የጁሙዓ ኹጥባ ተጀምሮ ሚንበር ላይ ኢማሙ ቁመው ሲኾጥቡ ታዳሚዎቹ በፅሞና በማዳመጥ ላይ ናቸው። (ኢማሙ ነቢ ሰዐወ ነበሩ)
ከጀመዓው መሀል የሰልፉን እኩሌታ እያቆራረጡ የሚመጡ ሁለት ቀያይ ተመሳሳይ ቀሚሶችን የለበሱ ህፃናት ይታያሉ። ጨቅላ ከመሆናቸው የተነሳ እየተንገዳገዱ ነበር ሚራመዱት፤ ኢማሙ ይህን ትዕይንት ሚንበር ላይ ሁነው መቋቋም ተሳናቸው።
እኚህ አያት የልጅ ልጆቻቸው እየተንገዳገዱ ሲመጡ ተመልክተው መቻል ቢያቅታቸው ታዳሚውን ትተው ከሚንበሩ ወረዱ። ልጆቹንም በስስት እቅፍ አድርገው በታፋቸው ካስቀመጡ በኋላ ወደ ህዝቡ ዙረው፦‹‹እንደው አላህ ልጆች ፈተና ናቸው ያለው'ኮ እውነቱን ነው። እኔ እኚህ ህፃናትን ሳይ አንጀቴ አልችል ቢለኝ እኮ ነው ሚንበሬን ትቼ የወረድኩት›› ብለው ኹጥባቸውን ቀጠሉ።
--------
ጃቢር የነቢ ሰዐወ የቅርብ ሰው ነው። ቤታቸው ሲገባ የገጠመውን እንዲህ ይተርካል።
ነቢ ሰዐወ ቤት ስገባ ነቢ በሁለት እግራቸው ተንበርክከው በሁለት እጃቸው ደግሞ መሬትን ይዘው ሁለቱን የልጅ ልጆቻቸውን ከጀርባቸው አዝለው እንደ ፈረስ ሲያጫውቷቸው ተመለከትኩ።
ከልጆቹ ልቀልድ ፈልጌ፦‹‹ምንኛ ያማረ ፈረስ ላይ እየጋለባችሁ ነው! ›› አልኳቸው።
ነቢም ሰዐወ ልጆቹን በጀርባቸው እንብርክክ እንደተሸከሙ፦‹‹እነሱስ ቢሆኑ ምንኛ ያማሩ ፈረሰኞች መሰሉህ›› ብለው ቀለዱ።
---------------
እንዲሁ በሌላ ቀን እኒህ ልጅ ወዳድ የሆኑ ነቢይ ተከታዮቻቸውን እያስከተሉ በመስገድ ላይ ሳሉ ቤት የለመደ ህፃን ከመስጂድ ሱጁድ ሲያደርጉ ተመልክቶ ከጀርባቸው ላይ ሊጋልብ ወጣ።
ነቢ ሰዐወ ልጅ ያከብራሉ። ከጀርባቸው ግልቢያውን ጠግቦ እስኪወርድ ሱጁድ አድርገው ጠበቁት። ከብዙ ቆይታ በኋላ ሲወርድ እሳቸውም ከሱጁድ ቀና አሉ።
በመጨረሻም ሰላቱ ሲጠናቀቅ ከኋላ ሁነው ሲሰግዱ የነበሩ ሰሓባዎች ሱጁድ እጅግ ስለረዘመባቸው ለምን እንደረዘመ ጠየቁ።
ነቢም ሰዐወ፦‹‹ይህ ልጄ ሱጁድ ላይ ሳለሁ ከጀርባዬ ወጥቶ ጫወታውን ጀመረ። ጨዋታውን ሳይጨርስ እንዳላቋርጠው ብዬ ሱጁዴን አስረዘምኩት›› አሉ።
የኔ ነቢ አባትነት....... አያትነት...... መሪነት...... ታዛዥነት....... አዛኝነት
«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»