👉የሽርክ አይነቶች
1ኛ. ትልቁ ሽርክ፡-
ለአላህ ቢጤ በማድረግ ልክ እንደርሱ ማምለክ ሲሆን ይህ ከእስልምና
የሚያስወጣና መልካም ስራን በአጠቃላይ የሚያበላሽ ተግባር ነው፡፡ ይህን
ድርጊት ፈፃሚ በዚህ ሁኔታ ከሞተ ጀሀነም ውስጥ ዝንተ አለም ይዘወትራል፡፡
ሞቶ አያልቅለትም።
የትልቁ ሽርክ አይነቶች
ትልቁ ሽርክ አራት አይነት ነው፦
📚1 በልመና ማጋራት፡-
ልመና ከታላላቅ የአምልኮ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ እንዲያውም የአምልኮ ዋናው
ክፍል ነው፡፡
ነብዩ ( ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡
‹‹ዱዓዕ የዒባዳ ዋናው ነው››
አላህም እንዲህ ብሏል
ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺭَﺑُّﻜُﻢُ ﺍﺩْﻋُﻮﻧِﻲ ﺃَﺳْﺘَﺠِﺐْ ﻟَﻜُﻢْ ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ ﻋَﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩَﺗِﻲ ﺳَﻴَﺪْﺧُﻠُﻮﻥَ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ
ﺩَﺍﺧِﺮِﻳﻦَ
‹‹ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት
የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡››
(አል ጋፊር 6ዐ)
ዱዓእ አምልኮ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ከአላህ ሌላ ለሆነ ፍጡር ማድረጉ
ሽርክ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነብይን፣ መልአክን፣ ወልይን፣ ቀብርን፣ ድንጋይንና
ማንኛውንም ፍጡር የለመነ አጋሪ ከሃዲ ይሆናል፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፦
ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺪْﻉُ ﻣَﻊَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻟَﻬًﺎ ﺁﺧَﺮَ ﻟَﺎ ﺑُﺮْﻫَﺎﻥَ ﻟَﻪُ ﺑِﻪِ ﻓَﺈِﻧَّﻤَﺎ ﺣِﺴَﺎﺑُﻪُ ﻋِﻨﺪَ ﺭَﺑِّﻪِ ﺇِﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳُﻔْﻠِﺢُ
ﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮُﻭﻥَ
‹‹ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ
ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡››
(ሙእሙኑን 11)
ዱዓእ አምልኮ ስለመሆኑና ከአላህ ውጭ ለሆነ ማድረግ ሽርክ እንደሚሆን
ከማስረጃዎች ውስጥ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡
ﻓَﺈِﺫَﺍ ﺭَﻛِﺒُﻮﺍ ﻓِﻲ ﺍﻟْﻔُﻠْﻚِ ﺩَﻋَﻮُﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻣُﺨْﻠِﺼِﻴﻦَ ﻟَﻪُ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﻧَﺠَّﺎﻫُﻢْ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟْﺒَﺮِّ ﺇِﺫَﺍ ﻫُﻢْ
ﻳُﺸْﺮِﻛُﻮﻥَ
‹‹በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ
ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ
(ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡››
(አንከቡት 65)
እነዚህ አጋሪዎች ሲመቻቸው እንደሚያጋሩና ሲቸግራቸውና ሲጠባቸው ግን
ዒባዳን ለአላህ ብቻ እንደሚያደርጉ ተናገረ፡፡ ታዲያ ሁሌ በድሎትም በችግርም
በአላህ ላይ የሚያጋራ እንዴት ሊሆን ነው? አላህ ይጠብቀን፡፡
📚2 በፍላጐትና የኒያ ማጋራት፡-
ማለት በሚሰራው ስራ ዱንያን ወይም ልክ እንደሙናፊቆች ሙሉ በሙሉ
ለይዩልኝና ይስሙልኝ ብቻ መስራትና የአላህን ፊትና የአኺራን ሀገር አለመፈለግ፡፡
ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፦
ﻣَﻦ ﻛَﺎﻥَ ﻳُﺮِﻳﺪُ ﺍﻟْﺤَﻴَﺎﺓَ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﻭَﺯِﻳﻨَﺘَﻬَﺎ ﻧُﻮَﻑِّ ﺇِﻟَﻴْﻬِﻢْ ﺃَﻋْﻤَﺎﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻭَﻫُﻢْ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻟَﺎ ﻳُﺒْﺨَﺴُﻮﻥَ
ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻟَﻴْﺲَ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺂﺧِﺮَﺓِ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺭُ ﻭَﺣَﺒِﻂَ ﻣَﺎ ﺻَﻨَﻌُﻮﺍ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻭَﺑَﺎﻃِﻞٌ ﻣَّﺎ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ
ﻳَﻌْﻤَﻠُﻮﻥَ
‹‹ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን
(ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ
ምንም አይጎድልባቸውም፡፡ እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት
በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ
ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡››
(ሁድ 15-16)
ይህ የሽርክ አይነት ስውር የሆነና አደገኝነቱ የከፋ ነው፡፡
📚3 በትዕዛዝ ማጋራት፡-
አንድ ሰውን አላህ የፈቀደውን ሲከለክልና አላህ የከለከለውን ሲፈቅድ መታዘዝ
እንዲሁም ሰዎች ሀላልና ሀራም ማድረግ እንደሚችሉና በዚህ ላይ እነሱን
መታዘዝ እንደሚቻል ማመን ማለት ነው::ይህ ተግባር እስላምናን ሀይማኖት
እንደሚጋጭ እያወቀ ይህን የሚያደርግን የሚታዘዝ አዛዡን ሰው የአላህ ቢጤ
አድርጓል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ትልቁን ሽርክ ፈፃሚ ነው፡፡አላህ እንዲህ
ይላል፦
ﺍﺗَّﺨَﺬُﻭﺍ ﺃَﺣْﺒَﺎﺭَﻫُﻢْ ﻭَﺭُﻫْﺒَﺎﻧَﻬُﻢْ ﺃَﺭْﺑَﺎﺑًﺎ ﻣِّﻦ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻤَﺴِﻴﺢَ ﺍﺑْﻦَ ﻣَﺮْﻳَﻢَ ﻭَﻣَﺎ ﺃُﻣِﺮُﻭﺍ ﺇِﻟَّﺎ
ﻟِﻴَﻌْﺒُﺪُﻭﺍ ﺇِﻟَﻬًﺎ ﻭَﺍﺣِﺪًﺍ ﻟَّﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﺳُﺒْﺤَﺎﻧَﻪُ ﻋَﻤَّﺎ ﻳُﺸْﺮِﻛُﻮﻥَ
‹‹ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ
ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም
ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡››
(አል ተውባህ 31)
የዚህ አንቀፅ ትርጓሜ፡- ዑለማዎችንና ባህታዊያንን በኃጢአት መታዘዝ ማለት
እንጂ እነርሱን መለመን ማለት እንዳልሆነ ነብዩ አብራርተዋል፡፡
ዓዲይ ኢብኑ ሃቲም ለነቢዩ (ﷺ)
“እኛኮ ስናመልካቸው አልነበረም” ሲላቸው
እንዲህ በማለት እነርሱን ማምለክ ማለት የአላህን ህግ በመቀየር በወንጀል
ሲያዙ ትዕዛዛቸውን መቀበል ማለት እንደሆነ ገለፁለት “አላህ ሀላል ያደረገውን
ሲከለክሏችሁ እናንተ ትታዛቿቸው አልነበረምን? አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ
ሲፈቅዱ እነርሱን በመታዘዝ የተፈቀደ ታደርጉ አልነበርን? “እንዴታ” ሲላቸው
እነርሱን ማምለክ ማለት ይኸው ነው አሉት፡፡››
📚4 በውዴታ ማጋራት፡-
ማክበር፣ ማላቅ፣መዋረድና መተናነስን የሚያስከትል ለአላህ እንጂ የማይገባን
ውዴታ ለፍጡር ማድረግ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻣَﻦ ﻳَﺘَّﺨِﺬُ ﻣِﻦ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻧﺪَﺍﺩًﺍ ﻳُﺤِﺒُّﻮﻧَﻬُﻢْ ﻛَﺤُﺐِّ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﺷَﺪُّ
ﺣُﺒًّﺎ ﻟِّﻠَّﻪِ
‹‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ
የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ
(ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡››
(አል በቀራህ 165)