UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Translation is not possible.

ይቅርብኝ በእውነቱ

በቂያማ ለታ ካልሆነልኝ ሁጃ፤

በላን ካልመለሰ ካላወጣ ሀጃ።

ምንስ ሊያደርግልኝ

ስደነፋ ብውል እንዲህ ነኝ እያልኩኝ ፣

ዘሬን አስበልጬ ሸሪአን ከናድኩኝ፣

ከተውሂድ ቃል በልጦ ዘሬ አንድ ካረገኝ።

ከመተዋቂያ ውጭ ሌላ ጥቅም ካለው፣

የአላህን ተአምር ካልሆነ ሚያሳየው፣

እኔ ዘር የለኝም ማንነቴ #ሰው_ነው!!

አዎን!

ሠውን ለመግደያ ለማቅሪያ በከንቱ፣

ወገንን  ለማፈናቀል ከሀብት ንብረቱ፣

ይህማ ከሆነ የዘር ጥቃሞቱ፣

እኔ ዘር የለኝም #ይቅርብኝ_በእውነቱ!!

✍️አብደልከሪም ሁሴን

(ለዘረኞች አድርሱልኝ)

https://t.me/MEFATIH_ALKHYER

Telegram: Contact @MEFATIH_ALKHYER

Telegram: Contact @MEFATIH_ALKHYER

→ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፅሁፎች የሚገኝበት ቻናል ነው። ይ ቀ ላ ቀ ሉ ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓ https://t.me/MEFATIH_ALKHYER
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የኡለሞች ደረጃ ምጥቀት፤ በታላቁ ኢማም አል-ኣጁሪ አንደበት!

==========

ምን ብትበላሽ፤ ምን ያህል ብትጠም ነው ነፍስህ፣

በነብያት ወራሽ በምድር ኮከብ ላይ ሽጉጥ ያስመዘዘህ።

==========

በ360 ዓ.ሂ የሞቱት ታላቁ የመካ ኣሊም ኢማሙ አል-ኣጁሪ የኡለማዎችን ደረጃ ክብር ምጥቀት ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ

«ስሞቹ ከጉድለት የጠሩት ጌታ አላህ ከፍጥረታቱ የወደዳቸውን መርጦ ለኢማን መርቷቸዋል። ከተቀሩት አማኞች ደግሞ (ኡለማዎችን) መርጦ ችሮታውን ውሎላቸዋል። መፀሀፍንና ጥበብን አሳወቃቸው የዲን ሊቃውንትም አደረጋቸው።(የመፅሀፍቱን) ተእዊልም(ፍቺም) አስተማራቸው። በሁሉም ዘመንና ግዜ ከተቀሩት አማኞች በላጮች አደረጋቸው። በእውቀት አነሳቸው በትእግስት አስዋባቸው። በነሱ (በኡለማዎች) ሀላል ከሀራም ሀቅ ከባጢል ጠቃሚ ከጎጂ ጥሩ ከመጥፎ ተለይቶ ይታወቃል።

የኡለሞች ደረጃ ትልቅ ነው (ከተጎዱ) አደጋቸው ከባድ ነው።(ኡለሞችኮ) የነብያት ወራሾች የወልዮች አይን መርጊያ ናቸው። ለነሱ በባህር ውስጥ ያለ አሳ ሳይቀር ማህራታን ይማፀንላቸዋል መላእክ ክንፋቸውን ይዘረጉላቸዋል።ኡለማዎች የቅያማ እለት ከነብያቶች ቀጥለው ያማልዳሉ።

ከነሱ ጋር መቀማመጥ ጥበብን ያወርሳል። በስራቸው ዝንጉ ይገሰፃል።

ኡለሞች አላህን ቀን ከሌት ከሚገዛ ኣቢድ ይበልጣሉ ዱንያን ትቶ ወደ አኺራ ከገባ ዛሂድ ደረጃቸው በጣም ከፍ ያለ ነው። የነሱ መኖር ምርኮ ሞታቸው ደግሞ ችግር አደጋ ነው። በነሱ ዝንጉ ይገሰፃል አላዋቂ ይማራል...በውብ ምክራቸው አምልኮን የሚያጓድል ይገሰፃል ሁሉም ፍጥረት ወደ ስራቸው ገጃይ ነው እውነታው ንግግራቸውን የተጣረሰ ዛቻ አለበት። በፍጥረታቶች ላይ እነሱን መታዘዝ ግዴታ ነው እነሱን ማመፅ ወንጀል ነው። እነሱን ይታዘዘ ይመራል እነሱን ያመፀ ከቀጥተኛው መንገድ ያፈነግጣል....»[አኽላቁ አል-ኡለማእ ሊኢማሚል ኣጁሪ]

✍️አብዱልከሪም ሁሴን

በድጋሜ የተለቀቀ

https://t.me/MEFATIH_ALKHYER

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንደምጠየቅበት ባልፈራ ብዙ መፃፍ እችል ነበር!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ችግሩ የትዳር አጋራችንን ስንመርጥ ምርጫችንን አለማስተካከላችን እንጂ ትዳር የንትርክም የጭቅጭቅም አልያም አንዳንዶች እንደሚሉት እስር ቤት ሆኖ አይደለም። ይልቁንም ምርጫውን ላስተካከለ የስኬት ቁልፋ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ አብዱልዋሀብ ትክክለኛው አቂዳ

✍ክፍል 1

~~

ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ አብዱልዋሀብ ለተውሂድ የታገሉ ብዙ መስዋእትነትን የከፈሉ ታላቅ ሰው መሆናቸውን ሱናን ያሸተተ ወደ ታሪካቸው መለስ ብሎ የተመለከተ ሁላ የሚረዳው እውነታ ነው።

ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ አብዱልዋሀብ በተውሂድ ዙርያ የፃፏቸው መፅሀፍቶች ለስንቱ ቅናቻ ምክንያት ለብዙዎች ፅናት መሰረት የሆኑ ዘመን ተሻጋሪም ጭምር ናቸው።ስለ ሸይኹ ታላቅነት ምንነት የሸይኹ ዳእዋ መሰረት ብዙ መፅሀፍቶች ከብዙ ከሳቸው በኋላ ከመጡ ትላልቅ የዲን ሊቃውንቶች ባለ ብዙ ጥራዝ ባለብዙ ገፆች መፅፍቶች ተፅፈዋል። በተቃራኒው በግዜያችን እንዲሁም በግዜያቸውም ጭምር በእሳቸው ላይ ብዙ ቅጥፈቶች መሰረተ ቢስ ልብወለዶች ሲነዙ ሲፈበረኩ ቆይተዋል። ሸይኹም በተቻላቸው አቅም ያሉበትን የያዙት እውነተኛ አቂዳ ለግለሰብ ለጀመአም በድምፅም በደብዳቤ ፅሁፍም ገልፀዋል። አቂዳቸውን ከገለፁበት ደብዳቤዎቻቸው ውስጥ ለቀሲም ሰዎች ስለ አቂዳቸው በተጠየቁ ሰአት የፃፉትን ደብዳቤ በተወሰነ መልኩ እንመልከት። ምንምንኳ ሸይኹ የፃፉት ደብዳቤ በርዕስ የተከፉፈለ ባይሆንም ለአንባንቢ ውስብስብና አሰልቺ እንዳይሆን በመስጋት ርእሶችን አብጅቼላቸዋለሁ። በተጨማሪም ሸይኹ የተጠቀሷቸውን ቡድኖች ምንነት ከተለያዩ የአቂዳ ድርሳናት ማብራሪያ በመቀነጫጨብ በአጭሩ ለማብራራት ሞክሬያለሁ።

ከሁሉ በፊት ግን ስለ ሸይኹም ሆነ ስለተቀሩት የዲን ሊቃውንቶች አሉባልታን በማመን ጥላቻን ከማራመዳችን በፊት ስለሸይኹ ማንነት ስለተፃፉ እውነተኛና እውነታውን ስለሚያስረዱ ኪታቦች ራሳቸውም ሸይኹ ስለፃፏቸው ኪታቦች መለስ ብለን ሀቁን ማጥናታችን ከብዙ ይቅር ሊባሉ ከማይችሉ ስህተቶች እንድናለን። ይህ ወንድማዊ ምክሬ ነው በተረፈ መልካም ንባብ።

➥*ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ አብዱልዋሀብ በአላህ ስሞችና መገለጫዎች ያላቸው አቋም

~

ሸይኹ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ“ አላህ (ስራዬን በመመዝገብ) የተጣዱ መላእኮችና እናንተም ምስክሮቼ ናችሁ። እኔ የምትድነዋ ቡድን አህለልሱና ወልጀማአዎች ከአላህ ከመልአኮቹ ከመፅሀፍቱ ከመልእክተኞቹ ከሞት በኋላ መቀስቀስ እንዳለ መልካምም ይሁን መጥፎ ከአላህ ውሳኔዎች የሚያምኑትን ሁሉ አምናለሁ። በአላህ ከማመን ውስጥ አላህ በመፅሀፍቱ ውስጥና በመልእተኛው ﷺ አንደበት ራሱን በገለፀባቸው መገለጫዎች ሁሉ ያለምንም ማራቆት ማዛባት ማመሳሰልና ዝርዝር ሁኔታቸውን ያለማስቀመጥ አምናለሁ። ይልቁንስ እሱን የሚመስል ፍፁም እንደሌለ እርሱም ሰሚና ተመልካች እንደሆነ አምናለሁ። አላህ ራሱን የገለፀባቸውን ውድቅ አላደርግም ቃላቶችን ከመቀመጫቸው አላጣምም ከአናቅፆቹና ከስያሜዎቹ አንድንም አላዛባም።(ለባህርያቱም) ዝርዝር ሁኔታን አላስቀምጥም። የፈጣሪን መገለጫ ባህሪ ከፍጡር መገለጫ ባህርያቶች ጋር አላመሳስልም። ምክንያቱም አላህ አምሳያ ብጤና ባላንጣ የለውም በፍጥረታቱም አይለካም። እሱ አላህ ስለራሱም ይሁን ስሌሎች ይበልጥ አዋቂ እውነትን ምርጥን ንግግር ተናጋሪ ነው።

አላህ (ከቀጥተኛው መንገድ) የተቃረኑ የሆኑ የተክዪፍና የተምሲል ሰዎች እሱን ከገለፁበት ነገር እንደዚሁም ውድቅ አድራጊያን የተእጢልና የተህሪፍ ሰዎች ከሱ ውድቅ ከሚያደርጉት ነገር ሁሉ ራሱን አጠራ። እንዲህ አለ አላህ

سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ ١٨٠۞وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٨١۞وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ١٨٢

ጌታህ-የአሸናፊነት ጌታ-ከሚገልፁት ሁሉ ጥራት የተገባው ነው! ۞በመልእክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን۞ ምስጋናም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን۞[አስ-ሷፍፋት: 180-182]»

ይቀጥላል...

✍️Abdulkerim husen (Abu suleyman

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group