንቀቅ ምክንያቱም እሷ ጥመት ናት።}

📚[ ذم التأويل لابن قدامة (13) ]

💫\"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይላሉ።

ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦

{ዲን ውስጥ ቢድዓ ፈጥሮ መልካም ነገር ናት ብሎ የሚያስባት ሰው \"በእርግጥም ሙሐመድ መልዕክቱን በማስተላለፍ ላይ አታሎናል\" እያለ ነው} ምክንያቱም አላህ

﴿ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ ﴾

{በዛሬዋ ቀን ዲናችሁን ሞላሁላቹ} እያለን ነው።

\"የዛኔ ዲን ያልነበረ ነገር ዛሬ ላይ ዲን ሊኾን አይችልም\"

📚[ الاعتصام للشاطبي (1 /64) ]

ታድያ እንዴት \"መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ናት\" ይባላል❓

   

منقول

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Deresaw media Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እኔ ቁርዓንን አጠናሁ እሷ መፅሐፍ ቅዱስን አጠናች ከዛም.....

የኔ ወደ ኢስላም መቀየር የራሱ የሆነ ታሪክ አለው፣ ከባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው ቱርክ ውስጥ በ1996 ሲሆን በ1997 ተጋባን ሁለታችንም ስለ ሀይማኖታችን ግድ የለሾችና የራቅን ነበርን፣ በዛ ሁኔታ ለ10 ዓመታት ዘለቅን።

በድንገት አንድ ቀን ባለቤቴ ስለ እምነቷ ኢስላም መጨነቅ መጠበብ ጀመረች፣በዚህ ሁኔታ እያለች ከ2 ዓመት በኋላ በድርጊቷ መፀፀቷንና ክርስቲያን ማግባቷ ከኢስላም አንፃር ስህተት መስራቷን ነገረችኝ።

ከዚያም ወደ ኢስላም እንድገባ ታግባባኝና ትለምነኝ ጀመር፣እኔ ደግሞ በወቅቱ ስለ ኢስላም ምንም ግንዛቤና ዕውቀት የሌለኝ ሰው ነበርኩ፣ይሁን እንጂ እኔም ክርስቲያን ትሆን ዘንድ በውስጤ አስብ ነበር።

የአሜሪካ ሚሊታሪ አባል ነኝና ለስራ ወደ ቀጠር ኳታር ተመደብኩ በዚህም በጉዳዩ ሁለታችንም ቁጭ ብለን

ከተወያየን በኋላ እኔ ቁርዓንን ላነብና ላጠና እሷም መፅሐፍ ቅዱስን ልታነብና ከዛም ልንወስን ተስማማን።

ከዚያስ!? ከዛማ ቁርዓኑ ባነበብኩት ቁጥር እየሳበኝ እየማረከኝ መጣ፣ የቃላት ውበቱ፣ እርስ በርስ ስምም መሆኑ፣ከግጭት መፅዳቱ ወዘተ ምርኮኛው እያረገኝ መጣ። ከመወሰኔ በፊት እኔም መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዳለብኝ ወሰንኩና ጀመርኩት፣ለስድስት ወራት አጠናሁት፣ በፍፁም ከቁርዓኑ የተለየና በግጭትና አስቂኝ ታሪኮች የተሞላ መሆኑን አጤንኩ፣ባለቤቴም ተመሳሳይ ግራ መጋባት ተፈጥሮባት እንደነበር ተነጋገርንበት።

ለሁለት ዓመት ከራሴ ጋር ክፉኛ ከታገልኩ በኋላ ኢስላም ትክክለኛው ሀይማኖት መሆኑን አረጋግጬ በ2009 ረመዳን ወር ላይ south dakota ውስጥ በሚገኝ መስጂድ ኢፍጧር ላይ ሸሐዳዬን የምስክርነት ቃሌን ለአላህ ሰጠሁ።

አሁን ኢስላምን በሚገባ ተምሬ ተግባራዊ ሙስሊም በመሆን ዑምራም አድርጊያለሁ #አልሃምዱሊላህ !✌️❤

ወንድማችሁ አንዲ ነኝ"፣

Via Jemal Dawud Muzeyin

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የጎዳና ላይ እፍጣርን በተመለከተ ፈትዋ (የሸሪዓ ብይን ተሰጠ)::

《《《《《《●》》》》》》

የጎዳና ላይ እፍጣር በሸሪዓ እንደለለና በአንዳንድ ሀገሮች ላይ ተጀምረው ዛሬ ልማድ ሆኖ ማስቆም እንዳልተቻለ የሀገራችንና የምስራቅ አፍሪካ ሙቲ የሆኑት ታላቁ ዓሊም ዶ/ር ጀይላን ከድር ገመዳ የፈትዋ ብይን ሰጡ:: ዶ/ሩ አክለውም ሽሪዓ ውስጥ የለለ ብደዓ (እስልምና ውስጥ አዲስ ፈጠራ) መሆኑን በማስገንዘብ ነገ ማስቆም ወደማይችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት በአስቾካይ መቆም እንዳለበት አሳስቧል::

========***=========

በሌላ በኩል ታላቁ ዓሊም ዶ/ር ሸህ ሙሐመድ ሓሚዲንም በተመሳሳይ አቋም በመያዝ ታላቁ የጎዳና ላይ እፍጣር ብደዓ ከመሆኑ በተጨማሪ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይመዝናል በማለት ማስቆሙ የተሻለ መሆኑን አስረድቷል:: የጋራ እፍጣሮችን በየመስጅዱ ደጅ ላይ በማድረግ በጋራ በማፍጠር እና አቅም የለላቸውንም ማስፈጠር ይቻላል ብለዋል::

======*=======

ሁለቱም ተላላቅ ዶ/ሮች አብዮት አደባባይን በተመለከተ ሜዳው የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ሙስሊሙ እስላማዊ ትዕይንቶችን ከእፍጣር ውጭ በሌሎች ፕሮግራሞች ማሳየት ይቻላል ብሏል:: አመሻሽ ላይ በጨለማ ጎዳና ላይ እፍጣር ከማድረግ ወጣ ብለን በቀን በየአመቱ ሀገረአቀፍ የረመዳን አቀባበል እና የደዓዋ ፕሮግራም በአብዬት አደባባይ ማካሄድ ይቻላል በማለት አቅጣጫ ሰጥተዋል::

የጎዳና ላይ እፍጣርን በሸሪዓ ብይን ስከለከል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ነው::

1. የጎዳና ላይ እፍጣር ፕሮግራሙ የሚካሄደው አመሻሽ ላይ በመሆኑ ከእፍጣር በኃላ ወንዶች እና ሴቶች በጨለማ በመቀላቀላቸው በተለይ ከቤተሰብ ክትትል ዉጭ ሆኖ ከሁሉም አቅጣጫ ከሩቅ ወደ አደባባይ የተመሙ ወጣቶች መካከል ጨለማን ተገን አድርገው ብዙ ችግሮች ልፈጠሩ ይችላሉ ተብሏል::

2. በአደባባዩ እፍጣር ላይ ባለፈው አመት የተከሰተው ሴት እህቶቻችን ላይ በዱርዬዎች የደረሰው ልብሶቻቸውን በምግብ: በእርጎ: በወተት: በለስላሳና በመሳሰሉት ለእፍጣር በቀረቡ ምግቦች እና መጠጦች የለበሱትን ሂጃቦቻቸውን አውቀው በማጨመላለቅ ተበለሻሽተውባቸው ክብራቸው ተነክቷል:: ካደባባዩ ከወጡ በኃላም ጨለማን ተገን አድርገው ጎዳናዎች ላይ በየመንገዱ ትንኮሳዎች እና መተናኮሎች ተስተውሏል::

3. እንደሚታወቀው በአገራችን አንፃራዊ የፀጥታ ችግሮች ይከሰታሉ:: ጨለማን ተገን አድርገው በሁከት ፈጣሪዎች የፀጥታ ችግር ካጋጠመ በፀጥታ አስከባሪዎች ለመቆጣጠር ያስቸግራል::

4. እስካሁን የተካሄደው የአብዮት አደባበባይ የጎዳና ላይ እፍጣር ፕሮግራሞች አብዛኛው በመደበኛ የስራ ቀናት ላይ በመሆኑ ከቀኑ 5:00 ጀምሮ መንገዶችን በማዘጋጋት ሰፊ ህብረተሰብን መተላለፊያ መንገድ በማሳጣት ከፍተኛ የትራፍክ መጨናነቅን አስከትሏል:: ህብረተሰብን ማስቸገር እና ጎዳናዎችን ማዘጋጋት ከሙስሊም በተለይ ከፆመኛ አይጠበቅም::

5. ለዚህ እፍጣር ፕሮግራም ላይ ያለ በቂ ቁጥጥር እና ክትትል የሚባክኑ ንብረቶች እና የሰው ጉልበት ከፍተኛ በመሆኑ እንደማህበረሰብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይመዝናል::

~¤¤¤~

በመጨረሻም በጨለማ ጎዳና ላይ እፍጣር ከማድረግ ወደየመስጅዶች መልሰን አቅም ከለላቸው ከደሃ ማህበረሰብ ጋር ብናፈጥር የተሻለ መሆኑን ዑለማዎች አስረድቷል:: በየአመቱ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ሆኖ በእረፍት ቀን ላይ አገር አቀፍ የረመዳን አቀባበል እና ሰፊ የደዓዋ ፕሮግራም በአብዮት አደባባይ ላይ ማካሄድ እንደሚቻል አስገንዝበዋል::

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group