Translation is not possible.

እቅድህ ሰባት ነገሮችን ከግምት ያስገባ እንድሆን እመክርሃለሁ፤ እነዚህን ሰባት ነገሮች ቀጥዬ እዘረዝርልሃለሁ። በእርጋታ አንብበህ በሚገባ ተረዳቸውና እቅድ ስታወጣ ተጠቀምባቸው።

1. መጣጣም;  እቅድህ በህይወትህ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ መሆን ይገባዋል። ራዕይህ እና ተልዕኮህ፤ ፕርግራምህ እና ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች፤እንድሁም ልማዶችህ እና ፍላጎቶችህ መጣጣም አለባቸው ማለት ነው።

2. መመጣጠን; እቅድህ በህይወትህ ላይ መመጣጠንን የሚፈጥርልህ መሆን ይገበዋል።ማለትም የምታወጣው እቅድ በስራህ፣ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት፣በህልምህ/ራዕይህ/ እንድሁም በመንፈሳዊ ህይወትህ መካካል የተመጣጠነ ስኬት ሊያጎናፅፍህ የሚችል መሆን አለበት ማለት ነው።

3.አስፈላጊ ጉዳዮችን ብቻ የያዘ ይሁን;

በእቅድህ ውስጥ የሚካተቱ ነገሮች ለዋናው አላማህ የሚያግዙ ብቻ መሆን አለባቸው።ዋናውን አላማህን ለማሳካት የማይጠቅሙህን ጉዳዮች በእቅድህ ውስጥ አታካትት።

4. ሰው ተኮር ይሁን; እቅድህን ለመተግበር የሌሎች ሰዎች እገዛ ያስፈልግሃል። የሌሎችን እገዛ ለማግኘት ደግሞ እቅድ ስታውጣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ከግምት ውሰጥ ማስገባት አለብህ። የራስህን ፍላጎት ብቻ ማሰብ የለብህም።

5. ተቀያያሪ; እቅድህ አገልጋይህ እንጂ ተቆጣጣሪህ መሆን የለበትም።ስለዚህ ዛሬ ላይ የምታወጣው እቅድ ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ሁኔታዎች ማሻሻል ቢያስፈልግህ በቀላሉ ልታሻሽለው የምትችለው መሆን አለበት።

6. ተንቀሳቃሽ;  እቅድህን በቀላሉ ይዘኸው ልታንቀሳቅሰው በምትችልበት መልኩ ማዘጋጀት አለብህ። ይህም በየጊዜው እንድታየው እና እያንዳንዱን እርምጃህን በእቅድህ ለመገምገም ይረዳሃል።

7.የአላህን ውደታ ለማግኘት የሚረዳህ መሆን አለበት:

ምድራዊ ስኬት ብቻውን በቂ አይደለም።የምታወጣው እቅድ በደ አኼራ መሸጋገሪያ ሊሆንህ ይገባል።

ለሌሎች ማጋራት አይርሱ

Send as a message
Share on my page
Share in the group