UMMA TOKEN INVESTOR

About me

አለሁ በበረካው!

Translation is not possible.

« ምን ያወጉ ነበር? »

ሌት ተቀን በሒክማ ወደ አላህ ሲጣሩ

ከእስትንፋሱ የወጣው ምን አለ « አየሩ »?

አንጀታቸው ታጥፎ ድካማቸው ሲያይ

ርቧቸው ያሰሩት ምን አለ ያ « ድንጋይ »?

መንገዱን ለመዝጋት ሰርክ የሚጣሉ

ሊጎዱት ሲታጩ « እሾኾች » ምን አሉ?

ወዳጃቸው አጥተው በሀዘን ሲዋጡ

« እንባዎች » ምን አሉ ’ካይናቸው ሲወጡ?

መዓዛው የለመደው የኹጥባው « ሚንበሩ »

ምን ተሰምቶት ይሆን ሲርቀው ኸበሩ?

ናፍቆት ፍቅሩን ይዛ ክብር የታደለች

ሽሽግ ያረገችው « መዲና » ምን አለች?

ለፍቅሩ ሊሰዋ ሸሂዱ ሲቀርባት

« መደቧ » ምን አለች አሊ ሲያርፍባት?

ጧኢፍ የነበረ « ድንጋይ ዱላ » ሁሉ

ምን ተሰምቶት ይሆን ሲያርፍ ከአካሉ?

በድር ላይ በዱዓ አላህ ሲማፀኑ

ምንድን ተባባሉ « ንፋስ እና ቀኑ »?

ከፍ ሊሉ

ዝቅ ሲሉ

በሩኩዕ ጎንብሰው ሱጁድ ላይ ሲደርሱ

ትንፋሹ የደረሰው

እንባው የዳበሰው

ገላው ለሸፈነው

ምን ብሎ አወጋው ያ « መሬት ለልብሱ »?

በገደል በሜዳው ከጋጣው የዋሉ

በእሱ የተጠበቁ « ፍየሎች » ምን አሉ?

ሲርበው ሲጠማው ሲታጠፍ አንጀቱ

ባዶ ሆዱን ሲያድር ምንድን አለ « ቤቱ »?

ገላው ሰንበር ስሎ ሲታይ ምልክቱ

ጎኑ ምቾት ሲያጣ ምን አለ « ውበቱ »?

ለፍቅር ናፍቆቱ ለሀዘን ብሶቱ

ቃል እየመረጠ ባለ አንደበቱ

በድርሳን አስፍሮ የውስጡን ሲያሰማ

ትዝታ ያለበት

ቃል የሌለው ግዑዝ አንዴም አልተሰማ።

ግና…

እንዴት ነበር ’ሚሆን ቃል ቢያውቁ ግዑዛን

ምን ያወጉ ነበር ስለዛ የሰው ሚዛን?

ብቻግን…

ውስጡን ላልገለጠ

ቃልም ላልመረጠ

ፍቅሩን ላሰፈረ

በመራቅ ላፈረ

ለሁሉም እንዲሆን ሁሌም ባ’ለም ደጃፍ

ሁሉም እንዲግባባ እንዲህ ተብሎ ይፃፍ!

«ሙሀመድ ትልቁ፣ የፍጥረታት እንቁ

ታውቀው አይሰለቹ፣ ተገልፀው አያልቁ።»

[አብዱልሀኪም ሰፋ ]

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰውረኝ ሸሽገኝ ከሀላልህ ማጀት

ሀራም ተመግቦ እንዳይቀር የኔ አንጀት።

[አብዱልሀኪም ሰፋ]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » የሚሉት ገንዘብ ስለቸገራቸው ብቻ አይደለም። የሚጠቃቀሙበትን ነገር ወጪ መሸፈን ስላቃታቸው ብቻ አይደለም። በእርግጥ ዱንያ ልጋጋም ነች አስቀይማቸው ሊሆን ይችላል። ነገርን ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ገንዘብን ፍለጋ ብቻ አይደለም።

ሰዎች ሰውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማስተካከል « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

አብሽሩ፣ አይዟችሁ የሚላቸውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ፈተናዎቻቸው በዝተው መቋቋም ተስኗቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

እራስን ስለማጥፋት እያሰቡ ከዚህ ሀሳብ እንዲላቀቁ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

አኼራቸው አስጨንቋቸው፣ ወንጀላቸው አሳስቧቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያስገድዳቸው ነገር ዙርያቸውን ከቧቸው ተስፋ እንዳይቆርጡ ሲሉ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምክንያቶች ይኖራቸዋል። ዱዓ’ን ለገንዘብ ብቻ አትስጡ። የገንዘብ ችግር አንድ እራሱን የቻለ ችግር እንጂ ሁሉንም የሚያጠቃልል አይደለም። ገንዘብ የማይፈታው ስንትና ስንት መዓት የልብ ጉዳይ አለ መሰላችሁ።

ማንኛውም ሰው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲላችሁ Materialistic want/ቁሳዊ ፍላጎት ብቻ እየሻ ነው ብላችሁ አትደምድሙ። ሁሉንም የ« ዱዓ አድርጉልኝ! » አደራዎች ገንዘብ ተኮር ብቻ አድርጎ ማሰብ በራሱ ውስጣዊ የቁስ ባርነትን ማመላከቻ ነው።

ይሄኔ ስንቱ በልቡ ጉዳዩን ይዞ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ስላለን ቁስ ለመመፅወት ተጣድፈን አሳዝነነው ይሆን? ግዴላችሁም አስፍተን ነገሮችን ለመረዳት እንሞክር። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል።

(አብዱልሀኪም ሰፋ)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እስቲ ፈገግ ልጆቼ… አላህ ዘንድ የተሻለን የከጀለ የዱንያው ውድመት አይበግረውም!

አው… እስቲ አሳዯቸው ለአላህ ብለው ሲታገሉ መረበሽ እንደሌለ ይዩማ!

እስቲ ከፍ… እጃችሁን ልጆቼ… በአላህ አንደተመካን ያልገባቸው በዳዮች ሊሰብሩን እንደማይቻላቸው ይወቁማ!

ጎበዝ… ውዶቼ… ካጣነው የበለጠ አላህ ዘንድ ተስፋ የምናደርገው ይገዝፋል በሏቸው!

እስቲ አው…ለአንዳንድ ወንድሞቻችን ከምትሳሱለት ዱንያ የፈራረሰው ቤታችን ክብር አለው እንበላቸውማ!

አው…እኛም የአላህ ነን፣ ወደ አላህም ተመላሾች በመሆናችን ደስተኛ እንሆናለን በሏቸውማ!

እስቲ ፈገግ ልጆቼ… እጃችሁን ከፍ… ዝቅ ብለው የተዋረዱ ወንድሞቻችን እኛን አይተው ክብራቸው ትዝ ካላቸው እንኳ… እስቲ ፈገግ!

አው… አላህ ዘንድ የተሻለን የከጀለ የዱንያ ውድመት አይበግረውም!

አልሀምዱሊላህ! አው…እንደሱ… ሁሉም እንደሆነ ታሪክ መዝግቧል። በሉ አሁን ከዚህ በፈገግታ እንውጣ!

[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ስቃዬን የሰማ መበደሌን ያየ

ጨቋኜ እንዳይከፋው አለፈ እንዳላየ

ጎኔን ሰው ሲርበው ጠላቴ እያደባ

እኔ አውቅልህ አለኝ ደም እንባ እያስነባ።

የሚያርፍብኝ በትር ሊሰብረኝ መች ቻለ

ብቸኝነቱ ነው ውስጤን ያቆሰለ

ዙርያዬ ቢከበብ በአድማቂና አጃቢ

ካለ ወንድም አይሆን ወንድም ስጠኝ ረቢ።

ያ ወዱድ

ያ ወዱድ!

ትላንት ያሳደግኋት ያቺ ትንሽ ግልገል

አንዴ ብትረግጠኝ ተሰበርኹ እንደ ገል

እንኳንስ የሩቁ የቅርቤም አልሆነኝ

እኔ አቅም የለኝም ጌታዬ አንተው ሁነኝ።

[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group