Translation is not possible.

ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » የሚሉት ገንዘብ ስለቸገራቸው ብቻ አይደለም። የሚጠቃቀሙበትን ነገር ወጪ መሸፈን ስላቃታቸው ብቻ አይደለም። በእርግጥ ዱንያ ልጋጋም ነች አስቀይማቸው ሊሆን ይችላል። ነገርን ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ገንዘብን ፍለጋ ብቻ አይደለም።

ሰዎች ሰውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማስተካከል « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

አብሽሩ፣ አይዟችሁ የሚላቸውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ፈተናዎቻቸው በዝተው መቋቋም ተስኗቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

እራስን ስለማጥፋት እያሰቡ ከዚህ ሀሳብ እንዲላቀቁ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

አኼራቸው አስጨንቋቸው፣ ወንጀላቸው አሳስቧቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያስገድዳቸው ነገር ዙርያቸውን ከቧቸው ተስፋ እንዳይቆርጡ ሲሉ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ።

ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምክንያቶች ይኖራቸዋል። ዱዓ’ን ለገንዘብ ብቻ አትስጡ። የገንዘብ ችግር አንድ እራሱን የቻለ ችግር እንጂ ሁሉንም የሚያጠቃልል አይደለም። ገንዘብ የማይፈታው ስንትና ስንት መዓት የልብ ጉዳይ አለ መሰላችሁ።

ማንኛውም ሰው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲላችሁ Materialistic want/ቁሳዊ ፍላጎት ብቻ እየሻ ነው ብላችሁ አትደምድሙ። ሁሉንም የ« ዱዓ አድርጉልኝ! » አደራዎች ገንዘብ ተኮር ብቻ አድርጎ ማሰብ በራሱ ውስጣዊ የቁስ ባርነትን ማመላከቻ ነው።

ይሄኔ ስንቱ በልቡ ጉዳዩን ይዞ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ስላለን ቁስ ለመመፅወት ተጣድፈን አሳዝነነው ይሆን? ግዴላችሁም አስፍተን ነገሮችን ለመረዳት እንሞክር። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል።

(አብዱልሀኪም ሰፋ)

Send as a message
Share on my page
Share in the group