UMMA TOKEN INVESTOR

About me

አል ከሊመቱ ጠይባ

Translation is not possible.
🔺ዑለማዎቻችንን እንተዋወቅ
#ክፍል4
~~~
ኢማሙ አሕመድ፡ (164-241 ዓ.ሂ)
«ኢማሙ አህሊ ሱንና ወል ጀመዓ»
ሙሉ ስማቸው አቡ ዓብዱልሏህ አሕመድ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ሐምበል ሸይባኒ አል ማሩዚ ይባላሉ።
ኢማሙ አሕመድ በ164 ዓ.ሂ በባጝዳድ ተወለዱ።
ባጝዳድ በዚያን ጊዜ በበኑ አባስ ስርወ መንግስት ግዛት ስር ስለነበረች፣
አይነተኛዋ የሙስሊሞች ከተማ ነበረች።
ኢማሙ አሕመድ  አባታቸውን ገና የሶስት አመት ህጻን ሳሉ በሞት አጥተዋል።
የዘር ግንዳቸው ከነብዩልሏህ ኢብራሂም ዓለይሂ ስ-ሰላም ጋር የሚያያዝ ንጹህ ዓረብ ናቸው።
ኢማሙ አሕመድ ቁርአንን ገና በለጋ እድሚያቸው ነው የሐፈዙት።
✍️በ180 ዓ.ሂ የ16 አመት ታዳጊ በነበሩበት ጊዜ፣
የኢማሙ አቡ ሐኒፋ ታዋቂ ተማሪ በሆኑት በኢማም አቡ ዩሱፍ ላይ ሐዲሥን መማር ጀመሩ።
ከኢማም አቡ ዩሱፍ ጋርም ለሶስት አመታት ያክል በመቆየት ብዙ ነገሮችን ተምረዋል።
ኢማሙ አሕመድ በባጝዳድ ከብዙ ዑለማዎች ላይ ከተማሩ በኋላ፣
የሐዲሥ እውቀት አድማሳቸውን ለማስፋት ወደ ኩፋ፣ በስራ፣ መካ፣ መዲና፣ የመን፣ ሶሪያ እና ወደ አልጀዚራ አቀኑ።
ከመቶ በላይ ከሆኑ ሸይኾች ጋር ከተገናኙ በኋላም፣
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሐዲሦችን የማሰባሰብ ስራ ጀመሩ።
👉በ187 ዓ.ሂ ኢማሙ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢማሙ ሻፊዒይን በመካ አገኟቸው።
በኋላም ኢማሙ ሻፊዒይ ወደ ባጝዳድ ሲሄዱ፣
ኢማሙ አሕመድም አብረው ተቀላቅለው ከኢማሙ ሻፊዒይ ላይ የሒዲሥ እውቀታቸውን ይበልጥ አዳበሩት፣ አመጠቁት።
ኢማሙ ሻኢዒይ በኢማሙ አሕመድ የሐዲሥና የሱንና እውቀት ላይ በጣም ተስፋ ጣሉ።
እጅጉን ተገረሙባቸው፣ አድናቆትንም ቸሯቸው።
👉ጊዜው 204 ዓ.ሂ ነበር፤
ኢማሙ አሕመድ በአርባ አመታቸው ማስተማርን ጀመሩ።
ወደ 5,000 ያክል ተማሪዎች ይከታተሏቸዋል።
500 ያክሉ ደግሞ በየቀኑ ፊት ለፊታቸው በመገኘት ከርሳቸው ትምህርት የሚወስዱ ናቸው።
ኢማም ቡኻሪ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ኢማም ቲርሚዚይ
ከእነዚህ የእለት ተእለት ተማሪዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
✍️ኢማሙ አሕመድን ለ አመታት ተፋፍሞ ይበልጥ የጎላ ፈተና አጋጠማቸው።
ይሄውም <<ቁርአን ፍጡር ነው።>> የሚለው የሙዕተዚላዎች አስተሳሰብ ነበር።
በሰአቱ የነበሩት የበኑ አባስ መሪዎች አል መዕሙንና አል ሙዕተሶም፤
እንደ ኢማሙ አሕመድ ያሉ ዑለማዎችን የሙዕተዚላዎችን እርዕዮት ተቀበሉ ብለው ጫና አደረጉባቸው፣ አስገደዷቸው።
ይህ ጊዜ ለኢማሙ አሕመድና ለመሰል የዘመናቸው ዑለማዎች እጅጉን ፈታኝ ነበር።
ኢማሙ አሕመድ ግን ፈተናውን እንደምንም ተወጡት።
በኋላም አል ሙተወኪል የበኑ አባስን የመሪነት ስልጣን ተቆናጠጠ።
ለኢማሙም እውቅና ሰጠ፣ እርሳቸውም ተመቻቸው።
ማስተማራቸውንም ቀጠሉ።
✍️ከአስተማሪዎቹ መካከል፥
=================
#አቡ ዩሱፍ (ያዕቁብ ኢብኑ ኢብራሂም አል አንሷሪ)
#ኢማሙ ሻፊዒይ
#ሑሻይም ኢብኑ በሽር
#ኢብራሂም ኢብኑ ሰዒድ
#ያሕያ ኢብኑ ሰዒድ
#አቡ ሙሐመድ ስ ኡፍያን ኢብኑ ዑየይናህ
#ኢማም የዚድ ኢብኑ ሃሩን
#ኢማም ዋቂዕ ኢብኑል ጀራህ
እና ሌሎችም።
✍️ከተማሪዎቻቸው መካከል፥
================
#ኢማም ቡኻሪ
#ኢማም ሙስሊም
#ኢማም ቲርሚዚይ
#አቡ ዳውድ ሱለይማን
#አቡ ዙርራዓህ
#ዓብደልሏህ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ልጃቸው)
#ሷሊሕ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ልጃቸው)
#አቡል ሐሰን ዓሊ ኢብኑ ሙሐመድ አል መውሩዲ
#አቡበከር አል አሥረም
#ሐምበል ኢብኑ ኢስሐቅ
#አቡል ቃሲም አል በጘዊይ
እና ሌሎችም።
✍️ከመጽሃፍቶቻቸው መካከል፥
==================
ኢማሙ አሕመድ ብዙ ድርሳናቶች አሏቸው።
ከነዚህም ውስጥ፦
📚ሙስነድ ኢማም አሕመድ (ከ30, 000 ገደማ በላይ ሐዲሦችን ያቀፈ ነው።)
📚አስ-ሱንና
📚ኡሱሉ ሱንና
📚ኪታቡል ዒለል ወመዕሪፈቲ ሪጃል
📚ኪታቡል መናሲክ
📚ኪታቡ ዙህድ
📚ኪታቡል ኢማን
📚ኪታቡል መሳኢል
📚ኪታቡል አሽሪባ
📚ኪታቡል ፈራኢድ
📚ኪታቡ ር-ረድ
📚ኪታብ ፈዷኢሉ ሶሐባ
📚ኪታብ ጦዓቱ ርረሱል
እና ሌሎችም።
✍️የዑለማዎች ውዳሴ፦
=============
✔️ኢማሙ ሻፊዒይ ስለ ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፦
"ከባጝዳድ ለቅቄ ስወጣ፣
ከአሕመድ ኢብኑ ሐምበል የበለጠ
በጎ ስነ ምግባር ያለው፣ አዋቂ፣ ምሁር ማንንም ትቼ አልወጣሁም።"
"እንዲህ ብለዋል፦
አሕመድ ኢብኑ ሐምበል በብዙ የእውቀት መስኮች ተቀዳሚ ምሁር ነው።
በፊዊህ፣ በሐዲሥ፣ በቁርአን፣ በተቅዋ እና በሱንና እውቀት።"
✔️ልጃቸው ዓብደልሏህ አቡ ዙርራዓህ እንዲህ ሲለኝ ሰምቻለሁ ይላል፦
"አባትህ (አሕመድ) አንድ ሚሊዮን ሐዲሥ ሸምዷል።"
✔️ዓሊ አልመዲኒ እንዲህ ይላል፥
አላህ ይህንን ዲን በሪዳ ዕለት (ሰዎች ነብያችን የሞቱ ጊዜ ወደ ኩፍር በተመለሱበት ዕለት) በአቡበከር ሲዲቅ አጠንክሮታል።
አሁንም በሚህናህ ዕለት (ሰዎች ቁርአን ፍጡር ነው ብላችሁ በሉ ተብለው በተገደዱበት ዕለት) ይህን ዲን በአሕመድ ኢብኑ ሐምበል አጠንክሮታል።"
✔️አቡ ሠውር እንዲህ ይላሉ፥
"አሕመድ ከሱፍያነ ሠውሪ የበለጠ አዋቂ ነበር።"
✔️የሕያ ኢብኑ መዒን እንዲህ ይላል፦
"ሰዎች እንደ አሕመድ ኢብኑ ሐምበል እንድንሆን ይፈልጋሉ።
በአላህ ይሁንብኝ፣ መቼም አንሆን።
እንኳን እንደ አሕመድ ያለን ጠንካሮች ልንሆን ቀርቶ፣
የአሕመድን ፈለግ ለመከተል እንኳ ጠንካራ አንሆንም።"
✔️ዓብዱል ማሊክ አልመይሙኒ እንዲህ ይላል፦
"አይኖች ከአሕመድ ኢብኑ ሐምበል የበለጠ ሰው አይተው አያውቁም።"
✔️ቁተይባህ ኢብኑ ሰዒድ እንዲህ ይላል፦
"ሱፍያን ሠውሪ በሞተ ጊዜ፣ ተቅዋም አብሮ ሞተ።
ሻፊዒይ በሞቱ ጊዜ ለሱንና በትክክል እጅ መስጠት አብሮ ሞተ።
አሕመድ የሞቱ ጊዜ፣ ቢዲዓ ተፈጠረ።"
ሌሎችም ውዳሴዎች አሉ።
✍️ህልፈታቸው፥
============
ኢማሙ አሕመድ ለዘጠኝ ቀናት ያክል ታመው፣
እለተ ጁሙዓ ረቢዓል አወል 12, 241 ዓ.ሂ በ77 አመታቸው ከዚህች አለም በሞት ተለዩ።
የቀብር ስነ ስርአታቸውም በባጝዳድ ተፈጽሟል።
በዚህ ዕለትም አንድ ሚሊዮን ያክል ሰዎች በሶላተል ጀናዛ ላይ ተሳትፈዋል።
በአጠቃላይ በአለም ደረጃም ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ሰግደዋል።
አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳይቱም 20, 000 ያክል አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች በዚህ ዕለት እስልምናን ተቀብለዋል።
አላሁ አክበር‼️
ኢማሙ አሕመድ ታላቅ ፈርጥ ናቸው።
ኢማሙ አሕመድ ከአራቱ ታዋቂ የፊቂህ ጠበብቶች ውስጥ አንዱ ናቸው።
የሐናቢላ (ሐንበልያ) መዝሃብ መሰረትም ናቸው።
ረሒመሁልሏህ ራሕመተን ዋሲዓ።
((ለበለጠ መረጃ፥
ሲየሩል አዕላም አንኑበላዕ፣ ቮሊዩም 11
ተዝኪረቱል ኹፋዝ (የኢማሙ ዘሃቢይን)
እና ሌሎችንም ተመልከቱ።
https://t.me/WATESiMU
Telegram: View @WATESiMU

Telegram: View @WATESiMU

فوائد : أبي لقمان فؤاد بن نغاش ስብና ካላማረ መልክ መልከ ጥፉ ነው
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
🔺ዑለማዎቻችንን እንተዋወቅ‼️
#ክፍል3
~~~
#ኢማሙ ሻፊዒይ፡ (150-204 ዓ.ሂ)
ሙሉ ስማቸው አቡ ዓብዱልሏህ ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ ኢብኑ አባስ ኢብኑ ዑሥማን ሻፊዒይ ይባላሉ።
በ150 ዓ.ሂ በጋዛ (አስቃላን) በሃገረ ሶሪያ ተወለዱ።
የዘር ግንዳቸው ከቁረይሽ ጎሳ (ዓብዱል መናፍ) የተመዘዘ ሲሆን፣
ከነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የዘር ግንድ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ብቸኛው ኢማም ናቸው።
ሻፊዒይ አባታቸውን ያጡት ገና በለጋ እድሚያቸው ስለነበር፣
ያደጉት ከየመናዊቷ እናታቸው ጋር በከፋ ድህነት ውስጥ ሁነው ነው።
ገና የሰባት አመት ህጻን በነበሩ ጊዜ ቁርኣንን ሐፍዘዋል።
በአስራ ሶስት አመታቸው ደግሞ የኢማሙ ማሊክን "ሙወጦእ" ሐፍዘዋል።
በወቅቱ የመካ ሙፍቲ የነበሩት የሻፊዒይ ሸይኽ ሙስሊም ኢብኑ ኻሊድ ለሻፊዒይ ፈቅደውላቸው በአስራ አምስት አመታቸው ፈተዋ መስጠት ጀምረዋል።
✍️ ሻፊዒይ ለእውቀት ካላቸው ጉጉት የተነሳ ከመካ ወጣ አሉ።
በሃያ አመታቸው ገደማ ወደ መዲና በማቅናት ከኢማሙ ማሊክ ላይ ለስምንት ወራት ያክል ተምረዋል።
ኢማሙ ማሊክም <<ሙወጦእን>> በለጋ እድሚያቸው በሐፈዙት በኢማሙ ሻፊዒይ ይደነቁ ነበር።
የሻፊዒይን የእውቀት አቀባበልና የአረዳድ ፍጥነታቸውን በጣም ያደንቁት ነበር።
ኢማሙ ማሊክ ተማሪያቸውን ኢማሙ ሻፊዒይን እንዲህ ሲሉ ይገልጿቸዋል፥
"ወደኔ ለመማር ከመጡ ተማሪዎች ውስጥ እንደ ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ ሻፊዒይ ያለ ብሩህና አዋቂ አላየሁም።"
ሻፊዒይ ከስምንት ወራት ቆይታ በኋላ ወደ መካ ተመልሰዋል።
ከታላቁ ዓሊም ከሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ ላይም ተምረዋል።
ኢማሙ ሻፊዒይ ኢማሙ ማሊክንና ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህን በተመለከተ እንድህ ብለዋል፥
"ኢማሙ ማሊክና ሱፍያን ባይኖሩ ኑሮ፣
እውቀት በሒጃዝ ውስጥ አይቆይም ነበር።"
ሻፊዒይ ቁርኣንና ሐዲሥን ከ81 በላይ ከሆኑ ዓሊሞች ላይ ተምረዋል።
👉ሻፊዒይ በ34 አመታቸው ወደ ባጝዳድ አቀኑ።
እዚያም ለሶስት አመታት ያክል ከኢማም ሙሐመድ ላይ ተምረዋል።
ኢማሙ ሻፊዒይ ስለ ኢማም ሙሐመድ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
"ከኢማም ሙሐመድ በላይ የአላህን ኪታብ አዋቂ የሆነ አንድንም አላውቅም።"
ኢማም ሙሐመድም ስለ ሻፊዒይ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፥
"የፊቂህ (የእውቀት) በር ለህዝቦች ተዘግቶ ነበር፤
አላህ በሻፊዒይ ሰበብ ከፈተው።
ሻፊዒይ የዲኑ ሙጀዲድ (አዳሽ) ነው።"
ኢብኑ ራሓዊ <<ኢማሙ ሻፊዒይ እንደት በልጅነታቸው ይህን ሁሉ መፅሀፍ ሊሐፍዙ ቻሉ??>> ተብለው ተጠይቀው፥
"አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ በወጣትነታቸው ምጡቅና በሳል አስተሳሰብ ሰጥቷቸዋል" አሉ።
ኢማሙ ሻፊዒይ የሐነፍያንና የማሊኪያን ፊቂህ በማጥናት የራሳቸውን የሻፊዒያ ፊቂህ መሰረት ጥለዋል።
👉ኢማሙ ሻፊዒይ የኸሊፋውን ዑሥማን ኢብኑ አፋን ረዲየልሏሁ ዓንሁ የልጅ ልጅ ሐምዲያህ ቢንት ናፊን በመካ አግብተው ሶስት ልጆችን ወልደዋል።
ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ ስማቸውም፥ ዑሥማንና ሐሳን ይባላሉ።
አንዷ ልጃቸው ሴት ስትሆን ስሟም ፋጢማ ትባላለች።
#ከአስተማሪዎቹ መካከል፥
===============
#ሙስሊም ኢብኑ ኻሊድ (በመካ)
#ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ (በመካ)
#ኢብራሂም ኢብኑ የሕያህ (በመዲና)
#ኢማሙ ማሊክ ኢብኑ አነስ (በመዲና)
#ዋቂዕ ኢብኑል ጀራህ (በኩፋ)
#ሙሐመድ ኢብኑ ሐሳን (በበስራ)
#ሐማድ ኢብኑ ኡሳማህ (በኩፋ)
#ዓብዱል ወሃብ ኢብኑ ዓብዱል መጅድ (በበስራ)
እና ሌሎችም።
✍️ከተማሪዎቻቸው መካከል፥
================
#ኢማም አቡ የዕቁብ
#አቡ ኢብራሂም ኢስማዒል ኢብኑ ያሕያ
#ረቢዕ ኢብኑ ሱለይማን
#አቡ ዓሊ አለከራቢሲ
#ኢብራሂም ኢብኑ ኻሊድ
#ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (በጥቂቱ)
እና ሌሎችም።
📚ከመጽሃፍቶቻቸው መካከል፥
==================
ኢማሙ ሻፊዒይ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ድርሳናቶች አሏቸው።
ከነዚህም ውስጥ፦
📚ኪታቡል "ኡም" (በጣም ታዋቂ ኪታባቸው ነው።)
📚አር-ሪሳላህ አልጀዲዳህ
📚ኪታቡል ሱነን
📚ኢኽቲላፉል ሐዲሥ
📚አሕካሙል ቁርኣን
📚ኢኽቲላፉል ሐዲሥ
📚ሲፈቱል አምር ወንነሂይ
📚አል ኢምላ
📚ኢብጣሉል ኢስቲሕሳን
📚ኢኽቲላፉል ኢራቂያኒ
📚ኪታቡል ሑጃህ
📚ኢኽቲላፉል ማሊክ ወሽሻፊዒይ
እና ሌሎችም።
✍️ህልፈታቸው፥
============
ኢማሙ ሻፊዒይ በመጨረሻም ወደ ግብጽ በማምራት ትንሽ ከቆዩ በኋላ፣
በድንገተኛ ህመም ምክንያት፣
እለተ ሐሙስ ከዒሻእ ሶላት በኋላ በወርሃ ረጀብ የመጨረሻው ቀን ሙተው ጁሙዓ በካይሮ በበኑ ዓብዱል ሐኪም ቫውልት መቃብር ተቀብረዋል።
አመቱም 204 ዓ.ሂ ነበር።
እድሚያቸው 54 አመት ነው።
ሻፊዒይ ከአራቱ ታዋቂ የፊቂህ ጠበብቶች ውስጥ አንዱ ናቸው።
ረሒመሁልሏህ ራሕመተን ዋሲዓ።
https://t.me/WATESiMU
Telegram: View @WATESiMU

Telegram: View @WATESiMU

فوائد : أبي لقمان فؤاد بن نغاش ስብና ካላማረ መልክ መልከ ጥፉ ነው
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Abu_luqman Сhanged his profile picture
1 month
Translation is not possible.
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
🔺ዑለማዎቻችንን እንተዋወቅ
#ክፍል2
~~~
ኢማሙ ማሊክ፡ (93-179 ዓ.ሂ)
👉ሙሉ ስማቸው ማሊክ ኢብኑ አነስ ኢብኑ ማሊክ ኢብኑ አቡ ዓሚር ይባላሉ።
በ93 ዓ.ሂ በመዲና-ሳዑዲ ዓረቢያ ከተከበሩ ቤተሰቦች ተወለዱ።
((ከፊሎቹ በ90 ዓ.ሂ ወይም በ95 ዓ.ሂ ወይም በ94 ዓ.ሂ ብለዋል።
ኢማሙ ዘሃቢይና ሌሎችም ግን በ93 ዓ.ሂ የሚለውን አስፍረዋል።))
የዘር ግንዳቸው ከየመን የተመዘዘ ነው።
አያታቸው ማሊክ ኢብኑ አቡ ዓሚር ታቢዒይ ሲሆኑ የታወቁ የሐዲሥ ዘጋቢ ናቸው።
እናታቸው አሊያህ ቢንት ሻሪክ ኢብኑ ዓብዱራሕማን አልአዝዲያህ ትባላለች።
ኢማሙ ማሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ፣
በመዲና ኢስላማዊ የሸሪዓ ህግን ለማጥናት ጽኑ ፍላጎት ስለነበራቸው ፊታቸውን ወደ ፊቂህ ትምህርት አዞሩ።
ኢማሙ ማሊክ የነብዩን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሶሐቦች ባዩና በነርሱም ላይ ከተማሩ ሶስት መቶ ያክል ታቢዒዮች ላይ ተምረዋል።
በመዲና ብዙ ህይወታቸውን 95 ያክል መሻኢኾች ላይ በመማር አሳልፈዋል።
1725 ያክል የነብዩን ሐዲሦች የያዘውን "ሙወጦእ" የተሰኘውን ታዋቂ ኪታባቸውን የዘገቡትም ከነዚሁ መሻኢኾች ነው።
✍️ኢማሙ ማሊክ፡ ዓብደላህ ኢብኑ ዑመርን ከሰላሳ አመት በላይ ካገለገለውና በአንድ ወቅት አሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑ ኸጥጧብ ዲን እንዲያስተምር ወደ ግብጽ ልከውት ከነበረው ከናፊእ ላይ ቁርአንና ሐዲሥን ለአስር አመታት ያክል ተምረዋል።
ኢማሙ ማሊክ አንድን ሐዲሥ ውዱእ ሳያደርጉ አይዘግቡም ነበር።
ከመዘገባቸው በፊትም የእያንዳንዱን ግልሰብ ምንነት በጥልቀት ያጠኑ ነበር።
ኢማሙ ማሊክ ለ62 አመታት ያክል በማስተማርና ፈተዋ በመስጠት አገልግለዋል።
ከርሳቸው 1300 ያክሉ ሰዎች ሐዲሥን ዘግበዋል።
የኢማሙ ማሊክ ቤት የኢብኑ መስዑድ ቤት የነበረ ነው።
ከበሩም ላይ "ማሻ አላህ" የሚል ጽሁፍ ነበረበት።
ኢማሙ ማሊክ ረዝም፣ ጀግና፣ ቆራጥ፣ ትሁትና ቸር ናቸው።
አል-መንሱር ሶስት ሺህ ድርሃም ሰጥቶ ከመዲና ለቀው ወደ ባጝዳድ እንዲሄዱ ሲያዛቸው፣ እርሳቸው ግን ትዕዛዙን ነቅፈው በመዲና መቀመጥን መርጠዋል።
አል-መንሱር ለርሱ ህዝቡ ቃለ መሃላ እንዲገባ ሲያዝም፣ ይህ ቃለ መሃላ አይቻልም ብለው በቆራጥነት ሐቅን ሳይደብቁ ፈተዋ ሰጥተዋል።
ኢማሙ ማሊክ ማስተማር የጀመሩት ገና የ17 አመት ወጣት ሆነው ሳለ ነው።
#ከሸይኾቻቸው መካከል፦
—---------------------—
✔️ናፊእ
✔️ዓብደልሏህ ኢብኑ ዛቅዋን
✔️ሒሻም ኢብኑ ዑርዋህ
✔️ያሕያ ኢብኑ ሰዒድ
✔️ዓብደልላህ ኢብኑ ዲናር
✔️ዘይድ ኢብኑ አስለም
✔️ኢማም አዝዙህሪ
✔️ዓኢሻህ ቢንት ሰዒድ ኢብን አቢወቃስ
✔️ዓብደልሏህ ኢብኑ አቡበከር ኢብኑ ሃዝም
✔️ዓብዱራሕማን ኢብኑ ቃሲም
✔️ኢብራሂም ኢብኑ ዓብደልላህ አልመቅደሲይና ሌሎችም ይገኙበታል።
✍️ኢማሙ ማሊክ ዒልም የተማሩት ንጹህ፣ ዛሂድና እውነተኛ ከሆኑ ሰዎች ነው።
ዓላማህ ዙልቃኒ እና ዱላቂ የኢማሙ ማሊክ አስተማሪዎች ዘጠኝ መቶ ይደርሳሉ ብለዋል።
ኢማሙ ነወውይ ደግሞ በተሕዚቡል አማእ ላይ ዘጠኝ መቶ ይደርሳሉ፦ ከነዚህም ውስጥ ሶስት መቶዎቹ ታቢዒዮች ሲሆኑ ስድስት መቶዎቹ ደግሞ አትባዑ ታቢዒይን ናቸው ብለዋል።
👉ከተማሪዎቻቸው መካከል፦
—---------------------------
እንደ ሐፊዝ ኢብኑ ከሢርና ኢማሙ ዘሃብይ ያሉ አኢማዎች የኢማሙ ማሊክን ተማሪዎች ከብዛት አንጻር መጥቀስ አይቻልም ብለዋል።
ቃዲ ዒያድ ግን 1300 ያክሉን ጠቅሰዋል።
ሐፊዝ ዳረቁጥንይ 1000 ደግሞ ያክሉን ጠቅሰዋል።
ሐፊዝ አቡበከር ኸጢብ አልባጝዳዲይ ደግሞ 993 ያክሉን ጠቅሰዋል።
በፊት የርሳቸው አስተማሪዎች የነበሩትም በኋላ ላይ የርሳቸው ተማሪዎች ሆነዋል።
ለምሳሌ፦ ዝሁሪ አቡል አስወድ፣ ያሕያ ኢብኑ ሰዒድ፣ አቡ ሱሐይል እና ሌሎችም።
✔️ኢማሙ ሙሐመድ
✔️ኢማሙ ሻፊዒይ
✔️ዓብደልሏህ ኢብኑ ሙባረክ
✔️ለይስ ኢብኑ ሰዒድ
✔️ሱፍያነ ሠውሪ
✔️ኢብኑ ዑየይናህ
✔️ኢማሙል አውዛዒይና ሌሎችም ይገኙበታል።
👉ከስራወቻቸው መካከል፦
—------------------------
በአለም ላይ እጅጉን ታዋቂውና የተለያዩ ኮሌጆችና ዩኑቨርስቲዎች በከፍተኛ ትምህርት ኮርስነት የሚጠቀሙት ታዋቂው መጽሐፋቸው "ሙወጦእ" ነው።
ኢማሙ ማሊክ እለተ እሁድ ታመው በ84 ወይም በ86 ወይም በ87 ወይም በ90 አመታቸው፣ በ11ኛው ወይም በ14ኛው ረቢየል አወል በ179 ዓ.ሂ ከዚህች አለም በሞት ተለዩ።
በመዲና በጀነቱል ባቂዕ መቃብር ተቀበሩ።
ረሒመሁልሏህ።
ያሕያ፣ ሙሐመድና ሐማድ የተባሉ የሶስት ልጆች አባት ናቸው።
ኢማሙ ማሊክ ሲሞቱ 3300 ያክል ዲናር ለልጆቻቸው አውርሰው ነው።
የማሊኪያ መዣብ በአሁኑ ሰአት በሰሜንና ምዕራባዊ አፍሪካ፣ በቱኒስ፣ በሞሮኮ፣ በግብጽና በአልጀሪያ ይገኛል።
||
👉ታላላቅ ዑለማዎች ስለርሳቸው የተናገሩት፦
—--------
#ለዘጠኝ አመታት ያክል የኢማሙ ማሊክ ተማሪ የነበሩት ኢማሙ ሻፊዒይ ማሊክን እንዲህ ሲሉ ይገልጿቸዋል፦
"ምሁራኖች ስማቸው ሲጠቀስ፣
ማሊክ ኮከቡ ናቸው።" (“when scholars are mentioned, Malik is the star.”)
#ያሕያ ኢብኑ ሙዓይን እንዲህ ይላሉ፦
"እርሱ (ኢማሙ ማሊክ) በሐዲሥ አሚረል ሙእሚኒን ነው።"
#ዓብዱራሕማን ኢብኑ መህዲ እንዲህ ይላሉ፦
"በዚህች ምድር ገጽታ ላይ በነብዩ ሐዲሥ ዘገባ ከማሊክ የበለጠ ታማኝ የለም።"
እንዲህም ብለዋል፦
"ሱፍያነ ሠውሪ የሐዲሥ ኢማም እንጂ የሱንና ኢማም አይደለም።
አውዛዒይ የሱንና ኢማም እንጂ የሐዲሥ ኢማም አይደለም።
ማሊክ ግን የሐዲሥም የሱንናም ኢማም ነው።"
#ኢማሙ አቡ ሐኒፋ እንዲህ ብለዋል፦
"ከኢማሙ ማሊክ የበለጠ ፈጣን የሚገባው፣ ትክክለኛ መላሽና መምሮ ወሳጅ አላየሁም።"
#ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፦
"የማን ሐዲሥ በልብ መያዝ (መሸምደድ) አለበት? ተብዬ ተጠየቅኩ።
እኔም የኢማሙ ማሊክ ስል መለስኩ።"
#ኢማሙል ቡኻሪ እንዲህ ይላሉ፦
"በጣም ታማኙ የዘጋቢዎች ሰንሰለት የቱ ነው? ተብየ ተጠየቅኩ፦
እኔም ከኢማሙ ማሊክ፣ ከዚያም ከናፊእ፣ ከዚያም ኢብኑ ዑመር ብዬ መለስኩ።"
✔️በዋና ዋቢነት፦
==========
#አቡ ኑዓይም፦ ሒልየቱል አውሊያእ: (6/345-392)
#አል-ዘሃቢ፦ ሲየር አላም አልኑበላእ: (7/382-437)
#ፉአድ አብዱል ባቂ፦ የሙወጦእ መግቢያ።
https://t.me/WATESiMU
Telegram: View @WATESiMU

Telegram: View @WATESiMU

فوائد : أبي لقمان فؤاد بن نغاش ስብና ካላማረ መልክ መልከ ጥፉ ነው
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
🔺ዑለማዎቻችንን እንተዋወቅ
#ክፍል1
~~~
👉አቡ ሐኒፋ፡ (80-150 ዓ.ሂ)
ሙሉ ስማቸው አቡ ሐኒፋ ኑዕማን ኢብን ሣቢት ኢብን ዙውጣ ኢብን መርዙባን (أبو حنيفة نعمان بن ثابت بن زوطا بن مرزبان‎) ይባላሉ።
በ80 ዓ.ሂ በአሁኗ ኢራቅ ውስጥ በምትገኘው በኩፋ ከተማ ተወለዱ።
ይህ ዘመን ኃያሉ የዑመያድ አስተዳዳሪ ዓብዱል መሊክ ኢብን መርዋን በስልጣን ላይ ያለበት ዘመን ነበር።
አባታቸው ሣቢት ኢብን ዙውጣ በአሁኗ አፍጋኒስታን ከምትገኘው የካቡል ከተማ አልባሳትና ቁሳቁሶችን በማምጣት የሚሰሩ ነጋደ ነበሩ።
የዘር ግንዳቸው ከፐርሽያ እንደሚመዘዝ ይነገራል።
አቡ ሐኒፋ በልጅነታቸው ከአባታቸው ጋር በመሆን በሐር ልብስ በመነገድ አሳልፈዋል።
አባታቸው ሣቢት ኢብን ዙውጣ አቡ ሐኒፋን ሲወልዱ የአርባ አመት ጎልማሳ ነበሩ።
በወጣትነት ጊዚያቸውም ወደ ዓረቢያ ሂጃዝ ክልል በመሄድ በመካና በመዲና በሚገኙ ታላላቅ ዓሊሞች ላይ ተምረዋል።
#ፊቂህን ከኢማሙ ሐማድ፣
#ሐዲሥን ከኢማሙ ሸዓቢ ተምረዋል።
ከኢማሙ ሐማድ ሁለት ሺህ ያክል ሐዲሦችን ይዘዋል።
#ከኢማም ጃዕፈር ኢብን ሙሐመድ ሷዲቅ፣
#ከአዲ ኢብን ሣቢት፣
#ከመንሱር ኢብን ዑመርና ከሌሎችም ታላላቅ ዓሊሞች ላይ ተምረዋል።
👉አቡ ሐኒፋ የተወለዱት ነብያችን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከሞቱ ከ67 አመታት በኋላ ነበር።
በህይወታቸው እያሉ የነብዩን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሶሐቦች በህይወት ሳሉ አግኝተዋል።
ከነርሱም ሐዲሥ አስተላልፈዋል።
በህይወት ያገኟቸውን የሶሐቦች ብዛት በተመለከተ የተለያዩ ዓሊሞች የተለያዩ ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።
ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር ስምንት ብቻ ናቸው ሲሉ፣ የ"አል-ኸይራት አል-ሒሳን" ኪታብ ደራሲ ደግሞ 60 ሶሐቦች ናቸው ብለዋል።
ሐፊዝ አልሚዚ ደግሞ ሰባ ሁለት ናቸው ሲሉ ኢማም ሳሒብ ሃያ ስድስት ናቸው ብለዋል።
👉ከነዚህም ውስጥ የነብዩ አገልጋይና ተንከባካቢ የነበረው
#አነስ ኢብኑ ማሊክ፣
#ጃቢር ኢብን ዓብደላህ፣
#ሰህል ኢብኑ ሰዒድ፣
#አቡ ጡፈይል አሚር ኢብኑ ዋሲላህና ሌሎችም ሶሐቦች ይገኙበታል።
አቡ ጡፈይል አሚር ኢብኑ ዋሲላህ የሞተው አቡ ሐኒፋ የሃያ አመት ታዳጊ ሳሉ ነበር።
👉ከተማሪዎቻቸው መካከል፦
—---------------—
#ታዋቂው ኢማም አቡ ዩሱፍ፣
#ዓብደላህ ኢብኑ ሙባረክ፣
#ሐማድ ኢብን አቡ ሐኒፋ፣
#ዩኑስ ኢብኑ ኢስሐቅ፣
#አቡበክር ኢብኑ አያህ፣
#ዑበይዱልሏህ ኢብኑ ሙሳ፣
#ሙጚራ ኢብኑ ኢቅሳምና ሌሎችም ይገኙበታል።
👉ከስራወቻቸው መካከል፦
—------------------------
በሁለቱ ተማሪወቻቸው በአቡ ዩሱፍና በሙሐመድ አልሸይባኒ የተዘገበው ሰባ ሺህ ሐዲሦችን የያዘው
👉"ኪታቡል አሰር" አንዱና ዋነኛው ነው።
👉"ፊቂሁል አክበር": ሙስነድ ኢማሙል አዕዞም፣
👉"ዓሊም ወል ሙተዓሊም"፣
👉"ኪታቡል ረድ ዓለል ቀደሪያህ"ና ሌሎችም ይገኙበታል።
አቡ ሐኒፋ ከአራቱ ታላላቅ የፊቂህ አኢማዎች ውስጥ አንዱ ናቸው።
የሐነፍያ የፊቂህ ትምህርት በርሳቸው መዝሃብ ስም የተቋቋመ ነው።
አቡ ሐኒፋ በብዙዎች ዘንድ ኢማሙል አዕዞም (ታላቁ ኢማም) {The Great Imam)፣
ሲራጁል አኢማ (የአኢማዎች መብራት) (The Lamp of Imams) በመባል ይታወቃሉ።
"አቡ ሐኒፋ" የኩንያ ስማቸው ነው።
ተማሪያቸው አቡ ዩሱፍ በሃሩን ራሺድ የኺላፋ ዘመን ጊዜ ቃዲ ሆኖ ተሹሟል።
.
👉አቡ ሐኒፋ ከመሞታቸው አራት አመታት በፊት፡
አል-መንሱር የተባለ የአባሲዶች ገዥ አቡ ሐኒፋን በአስተዳደሩ ስር የቃዲዎች ቃዲ አድርጎ መሾም ፈለገ።
እርሳቸው ራሳቸውን ከማስተናነስ አንጻር ለአል-መንሱር እንዲህ አሉት፦
"እኔ ለዚህ ቦታ አልመጥንም!!"
አል-መንሱርም አቡ ሐኒፋን "ዋሽተሃል!" ብሎ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አደረገ።
እርሳቸውም እንዲህ አሉት፦
"ዋሽተሃል ካልክ፡ የኔ ንግግር እጥፍ እውነት ነበር።
ምክንያቱም እንደት አንተ ውሸታምን ቃዲ አድርገህ ትሾማለህ?"
ለዚህ ቦታ አልመጥንም ማለቴ አይጋጭም አሉ።
ከዚያም ይበልጥ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደረጉ።
በእስር ቤት ውስጥም ብዙ እንግልትና ስቃይ ደረሰባቸው።
ብዙም ሳይቆዩ ከአራት አመታት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት እዚያው እስር ቤት ውስጥ በ150 ዓ.ሂ በሰባ አመታቸው ህይወታቸው አለፈ።
በቀብር ስነ ስርአታቸው እለትም ከሃምሳ ሺህ በላይ የሚያክል ህዝብ ተገኝቷል።
ታላቅ ታብዒይ ናቸው።
አላህ ይማራቸው።
ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃቸው።
"በፊቂህ ትምህርታቸው ውስጥ ከቁርአንና ከሐዲሥ ውጭ ተቃርኖ የተገኘ ሃሳብ ካለ፣
በዚያ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የርሳቸውን እይታ ትተን ቁርአንና ሐዲሥ ያለውን እንድንከተል አዘዋል።"
https://t.me/WATESiMU
Telegram: View @WATESiMU

Telegram: View @WATESiMU

فوائد : أبي لقمان فؤاد بن نغاش ስብና ካላማረ መልክ መልከ ጥፉ ነው
Send as a message
Share on my page
Share in the group