Translation is not possible.

የኡለሞች ደረጃ ምጥቀት፤ በታላቁ ኢማም አል-ኣጁሪ አንደበት!

==========

ምን ብትበላሽ፤ ምን ያህል ብትጠም ነው ነፍስህ፣

በነብያት ወራሽ በምድር ኮከብ ላይ ሽጉጥ ያስመዘዘህ።

==========

በ360 ዓ.ሂ የሞቱት ታላቁ የመካ ኣሊም ኢማሙ አል-ኣጁሪ የኡለማዎችን ደረጃ ክብር ምጥቀት ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ

«ስሞቹ ከጉድለት የጠሩት ጌታ አላህ ከፍጥረታቱ የወደዳቸውን መርጦ ለኢማን መርቷቸዋል። ከተቀሩት አማኞች ደግሞ (ኡለማዎችን) መርጦ ችሮታውን ውሎላቸዋል። መፀሀፍንና ጥበብን አሳወቃቸው የዲን ሊቃውንትም አደረጋቸው።(የመፅሀፍቱን) ተእዊልም(ፍቺም) አስተማራቸው። በሁሉም ዘመንና ግዜ ከተቀሩት አማኞች በላጮች አደረጋቸው። በእውቀት አነሳቸው በትእግስት አስዋባቸው። በነሱ (በኡለማዎች) ሀላል ከሀራም ሀቅ ከባጢል ጠቃሚ ከጎጂ ጥሩ ከመጥፎ ተለይቶ ይታወቃል።

የኡለሞች ደረጃ ትልቅ ነው (ከተጎዱ) አደጋቸው ከባድ ነው።(ኡለሞችኮ) የነብያት ወራሾች የወልዮች አይን መርጊያ ናቸው። ለነሱ በባህር ውስጥ ያለ አሳ ሳይቀር ማህራታን ይማፀንላቸዋል መላእክ ክንፋቸውን ይዘረጉላቸዋል።ኡለማዎች የቅያማ እለት ከነብያቶች ቀጥለው ያማልዳሉ።

ከነሱ ጋር መቀማመጥ ጥበብን ያወርሳል። በስራቸው ዝንጉ ይገሰፃል።

ኡለሞች አላህን ቀን ከሌት ከሚገዛ ኣቢድ ይበልጣሉ ዱንያን ትቶ ወደ አኺራ ከገባ ዛሂድ ደረጃቸው በጣም ከፍ ያለ ነው። የነሱ መኖር ምርኮ ሞታቸው ደግሞ ችግር አደጋ ነው። በነሱ ዝንጉ ይገሰፃል አላዋቂ ይማራል...በውብ ምክራቸው አምልኮን የሚያጓድል ይገሰፃል ሁሉም ፍጥረት ወደ ስራቸው ገጃይ ነው እውነታው ንግግራቸውን የተጣረሰ ዛቻ አለበት። በፍጥረታቶች ላይ እነሱን መታዘዝ ግዴታ ነው እነሱን ማመፅ ወንጀል ነው። እነሱን ይታዘዘ ይመራል እነሱን ያመፀ ከቀጥተኛው መንገድ ያፈነግጣል....»[አኽላቁ አል-ኡለማእ ሊኢማሚል ኣጁሪ]

✍️አብዱልከሪም ሁሴን

በድጋሜ የተለቀቀ

https://t.me/MEFATIH_ALKHYER

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group