UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

እቅድህ ሰባት ነገሮችን ከግምት ያስገባ እንድሆን እመክርሃለሁ፤ እነዚህን ሰባት ነገሮች ቀጥዬ እዘረዝርልሃለሁ። በእርጋታ አንብበህ በሚገባ ተረዳቸውና እቅድ ስታወጣ ተጠቀምባቸው።

1. መጣጣም;  እቅድህ በህይወትህ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ መሆን ይገባዋል። ራዕይህ እና ተልዕኮህ፤ ፕርግራምህ እና ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች፤እንድሁም ልማዶችህ እና ፍላጎቶችህ መጣጣም አለባቸው ማለት ነው።

2. መመጣጠን; እቅድህ በህይወትህ ላይ መመጣጠንን የሚፈጥርልህ መሆን ይገበዋል።ማለትም የምታወጣው እቅድ በስራህ፣ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት፣በህልምህ/ራዕይህ/ እንድሁም በመንፈሳዊ ህይወትህ መካካል የተመጣጠነ ስኬት ሊያጎናፅፍህ የሚችል መሆን አለበት ማለት ነው።

3.አስፈላጊ ጉዳዮችን ብቻ የያዘ ይሁን;

በእቅድህ ውስጥ የሚካተቱ ነገሮች ለዋናው አላማህ የሚያግዙ ብቻ መሆን አለባቸው።ዋናውን አላማህን ለማሳካት የማይጠቅሙህን ጉዳዮች በእቅድህ ውስጥ አታካትት።

4. ሰው ተኮር ይሁን; እቅድህን ለመተግበር የሌሎች ሰዎች እገዛ ያስፈልግሃል። የሌሎችን እገዛ ለማግኘት ደግሞ እቅድ ስታውጣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ከግምት ውሰጥ ማስገባት አለብህ። የራስህን ፍላጎት ብቻ ማሰብ የለብህም።

5. ተቀያያሪ; እቅድህ አገልጋይህ እንጂ ተቆጣጣሪህ መሆን የለበትም።ስለዚህ ዛሬ ላይ የምታወጣው እቅድ ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ሁኔታዎች ማሻሻል ቢያስፈልግህ በቀላሉ ልታሻሽለው የምትችለው መሆን አለበት።

6. ተንቀሳቃሽ;  እቅድህን በቀላሉ ይዘኸው ልታንቀሳቅሰው በምትችልበት መልኩ ማዘጋጀት አለብህ። ይህም በየጊዜው እንድታየው እና እያንዳንዱን እርምጃህን በእቅድህ ለመገምገም ይረዳሃል።

7.የአላህን ውደታ ለማግኘት የሚረዳህ መሆን አለበት:

ምድራዊ ስኬት ብቻውን በቂ አይደለም።የምታወጣው እቅድ በደ አኼራ መሸጋገሪያ ሊሆንህ ይገባል።

ለሌሎች ማጋራት አይርሱ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከመልካም ሰው ጋር ያሳለፍከው ትንሽዬ ትዝታ ለብዙ ጊዜ ታወሳዋለሁ። በልብህ የማይጠፋ አሻራ ጥሎ ያልፋል። ባሰብከው ቁጥር ይናፍቀሀል። ደስታም ይሰማሀል። ሁሌም ትመኘዋለሁ።

በተቃራኒው ከመጥፎ ሰው ጋር ያሳለፍከው ብዙና ድንቅ ትዝታ ገና ስታስበው ያስጠላሀል። ደስታ ይነሳሀል። ያለመሆኑን ያስመኝሀል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

☞ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡  ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡ 

☞ ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡  ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ  በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡ 

☞ ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡  ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል። 

☞ ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡  ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው

ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።

ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ

ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።

ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ

የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤

በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ

ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።

አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ

አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።

አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ

ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።

ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም

እንኳን ያበላኸው…..

እንኳን ያጠጣኸው….

የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው

አለሁ ባይህ ኪስህ....

የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ

አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ

በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።

መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም

መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።

ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ

አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።

ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው

አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤

የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና

ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።

መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ

አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።

JOIN AND SHARE

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group