ሰውን መሠተር ነው እንጂ ማዋረድ ትርፍ የለውም።
ኢብኑ-ቀይም "በሆነ ወንጀል ሰውን ያነወረ ሰው ያንን ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም" ይላሉ።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ደግሞ "በውሻ ባሾፍ እንኳ ውሻ እንዳልሆን ብዬ እፈራለሁ፡፡"ይላሉ
ደጋጎችና ጥንቁቆቹ እንዲህ ናቸው። በሰው ነውር ላይ ሙድ አይዙም፤ አላህ በፈተነው ሰው አያላግጡም፣ በአፈጣጠሩም ሆነ በእንከኑ አያሾፉም፣ ያጠፋውን ቀርበው ይመክሩታል እንጂ አያሙትም፣ አይስቁበትም።
ሷሊሖቹ ሰዎች:-የጠፉት እንዴት እንደጠፉ ሳይሆን ነጃ የወጡት እንዴት ነጃ እንደወጡ ነው ጭንቀታቸው። ዛሬ በሰው ወንጀል የምትስቁ ነገስ እናንተ ላለመሥራታችሁ ምን ዋስትና አላችሁ? መሳደብም ሆነ መሳለቅ መልካም አይደለም።
አላህ ይሠትረን።
copy