Abdulmejid Hussein Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

Последствия одного из израильских авиаударов в Газе сегодня

5 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Последствия одного из израильских авиаударов в Газе сегодня

5 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፍለስጢን ላይ ያሉ ወንድሞቻችንን በዱዓ እናስባቸው።

የማን ዱዓ ተቀባይነትን እንደምያገኝ አናውቅምና ሁላችንም በዱዓ እንበርታ። ለዚህ ማሳያ አንድ ታሪክ ላጋራችሁ።👇👇👇

በታብዒዮች ዘመን ነው ።

ዐብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ለግላቸው ጉዳይ ወደሆነ ሀገር ሄድኩ ይላሉ። የሄዱበት ሀገር በዝናብ እጦትና በድርቅ የተመታ ሀገር ነውና ህዝቡ በአምስት ወቅት ሰላት ላይ ቁኑት ያደርጋል ምንም ጠብ አይልም ። አንድ ቀን ህዝቡ ሰላቱን ሰግዶ እንደተለመደው ዱዓ አድርጎ ወደየ ቤቱ ተበተነ። እሳቸው ደግሞ ከዒሻ በኋላ መስጂድ ለማደር ገባሁ ይላሉ ። መስጂዱ ውስጥ አንድ ሰው ጥግ ላይ በሱጁድ አላህን እየለመነ አገኙት። እሱ ግን አላገኛቸውም ።

ይህ ባሪያ እንዲህ ይላል:-

" አላህ ሆይ ባሪያዎችህ ባንተ ተስፋ ቆርጠዋል በዝናብ እጦት ሰውና እንሰሳት አለቁ " በማለት እያለቀሰ ዱዓ አድረገ። ከመስጅድ ሳይወጣ ዝናብ ዘነበ። ሰውዬ በጭቃ እየተራመደ ሄደ ።

ኢብኑ ሙባረክ ተከትዬው ወጣሁ ይላሉ ። ዱካውን እየተከታተልኩት የሆነ ቤት በመስኮት ዘሎ ገባ ይላሉ። የገባበትን ቤት ጠጋ ብዬ ሳይ ጥቋቁር የተጎሳቆሉ ሰዎች በብዛት አሉበት። ይህ ቤት የባርያ መሸጫ እንደሆነ ተነገራቸው። በነጋታው ባለቤቱን ፈልገው አገኙትና ባሪያ መግዛት እንደሚፈልጉና እዛ ውስጥ ካሉት ይህን ሰውዬ ነው መግዛት ምፈልገው አልኩት ይላሉ። ባለቤቱም እዚህ ውስጥ ካሉት መርጠህ ውሰድ ይሄ ሰውዬ ሲቀር ኣላቸው። ምክንያቱም ከሁሉም ደካማና ለምንም የማይሆን ሰው ነው እሱ አይሆንህም ኣላቸው። እሳቸውም እንደምንም አሳምነው ገዝተው ወሰዱት። ባሪያው ጠየቀኝ ይላሉ "ባለቤቱ እውነታውን እየነገረህ ለምን እኔን መረጥክ"?

እሳቸውም ማታ ዱዓ አድርጎ በሱ ሰበብ ዝናብ እንደዘነበ እና የዚህንም ሚስጥር እንዲነግራቸው ጠየቁት። ከአላህ ጋር ያለህ ሚስጥር ምንድነው ብዬ ጠየኩት ይላሉ።

እሱም አልናገርም አለ። እሳቸውም እንዲነግራቸው ወተወቱት እሱም እሺ ትንሽ ጠብቀኝ ብሎ ሱጁድ ተደፍቶ ረጅም ዱዓ ማድረግ ጀመረ ። ቢጠብቁ አይነሳም። ጠጋ ብለው ሲሰሙት " አላህ ሆይ ሚስጥሬን ግልፅ አውጥተሀዋል ከዚህ በኋላ ምድር ላይ መቆየት አልፈልግም" ብሎ ዱዓ ያደርጋል። እሳቸውም ይነሳል ብለው ሲጠብቁ በዛው ሞተ።

ለአላህ እንዲህ አይነት ባሪያም አለው

✍በኢብኑ የሕያ

Send as a message
Share on my page
Share in the group