UMMA TOKEN INVESTOR

ترجمہ ممکن نہیں

✨የትኛው ይበልጥ ይደንቃቹሃል✨

1⃣ የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር?

2⃣ ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር?

3⃣ ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት?

4⃣ አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር?

5⃣ በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም መለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት?

         

              

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ترجمہ ممکن نہیں

የደሴው ኡስታዝ ሙስጦፋ ድንቅ እይታ

=================================

👇👇👇

⭕️-➢ ሰው ሁሉ ለኔ የገረመኝ አልገረመውም.. ❗️

⭕️====⭕️ ⭕️====⭕️

⭕️➢የአሜሪካው እውቅ የእግረኛ ስትራቴጂ ነዳፊ ጀኔራል በግልፅ በቀጥታ ተሳትፎ የጋዛውን የፅዮናዊቷን የእግረኛ ጦር አቅጣጫ እያሳዬ እየመራ እንደሆነ ታውቋል ። በአሁኑ ሰዓት ሰሜን ጋዛ የሐማስ ውስብስብ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በብዛት አለበት ተብሎ ስለሚታሰብ ከባህር ከሰማይ ከየብስ በተቀጣጣይ ቦንብና በተምዘግዛጊ ሚሳይሎች ምድጃ ሆናለች ።

----

⭕️➢ የሚገርመው የውስጥ ለውስጡ ውስብስብ መንገድ ብዙው አርማታ ስለሆነ አሜሪካ ISISን ከመውሲል ከተማ ስታስወጣ የተጠቀመችውን ከ10 -30 ሜትር ወደ ውስጥ የሚገባ መሳሪያ ኢስራኤልም እየተጠቀመች እንደሆነ አስታውቃለች ።

⭕️---------- ------ ------------⭕️

⭕️-➢ እኔ የገረመኝ ከዓለም 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የአረቦች ኩራት የተባለለት የግብፅ ጦር ስርዓትህን ያዝ ተብሎ ከአሜሪካ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያና የኢስራኤልን ዛቻ በመፍራት ስብስብ ብሏል ። በእውነቱ ታሪክን ከቃኘን የግብፅና የዩርዳኖስ እንድሁም የሶሪያ ጦር የፅዮናዊቷን ክንድ ቀምሷል ፤ በደንብ ቀምሷታል ። በዚህ ሰዓት ንቅንቅ ብትሉ ከተማችሁን ወደ ታሪክነት እለውጠዋለሁ ብላ ኢስራኤል የፎከረችው በግብፅ እንጂ ሌሎቹማ ደካሞች ናቸው ጮከውም አያስደነግጧትም ። የፓርላማ አባሎቹ እንደ አንቡላንስ ከመጮህ ውጭ መራመድ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ተገንዝቦ የግብፅ ህዝብ ኳሱን እያዬ ጋዛ በደማችን ነፃ እናወጣሻለን እያለ እየዘመረ ኳሱን አድምቆ ወደ ቤቱ የሚሔድ ደንታቢስና በሰላም መዝናናት የሚፈልግ ህዝብ እንደሆነ ሁሉም እውነተኛ ገፅታውን አሳይቷል ።

⭕️------------------⭕️

⭕️ - ➢የተውሒዷ አገር በኮንሰርት ዝግጅት የጋዛን ጉዳይ ውኃ ቸልሳበታለች።

" إنا لله إليه راجعون "

የተውሒዷ ምድር የዑለሞቹ አገር የጀግኖች መፍለቂያ እነ አቡ በክር እነ ዑመር እነ ሐምዛ እነ ዓሊይ እነኻሊድ እነሚቅዳድ እነ በራእ ኢብን ማሊክ እንድሁም ሌሎችም ሶሐብዮች የተወለዱባት ያደጉባት ተዋግተው አጥንታቸውን ከስክሰው ዳመቸውን አፍሰው ተውሒድን ያነገሱባት አገር ዓለምን በፍትህና በጀግንነት የመሩ የጀግኖች የብልሆች አገር በዚህ ደረጃ ሆና ማየት ይከብዳል።

هداهم الله تعالى وأصلحهم.

። ይህቺ አገር በሚገርም ሁኔታ በምእራባዊያን የእድገት ጉዞ በገንዘብና ፍላጎትን በማርካት በጣም ተፈተነች... ❗️

---

⭕️➢ ቆይ ያ የመንን ስትደበድብበት የነበረው ጀት ሁሉ የት ገባ ... ❓

እሺ መተኮስ የራሳቸው አካሔድ ነው ዝም ብለው አይማገዱም ጎናቸውን ጠብቀው ነው እንበል የነዳጅ ማዕቀብስ የለም... ❓

ሐማስንና የሐማስን መንሐጅ ሳይሆን አሁን የፊሊስጤም ህፃናት ህልም በሚመስል መልኩ እየተቃጠሉ እንደማገዶ እየነደዱ ነው ።

---------

⭕️-➢ በጣም የገረመኝ የሰሜን ኮሪያው ካፊሩና እብዱ መሪ ኪም ለሐማስ በመሳሪያ ረድተነዋል አሁንም እንረዳዋለን ። አሜሪካ ሆይ አንቺ ባስታጠቅሻት መሳሪያ ሳይጣኗ ልጅሽ የጋዛን ህፃናት እየጨፈጨፈች ለነፃነታቸው ለህሎናቸው ለመኖር ብለው የሚታገሉትን በመርዳታችን ቅር ይልሻልን ሲል መረር ያለ ንግግር አሰምቷል ። አጭሩን ገፋፍታችሁ ወደ ሌላ እርምጃ አትውሰዱን ። እናንተን ማነው የዓለም ፖሊስ ያደረጋችሁ .. ❓ የፈቀዳችሁለት ሊኖር የጠላችሁት ሊገደል አለምን ለናንተ ያስረከባችሁ ማነው.. ❓

ሲልም አስገራሚ ጥያቄ ጠይቋል...።

------

اللهم اضرب الظالمي بالظالمين.

------

⭕️➢የዩርዳኖሱ ሚኒስቲር እንባ እየተናነቀው የተናገረው ገረመኝ ...

ሁሉም ባለ ስልጣን እየጮኸ ያለው ከኋላ ያለውን የህዝብ ማዕበል ለማቀዝቀዝ እንጂ ውጤት ያለው እርምጃ ከየትኛውም አገር እንዳትጠብቁ ብቻ ታሪክ ይፍረድ አለ... አዎ الله ይፍረድ ... ❗️

⭕️====⭕️ ⭕️===⭕️

⭕️--➢ እውነትም ቱርክም ፎከረች ኔቶ ዋ ብሏታል ። ኢራንም ፎከረች የአሜሪካ የጦር መርከብ ተጠግቷታል እያየሁሽ ነውም ብሏታል ። ተደብቀሽ መሳሪያ ልትሰጪ ትችይ ይሆናል ። አንድት ሚሳል ብትተኩሺ ግን መፈጠርሽን እናስረግምሻለን... የአሜሪካው የባህር ኃይል መሪ...❗️❗️❗️

⭕️----------------- -----------------⭕️

⭕️--➢ ኢስራኤልና አሜሪካ ያስቀመጡት የፊሊስጤሞች ዓልማንያው ፕሬዝዳንት መህሙድ አባስ : " ሐማሶች ጋዛ ብትወድም ተረት ብትሆን ደንታቸው አይደለም ። ሐማሶች ህዝባቸውን ለቦንብ አጋልጠው እነሱ በአንቡላንስ ወደ ሲና ከስደተኞችጋ ሸሽተዋል. " ይላል... ። እነ ኤምሬት ሐማስን እየረገሙ ኢስራኢልን ይቅናሽ እያሉ ነው ።

---------------------- --------------------

⭕️--➢ ሩሲያ የተናገረችው የተጠና ንግግር በደንብ ያሳምናል።

"" መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ያሉት የአሜሪካ ወዳጆችና አሜሪካ ያለቀው አልቆ ሐማስን ፈንቅላችሁ ከፊሊስጤን ምድር አውጡ ተባብለው ተስማምተዋል...""

👇 👇 👇 👇 👇 👇

⭕️➢ የሊባኖሱ ሒዝቡላት, የየመኑ የሁቲዮችጦር, የዒራቁ የጀኔራል ሱለይማኒ 1 ሚሊዮን የሚሆን ጀይሸ ሸዕቢ ስልጡን ጦር , የዒራቁ ሒዝቡላት , የሙቅተዷ ሶድር ጀይሹል መህዲ ይህ ሁሉ የሸዓ ጦር ኢራን ያሰለጠነችው እስካፍንጫው የታጠቀ ጦር ነው ። ዝቅተኛ የሚባለው የየመኑ የሁትዮች ጦር ሰሞኑን በራሱ የጦር ኢንጅነሮቹ ድሮን ሰርተው በተሳካ መልኩ ሞክረዋል ። ሰዑድን በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላር አስፈስሰዋት በመጨረሻ የማይሆን ሆነ ደከመች በመጨረሻ ለድርድር ዝግጁ ሆነች ..... ❗️

------------------- ------------------

👇👇 👇👇 👇👇

➢ ሽዓ እንደዚህ እየተባበረ እየሰለጠነ ሌላው ሱኒ ነን ወሐብዮች ነን የሚሉት ለምን እንደሚተኙ እስራኤልጋ ለምን ተጥቢዕ" የድፕሎማሲ ፊርማ " እንደ ጀመሩ ሳስበው ይገርመኛለሰ። እንቆቅልሽም ይሆንብኛል ....። ኢራን በየቦታው እያሰለጠነች እየረዳች አቅሟን እያፈረጠመች ሌላው በስልጣን ጥማት እየተባላ በውስጡ የምእራቡ ቅጥረኞች ሲነዱት ስታይ ትደነቃለህ... ❗️

ዛሬ ላይ ከالله በኋላ ሩሱያና ቻይና ካልተቆጡልን እንደ ህፃን ማልቀስ ሆነ... እነሱም ሲቆጡ ጎናቸውን ጠብቀው ነው ።

⭕️--➢ አቤት ውድቀት... ❗️

የላጭን ልጅ ቅማል በላት አሉ..።

https://t.me/AbuNamuse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ترجمہ ممکن نہیں

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ترجمہ ممکن نہیں

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group