Translation is not possible.
ልብህ በዱንያ ጭንቀት ሲወጠር፣ የወንጀልህ ብዛት ተስፋ ሲያስቆርጥህ፣ ወይንም የብቸኝነት ስሜት ሊውጥህ ሲደርስ...
ይህንን አንድ ነገር ብቻ አስታውስ፦
የፈጠረህ ጌታ ከአንተ ሩቅ አይደለም። በቁርኣኑ እንዲህ ይላልና፦
"وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ"
«እኛም ከደም ስሩ ይልቅ ወደ እርሱ ይበልጥ ቅርብ ነን።»
[ቃፍ:16]
አስበው! ከአንገትህ የደም ስር የቀረበ ጌታ አለህ። ጩኸትህን ይሰማል። የተሰበረ ልብህን ያያል። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆነህ የምታነባውን እንባህን ያውቃል።
ስለዚህ... ቃላትን ማሳመር አይጠበቅብህም። በቃ በሱጁድህ ላይ ግንባርህን አስቀምጥና በራስህ ቋንቋ እንዲህ በለው፦
«ያ ረብ! እርዳኝ።»🤲
«ጌታዬ ሆይ! ደክሜያለሁ፣ አንተ አበርታኝ።»
«ሸክሜን አቅልልኝ።»
እርሱ ምላሽ ሰጪ ነው፤ የጠየቁትን አይመልስም። እዝነቱ ከቁጣው ይቀድማልና።
አላህ የተሰበረውን ልባችንን ይጠግንልን። ጭንቀታችንን በሙሉ ያስወግድልን። ወደ እርሱም በንጹሕ ተውበት ይመልሰን።
Send as a message
Share on my page
Share in the group