munros abusalsa Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
5 month Translate
Translation is not possible.

🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ

- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤

ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡

@Alwan_tube || አልዋን ቲዩብ

@Alwan_tube || አልዋን ቲዩብ

https://t.me/+KeXAmvRpm0k1NDk0

https://t.me/+KeXAmvRpm0k1NDk

ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እጅግ ልብ የሚነካ ታሪክ

አንድ ሰሃቢ ወደ ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ) በመምጣት "አንቱ የአላህ

መልዕክተኛ አባቴ ሳያስፈቅደኝ ገንዘቤን ተጠቀመበት" ብሎ ስሞታ አቀረበ።

ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ) አባቱን ይዞ እንዲመጣ ነገሩት። አባትየውን ሲጠሯቸው

ለምን እንደሆነ ጠየቁ። ልጃቸው ቅሬታ አቅርቦባቸው መሆኑን ሰሙ።

እጅግ በጣም ቅር አላቸው። ሲመጡ በመንገዳቸው በልባቸው የተሰማቸውን

በግጥም መልክ አሉት። ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ) ወዳሉበት ቦታ ሄዱ። ቦታው

ላይ ከመድረሳቸው በፊት ጅብሪል(ዐ ሰ) ወደ ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ)

መልዕክት ይዞ ብቅ ብሎዋል። "አባትየው ሲመጡ አስቀድመህ በልቡ ይል

የነበረውን ትጠይቀው ዘንድ የአላህ(ሱ ወ) መሺዓ ነው" አላቸው።

አባትየው ድምፅ አውጥተው ባይናገሩትም የልብ አዋቂው ጌታችን አላህ(ሱ ወ)

ስሞታቸውን አድምጧቸዋል። ለኛ መማሪያ ይሆን ዘንድ መላይካውን ጅብሪል(ዐ

ሰ) ላከልን። ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ) "ጉዳዩ ላይ ከመግባታችን በፊት ስትመጣ

በልብህ ትለው የነበረውን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ" አሉት።

አባትየው በመገረም "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ መሆናችሁን እመሰክራለሁ።

እውነት ነው በመንገዴ ስመጣ አዝኜ በውስጤ ሳወራ ነበር። በልቤ ብናገረውም

አላህ ሰምቶኛል። አንተም ሀቅ ነህ ጌታህም ሀቅ ነው" አሉት። ነብዩ ሙሀመድ(ሰ

ዐ ወ) "ምን ነበር ትናገር የነበረው?" ብለው ጠየቁት።

አባትየውም ያሉትን ተናገሩ። "ልጄ አንተን ከወለድን ጀምሮ ለኛ መኖር ትተን

ላንተ መኖር ጀመርን። አንተን ለማስጠለል ነፋስን ታገልን። ቅዝቃዜ እንዳይነካህ

በረዶ ላይ ሰራን። ፈገግታህን ለማየት በማታ ሰራን። ሙሉ ለሊት እንደ እንስሳ

ለፋን። የወጣትነት ጉልበቴን አድክሜ አጥንትህን አጠነከርኩ። ላንተ ወጣትነት

ስለፋ እኔ አረጀሁ። ጀርባዬን አጥፌ ጀርባህን አቀናሁ።

በእግርህ ቆመህ እንድትሄድ ስለፋ እግሮቼ ሀይል አጡ። እጆችህ ሲጠነክሩ

የኔው ይንቀጠቀጥ ጀመር። ላንተ ስል ደከምኩ አንተ ግን አመፅክብኝ። ላን ስል

መድከሜ፣ ዱዓ ማድረጌ፣ ረፍት ማጣቴ እያደር እገዛ ይሆነኛል ብዬ አስቤ ነበር።

ነገር ግን ወጣትነት አንተ ላይ ሲነግስ እኔን እርጅና ጨረሰኝ። ወጣትነት ላንተ

ውበት ሲለግስህ እርጅና እኔን አረገፈኝ።

እርጅና ቢጠናብኝ ፊትህን አዞርክብኝ። ባሪያህ አደረከኝ። እኔ ታዛዥ አንተ አዛዥ

ሆንክ። የ30 አመት ልፋቴን አስዋሸሁ። አባትነቴን ረሳሁ። ባሪያህ ሆንኩኝ። ልጄ

ቢሆን ኖሮ ይህን አያደርግም ብዬ አሰብኩ። በብርድና በሞቃት ቀን ከለሊት

መልፋቴን ረሳህ። ስሜቴንና ደስታዬን ቀበርኩት። ዛሬ ላይ አንተ አለቃዬ እኔ

ባሪያህ ሆንኩኝ። እሺ ባሪያህ መሆኔን ልቀበል ግን ጎረቤትህም ጭምር ነኝ።

ሰው ጎረቤቱን ይጠይቃል። እየኝ ዛሬ እያለቀስኩ ነው" ብለው በሲቃ ድምፅ

ተናገሩ።

የአባትየውን ቃላቶች አማርኛ ችሎ አይገልፀውም። ነብዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ)

ይህን ሲሰሙ አለቀሱ። የልጁን ኮሌታ አጥብቀው ያዙና "ከዚህ ጥፋ። አንተም

ሆነ ያንተ ንብረት ያባትህ ነው። የኔ ነው የምትለው ሁሉ ያባትህ ነው" አሉት።

የአባቶቻችንን ሀቅ እንጠብቅ። ለኛ ብለው የደከሙትን አላህ ብቻ ነው

የሚያውቀው። አባት ቀልብ ያደረገበት ልጅ አያልፍለትም። ዱንያም አሄራውም

አያምርም። የአባቶችን ሀቅ ከሚጠብቁ ሙዕሚኖች አላህ ያድርገን።

በማያልቀው የአላህ አጅር ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ይህን መል ክት ሼር በማድረግ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group