UMMA TOKEN INVESTOR

Hussen Esmael поделился
7 месяцев перевести
Перевод невозможен

አሁን የሙስሊሞቹ አቋም ተጠናክሯል👍🧲✅

✅ዛሬ ጠዋት ናሃል ኦዝ በተተኮሰው ሚሳኤል የተገደሉ ሁለት የወራሪዋ ተዋጊዎች ራዝ ፔሬዝ እና ዚቭ ዳዱ።

✅የቀሳም ጦረኞች የእስራኤል ጦር ሰፈርን አተራምሰው ከወጡ በኋላ የወራሪዋ ወታደሮች የቀሳም ብርጌዶች መስለዋቸው እርስ በርስ በመታኮስ ጓደኞቻቸውን መግደላቸውን የእብራይስጥ ሚዲያ ሀርትስ ዘግቧል።

ተመልከቱ ልባቸው ውስጥ ያለውን ሽብርና ፍርሀት

✅"እኛም ደህና ነን ተቃውሞውም ጥሩ እየሄደ ነው ከወራሪዋ የእግረኛ ጦር ጋር ፊት ለፊት ልባችሁ ደስ ለሚሰኝበት ዘመቻ ተዘጋጅተናል"

የሀማስ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ሳሊህ አል አሩሪ

⭕️በምትበረው ወፍ መደናበራቸው⭕️

✅የዕብራይስጥ ሚዲያ እንደዘገበው

  ከዮርዳኖስ አቅጣጫ ወደ ወራሪዋ ከተማ በመብረር ላይ የነበረችው እርግብ ሮኬት ናት በሚል የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል በስህተት መተኮሳቸውን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አስታውቋል።

እርግቧ እንዲህ ካስደነገጠቻቸው የቀሳም ሚሳኤሎች ምን ያህል እንዳሸበራቸው መገመት አይከብድም።

Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
Hussen Esmael Изменил свою фотографию
7 месяцев
Перевод невозможен

image
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
Hussen Esmael поделился
7 месяцев перевести
Перевод невозможен

👉   በዱዓእ ስሰታም አንሁን

    ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ በሚሰራው ነገር ሁሉ ጥበቡ ሙሉ ነው ። ለባሮቹ እናት ለምታጠባው ልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ ነው ።

   በዚህች ምድር ላይ ብዙ ግፎች ይስተናገዳሉ ። የአላህ ጠላቶች በባሮቹ ላይ የሚያደርሱዋቸውን ግፎች እያየ መተዉ እራሱ የቻለ ረቂቅ ሚስጢር አለው ። እሱ የላካቸው ነብያቶች ሲገደሉ ፣ ለሁለት ሲከፈሉ አይቶ ማለፉ ለምን እንደሆነ የሚያውቀው እሱ ነው ።

    ማን አለብን ባዮች በሱ ደካማ ፉጡሮች ላይ የሚሰሩትን ግፍ እያየ መታገሱ እሱ ለሚያውቀው ጥበብ ነው ።

     በጥቅሉ ግን በባሕርና በየብስም ቢሆን የሚከሰተው ፈሳድ በላእና ፈተና የሚመጣው የሰው ልጆች በሚሰሩት ወንጀል መሆኑን ነግሮናል ።

    የወንጀል ተፅኖ በጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት እንደሚከለክል አላህ የነብዩ ተከታዮች በእሁድ ዘመቻ ቀን የደረሰባቸውን ሽንፈትና ሽሽት ከእነርሱ ውስጥ ከፊሎች ከዛ በፊት በሰሩት ወንጀል ተፅኖ መሆኑን ሲነግረን እንዲህ ይላል : –

« إِنَّ الَّذِينَ تَوَلَّوْا مِنكُمْ يَوْمَ الْتَقَى الْجَمْعَانِ إِنَّمَا اسْتَزَلَّهُمُ الشَّيْطَانُ بِبَعْضِ مَا كَسَبُوا ۖ وَلَقَدْ عَفَا اللَّهُ عَنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ »

                    آل عمران  ( 155 )

" እነዚያ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙ ቀን ከእናንተ የሸሹት ሰዎች በዚያ በሠሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው ፡፡ አላህም ከነሱ በእርግጥ ይቅር አለ፡፡ አላህ መሓሪ በቅጣት የማይቸኩል ነውና ፡ ፡ "

    ከዚህ አንቀፅ የምንረዳው የወንጀል ተፅኖ ከጠላት ፊት ለፊት በሚገናኙበት ጊዜ ጭምር ድል እንደሚከለክል ነው ። ለዚህ ነው አላህ ከወንጀል እንድንርቅ አጥብቆ የሚነግረን ።

    የአላህ መልእክተኛ በተለያዩ አስተምሮዋቸው የወንጀል አስከፊነትና በቅርቢቱም ሀገር በሚቀጥለውም ዐለም ውርደት እንደሚያሸልም ያስተማሩን ። በተለይ ወንጀሉ በአላህ ላይ ማጋራት ሲሆንና በነብዩ ዲን ላይ አዲስ ነገር መፍጠር ሲሆን ክብደቱና ውጤቱ የከፋ ይሆናል ።

     አላህ እኛን ካልነበርንበት አስገኝቶ መቁጠር የማንችለው ፀጋ ሰጥቶ ተንከባክቦ እያኖረን የሱን ስልጣን ለሌላ አሳልፈን ስንሰጥ ክብደቱን እንመልከት ። ዛሬ ከሀዲያን በሙስሊሞች ላይ በሚያደርሱት ግፍ ስናይ  እየተሰማን ያለውን ህመም እንመልከትና ባሮቹ በአላህ ላይ ከሚሰሩት ወንጀል ህመም ጋር እናነፃፅረው ። የሁለተኛው የለም ቢባል መዋሸት አይሆንም ።

     አላህ አዛኙ ጌታ በእዝነቱ ለባሮቹ አዝኖ ከሚደርስባቸው ግፍና መከራ አውጥቶ ወደርሱ እንዲመለሱ እንዲያደርጋቸው ዱዓእ እናድርግ ። እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም ታመናል ።

    በሁነይን ዘመቻ ቀን ምድር ከመስፋቷ ጋር በሶሓቦች ላይ ከጠበበች በኋላ አላህ ድል እንደሰጣቸው ሁሉ ምድር ለጠበበችባቸው ባሮቹ ድል እንዲሰጥና ማን አለብኝ ባይን እንዲያሳፍር እንለምነው ።

    እየአንዳንዱ ክስተት አስተማሪ ነውና እኛም ከዚህ ተምረን ተውበት አድርገን ወደርሱ እንመለስ ። እኛም ዛሬ ማን አለብን ብለን የነብያትን አስተምሮ አንሰማም የተውሒድ ተጣሪዎችን ጠላት እናደርጋለን ካልን የሁለት ሀገር ውርደት ይጠብቀናል ። በመሆኑም ፊታችን ወደ ተውሒድ አዙረን አላህን በብቸኝነት ማምለክና መልእክተኛውን መከተል አምሳያ የሌለው የልቅና በር መክፈቻ ቁልፍ ነው ።

    አላህ ሙስሊሞችን ወደ ተውሒድና ወደ ነብይ መከተል መልሶ የልቅና ባልተቤት ያድርግልን ። በእዝነቱ የፍሊስጢን ህፃናትና አዛውንቶችን ከአውሬ ጠላት መንጋጋ ያውጣቸው ።

     ሁላችንም ሌላ ቢያቅተን በዱዓእ አንሰስት ።

    

Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе