2 years Translate
Translation is not possible.
🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣
 
- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ
 
ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡
 
1- ልብሴን ያወልቃሉ፣
 
2- ያጥቡኛል፣
 
3- ይከፍኑኛል፣
 
4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣
 
5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣
 
6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣
 
7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡
 
ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡
 
8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል
 
- ቁልፎቼ 🔑🗝
 
- መጽሐፎቼ 📚
 
- ጫማዎቼ 👟
 
- ልብሦቼ 👖👔…..
 
በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡
 
- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣
 
- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣
 
- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣
 
- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣
 
- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣
 
- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤
 
- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል
 
- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤
 
 
 
ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …
 
በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ
 
1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ
 
2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣
 
3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣
 
የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ
 
ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!
 
1- መልክህ፣
 
2- ሀብትህ፣
 
4- ጤናህ፣
 
5- ልጅህ፣
 
6- ቪላህ፣
 
7- ዝናህ፣
 
8- ሚስትህ/ባልሽ
 
ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ
 
እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡
 
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ
 
ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡
 
እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ
 
1- በግዴታዎች፣
 
2- በሱንና ነገሮች፣
 
3- በድብቅ መፅውት፣
 
4- መልካም ሥራ አብዛ፣
 
5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣
 
ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡
 
መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡
 
@Alwan_tube || አልዋን ቲዩብ
@Alwan_tube || አልዋን ቲዩብ
https://t.me/+KeXAmvRpm0k1NDk0
https://t.me/+KeXAmvRpm0k1NDk
 
ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️
Send as a message
Share on my page
Share in the group