abu imran Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

abu imran shared a
Translation is not possible.

🚨🚨ትላንት በጋዛ ምን ተፈጠረ?

ትላንት ምሽ 4፡30 አከባቢ ላይ አልቃሳም ብርጌድ በፈፀመው እጅግ የተጠና ጥቃት ቢያንስ በመጀመሪያ ደረጃ በተደረገ ቆጠራ ብቻ 20 የእስራኤል ወታደሮች በአንድ ጊዜ መገደላቸውን እን መቁሰላቸው የተገለፀ ሲሆን ለሰአታት እስራኤል መረጃው ማንም ጋር እንዳይደርስ ስትቆጣጠር ብትቆይም አጋጣሚው በጣም ከፍተኛ የፀጥታ ችግር በካን ዮኒስ እንዲፈጠር አድርጎ እንደነበር የጽዮናውያን ምንጮች ገልጸዋል።

አልቃሳም ብርጌድ እና ሌሎች የተቃውሞው አጋሮች በርካታ የእስራኡል ወታደሮች የገቡበትን ሁለት ህንጻዎችን ማፈንዳታቸው የተዘገበ ሲሆን ሶስተኛው ህንጻ በመላው የጽዮናውያን ሃይል ላይ ወድቋል። የጽዮናውያን ምንጮች ዛሬ ጠዋት ላይ በደቡባዊ ጋዛ ሶስት መኮንኖች መሞታቸውን የእስራኤል ጦር ካመነ በኋላ "ተጨማሪ የሞቱ ሰዎች አሉ" እያሉ ይገኛሉ። የተጎዱ ወታደሮች ሲጓጓዙ የሚያሳይ ምስልም ወጥቷል፡፡

በምዕራባዊ ካን ዮኒስ ከፍተኛ ግጭት ቀጥሎ ያደረ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች የገ፤ልፁ ሲሆን የጽዮናዊያን ሃይሎች ከደቡብ ምስራቅ የከተማዋ ክፍል ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

የጽዮናውያን ምንጮች ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትላንት “በጣም አስቸጋሪ ከሆኑ የውጊያ ቀናት አንዱ ነው” ሲሉ ገልፀውታል። ባለፉት 24 ሰዓታት በትንሹ 15 የቆሰሉ ወታደሮች ወደ "ሶሮቃ" ሆስፒታል ተወስደዋል።

እኩለ ሌሊት 7፡00 አከባቢ በወጡ ተጨማሪ መረጃዎች መሰረት ደግሞ በካን ዮኒስ የተፈፀመው ዋናው የጸጥታ ችግር በጽዮናውያን የደህንነት ክትትል ስር የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው በመጀመሪያ ቆጠራ ቢያንስ 20 የእስራኤል ወታደሮች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል, ሌሎች ደግሞ ጠፍተዋል የሚል መረጃ ተረጋግጧል፡፡

ቆይተው በወጡ ተጨማሪ መረጃዎች ከጥቃቱ በኋላ ወዲያው 130 የእስራኤል የነፍስ አድን አባላት ከተጠባባቂ ወታደሮች ወዲያውኑ ወደ ጋዛ በአውሮፕላን ተወስደዋል። በነፍስ አድን ሙከራው ላይ ዘጠኝ ሄሊኮፕተሮች ተሳትፈዋል፣ ይህም ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትልቁ አደጋ መከሰቱን ያሳያል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሪፖርት እንደሚደረግም ይጠበቃል።

አል-ቃሳም ብርጌድ፡ ይህን ክስተት ባሳወቀበት ሪፖርቱ ከህንፃዎቹ ፍንዳታ ጥቃት በተጨማሪ አንድ የእስራኤል ታንክን አነጣጥሮ ካወደመ በኋላ የጽዮናውያን የነፍስ አድን ሃይል ታንኩን ጥቃቱ ከደረሰበት ቦታ ላይ ለማንሳት ሙከራ ሲያደርጉ ተዋጊዎቻችን ተኩስ የከፈቱባቸው ሲሆን ወደ ተሽከርካሪው እንዳይሄዱ በመከልከላቸው የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ወታደሮቻቸውን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ታንኩን ኢላማ አድርገው ያፈነዱት ሲሆን በውስጡ የነበሩት ሁሉንም ወታደሮቻችውን ጨምረው አጥፍተዋቸዋል ብሏል፡፡

የእስራኤል ጦር እውነተኛ መረጃ የማያሳውቅ ቢሆንም እስካሁን በወጡ መረጃዎች ትላንት ቢያንስ 20 የውራሪዋ ወታደሮች መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group