Elu Abubeker Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Elu Abubeker shared a
Translation is not possible.

የፌስቡክ መሥራች ማርክ ዙከርበርግ ስፖርት እሠራለሁ ሲል ጉልበቱ ላይ ስብራት አጋጥሞት የACL ቀዶ ጥገና ተደርጎለት በምታዩት መልኩ ይታያል።

አንዳንድ በሳይንስ ፊክሽን የተጠቁ ተማርንና አወቅን ብለው የሚያስቡ ወንድምና እህቶች ዘመናዊው ሳይንስ በተለይም የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንሱ ዓለም ለሁሉም ነገር መልስ ያለው ይመስላቸዋል። እንዳውም አንዳንዶች በድፍረት ከተለዋዋጩ ሳይንሳቸው ጋር የተቃረነውን ኢስላማዊ አስተምህሮ ሲተቹ ይስተዋላል።

እስኪ! ከእናንተ በላይ ሳይንሰም የገባው፣ የገንዘብ አቅምም ያለው ማርክ ለአንድት ተራ ስብራት እንዲህ በበርካታ ኮተት ተጠጋግኖ ከሚቀመጥ፤ ቶሎ ወደነበረበት የሚመልሰው ሳይንሳዊ  አንድ የኤአይ ውጤት ፈልጉለት ኣ¡

እርሱ ከፌስቡክ ባሻገር ከ94 በላይ ካምፓኒዎች ባለቤት ነው። በተጨማሪም እንደ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም፣ ኦኩለስ፣ ሜሴንጀርና መሰል ዕውቅ አፖች ባለቤት ነው። ፌስቡክ ብቻውን ከ2.9 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚ አለው።

ከገንዘብ አንፃርም ካየነው እነዚህንና ሌሎችንም የያዘው ሜታ ካምፓኒው 804.49 ቢሊዮን ዶላር ነው። ከፈለግክ በብላክ አብዛውና በኢትዮጵያ ብር አስበው። ከ80 ትሪሊዮን ብር በላይ ይመጣል። ይህ ማለት በኢትዮጵያ የ2016 አመታዊ በጀት (801.6 ቢሊዮን ብር) ካየነው ለ100 አመት ይበቃታል። ለአንድ ክፍለ ዘመን ትውልድ በለው¡ የካምፓኒው ያለፈው አመት ትርፉ በ130.58% የጨመረ ነው።

ግን ምን ዋጋ አለው? ሌላ ከባድ አደጋ እንኳ ሳያጋጥመው በዚህች ቀላል የጉልበት ስብራት ይሄው በዚህ መልኩ ተጠግኖ ነው ያለው።

ልብ ያለው ሰው ከዚህ በቀላሉ ይማራል። እርሱ ልብ ካለው ስለ ሜታቨርስና መሰል ነገሮች ከማውራቱ በፊት ስለ እምነት አጥንቶ እስልምናን ቢቀበል ይበልጠዋል። የሳይንስ ምርኮኞችም አይደለም ሌላ ዝንብ እንኳ መፍጠር እንደማትችሉ አውቃችሁ ወደ ዓለማቱ ጌታ ወደ አላህ ተመለሱ። ሳይንስን አትማሩ አላልኩም። ተማሩና ለመልካም ነገር ተጠቀሙበት፤ ዲናችሁን ካድሙበት። ግን ሁሉን ነገር የሚያውቅ አድርጋችሁ እምነታችሁን በፍልስፍና አትቀይሩት። ያልገባችሁ ነገር ሁሉ መልስ የሌለው አይምሰላችሁ። እናንተ በሰዋዊው ቅንጣቢ እይታችሁ ያልደረሳችሁበት ነገር ሁሉ ከናካቴው የሌለ አይምሰላችሁ። ቆም ብላችሁ ዐቅላችሁን አሠሩት። ከተማራችሁትና ካወቃችሁት ሁሉም ነገር በእስልምና መልስ አለው። የእስልምና መልስ ደግሞ ፍጹም እርካታና ስክነት የተሞላበት ነው።

አል-ሐምዱ ሊላህ! አላህ ሙስሊሞች ስላደረገን፤ ሙስሊሞችም አድርጎ ይግ'ደለን። ማርክም የፕላትፎርሞችህን በተለይም በፈለስጢን ጉዳይ ሙስሊም ጠልነትህን አስወግደህ አላህ እስልምናን የሚወፍቅህ፣ በዚህችም ቅምሻ ወደ ቀልብህ የምትመለስበትና አቅምህን የምትፈትሽበት ሰበብ ያድርግልህ።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group