UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የምድራችን ትልቋ እስር ቤት ስለ ፍልስጤሟ ጋዛ ከተማ(Gaza)

1.ጋዛ ማለት መካከለኛው ምስራቅ ላይ የምትገኝ በ ቆዳ ስፋቷ የአዲስ አበባን ግማሽ የምታክል ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የከተማ ነዋሪ ከምድር የተነጠሉ እስረኞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። በ 1967 እስራሄል ጋዛን ከወረረች ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በእስራሄሎች ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች::

2. ጋዛ በ3ቱም አቅጣጫዎች በእስራሄል ወታደሮችና በድርብ የኮንክሪት ግንብ የታጠረች በፊትለፊቷ በእስራሄል የባህር ሀይሎች የተከበበች ሲሆን በ 1ኛው አቅጣጫ ደሞ በግብፅና በ ዩናይትድ ኔሽን ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ታጥሯል ያ ማለት ጋዛ ልክ እንደ ትልቅዬ እስር ቤት ናት አይደለም ጋዛውያን ወፍ እንኳን ያለ እስራሄል ፍቃድ መውጣትም ሆነ መግባትም አትችልም::

3. እስራሄል ጋዛን ከመውረሯ በፊት አይሁዶች ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ጋዛ ውስጥ ከ1ዐዐዐ አመት በላይ በሰላም ይኖሩ ነበር። አሁን ላይ ግን እስራኤል በምታደርገው መስፋፋት እና የጦር ጭፍጨፋ አብዛኛው የፍልስጤም ምድር በመቀማቷ አብዛኛውን ከሞት የተረፉ ተፈናቃዮች በጋዛ ትልቁ የከተማ እስር ቤት አከማችታ ደስ ሲላት በቦንብ እያነደደቻቸው ነው የምትገዛቸው ።

4. ጋዛን ከሌላው አለም ሆነ ከተማ የሚያገናኝ የባህር ትራንስፖርት የለም አየር መንገድ የለም ባቡር የመኪና ትራንስፖርት የለም;;

5. የጋዛ ነዋሪዎች ጋዛን ለቀው መውጣት አይችሉም ሌላው ይቅር ፓስፖርት እንኳን የላቸውም ሌላው ደሞ ከጋዛ መውጣት ብቻ አይደለም ከባዱ ነገር ማንም ሰው ያለ እስራሄሎች ፍቃድ ወደ ጋዛ መግባት አይችሉም። አይደለም ለተራ ሰዎች ባለስልጣኖችና የሀገር መሪዎች ያለእስራሄሎች ፍቃድ አይገቡም በቃ ጋዛ ማለት ከሌላው አለም ተነጥላ የምትኖር የከተማ እስር ቤት ናት::

6. ከሻይ ቅጠል ጀምሮ እስከ መድሀኒቶች አልባሳቶች እኛ በየቀኑ እንደልባችን ከሱቅ የምንገዛቸው የእለት ተእለት እቃዎች ወደ ጋዛ ለመግባት ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ አለባቸው በየትኛውም አቅጣጫ ይምጡ ግዴታ የእስራሄል ጣቢያ ገብተው ተፈትሸውና ከፍተኛ ቀረጥ ከፍለው ነው ማለፍ የሚችሉት በጦርነት ጊዜ ይሄም ሊቀር ይችላል::

7. ጋዛ ማለት ልክ እንደ ትልቅ እስር ቤት ናት ድንበሮቿ ብቻ አይደሉም በእስራሄል የተከበቡት ጋዛ ውስጥ እራሱ እስራሄል ብዙ የፍተሻ ጣቢያዎች አሏት። ጋዛውያን ወደ ስራ ወይም ትምህርት ቤት ለመሄድ በየመንገዱ ባሉ በነዚ የፍተሻ ጣቢያዎች መፈተሸና ማለፍ አለባቸው 8 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራሄል ጋዛ ላይ እየተገበረች ያለችውን ኢሰብሀዊ ድርጊት እንድታቆም ከ 50 በላይ ጊዜ ትህዛዝ ቢያስተላልፍም እስራሄል ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ቀጥላበታለች::

9. የጋዛውያን መከራ አያልቅም ጋዛ የምግብ እጥረት አለባት:: እስራሄል ድንበሯን በመዝጋቷ በፊት የሚመጡ እቃዎች ቆመዋል ሱቆች ባዶ ሆነዋል ሆስፒታሎች በቂ መድሀኒት የላቸውም የጋዛ 80 ፐርሰንት ህዝብ ማብራትና ውሃ አያገኝም ሁሉ ነገር በ እስራሄል ቁጥጥር ውስጥ ይገኛል የኑሮ ውድነት ከላይ ደርሷል። በዚ ሁሉ መሃል የጋዛ ህፃናትን ስቃይ በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል::

10. ጋዛ ውስጥ ስፔሻላይዝድ ዶክተሮች የሉም እስራሄል ወደጋዛ ሚሳሄል በተኮሰች ቁጥር የሚጎዱት ንፁሀን ከጋዛ ወተው መታከም አይችሉም በየድንበሩ እነዚህ የተጎዱ ሰዎች ለመውጣት ይለምናሉ ነገር ግን እስራሄል አትፈቅድላቸውም ክፉኛ የተጎዱት እዛው ጋዛ ተሰቃይተው ይሞታሉ።

11. ከአመታት በፊት ሰላማዊና ሀብታም በነበረችው ጋዛ የሚኖሩ ፍሊስጤማውያን በገዛ ሀገራቸው ለማኞችና ድሃ ሆነዋል እነዚህ ህዝቦች ሀገራቸው ተወሮ እስረኛ ተደርገው በየቀኑ እየተገደሉ

እየተደበደቡ የሚደርስባቸውን ስቃይና መከራ አስባቹታል፣ ጋዛዊያንን ከ 5ዐ ኣመት በላይ ለነፃነታቸው ሲታገሉ ኖረዋል ነገር ግን በየቀኑ እስራሄል የበለጠ መሬት እየወሰደችባቸው ለዜጎቿ መኖሪያዎችን እየገነባች የነፃነታቸው ተስፋ እንማንኛውም የአለም ህዝብ በሰላም ሀገራቸው ላይ የመኖርን መብት ነፍጋ በስቃይ የምትገዛቸው የምድራችን ኢፍትሃዊነት ማሳያ የሆኑ ህዝቦች መገኛ ናት።

አሁን ላይ በዚህች እስር ቤት የሚገኙ ጋዛዊያንና ጋዛን ሙሙሉ በሙሉ በአሜሪካና በእስራኤል ትብብር ጠርጎ ለመጨረስ ወስነው የምግብ የመብራትና የውሃ አገልግሎት አቋርጠው በአየርና በምድር እየጨፈጨፏቸው ይገኛል ። የምዕራባዊያን ጉልበተኞች ፀረ ዲሞክራሲና ፀረ ሰብዓዊነት ትልቁ የዘመናት ማሳያ የሆነችው ጋዛ እንድትጠፋ ተወስኗል።

አላህዬ ለተበዳዎች ፍልስጤሞች እዝነትህን ለግሳቸው!

C ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet

image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reis Bedru Yishak Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group