UMMA TOKEN INVESTOR

1 year Translate
Translation is not possible.

አል-አቅሷ› የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ

1. መስጂድ አል-አቅሷ የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷና ዙሪያውን የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ ብሎታል፡፡

(አል-ኢስራእ ፡1)

2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ ከመካው መስጂድ ወደ መስጂድ አልአቅሷ ከዚያም በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ ከመካ ወደ በይት አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡

3. በአል-አቅሷ መስጂድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ነቢያትን ኢማም ሆነው አሰግደዋል፡፡

4. የነቢያት አባት ነቢዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ.) ጨምሮ አል-አቅሷና አካባቢው ብዙ የአሏህ ነቢያት የተላኩበት ምድር ነው፡፡

5. እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች ስምምነት አል-አቅሷን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነቢዩ ሱለይማን ኢብኑ ነቢዩ ዳዉድ (ዐ.ሰ.) ግንባታውን በማደስ አጠናከሩት፡፡

6. በምድር ላይ አሏህን ለማምለክ ታስቦ የተገነባው የመጀመሪያው መስጂድ መስጂድ አልሐራም (ከዕባ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው፡፡

7. አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ ነው፡፡ ሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆነ ከመደረጉ በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደዚያ ዞረው ሰግደዋል፡፡

8. ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት መስጊዶች ውስጥ አንዱ አል-አቅሷ ነው፡፡

9. በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡

10. በአል-አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ (መስጂድ አልሐራም)ና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡

11. አሏህ ሐቅ ላይ ሆነው ለሚዘልቁ በበይት አልመቅዲስ ጉያ ለሚገኙ ሙስሊሞች ድልን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡

12. በርካታ ሶሓቦችና ትላልቅ ደጋግ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ስለ አል-አቅሷ ደረጃና ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡

13. አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ ሙስሊሞች የከፈቱት በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.) ዘመን ነበር፡፡

14. ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡ የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው፡፡

15. አልአቅሷን ከጎበኙ ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ፣ አቡ ዑበይዳ፣ የምእመናን እናት ሶፍያ ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣ ኻሊድ ኢብኑ አልወሊድ፣ አቡ ዘር፣ አቡ ደርዳእ፣ ሰልማን አልፋሪሲይ፣ ዐምር ኢብኑ አልዓስ፣ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ፣ አቡ ሁረይራ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁም) እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

16. በርካታ ትላልቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንትም ለትምህርትና ለኑሮ ወደዚያው ተጉዘዋል፡፡ ታዋቂው ሙፈሲር ሙቃቲል ቢን ሱለይማን፣ ኢማም አልአውዛዒ፣ ኢማም ሱፍያን አስሠውሪይ፣ ኢማም ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሻፊዒይና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

17. ይህ አካባቢ የሰው ልጆች ከሞት በኋላ የሚነዱትና እንዲሰበሰቡ የሚደረጉበት የተከበረ ስፍራ (ምድር) ነው፡፡

18. አል-አቅሷና ምሥራቅ የአል-ቁድስ ከተማን አይሁዶች የተቆጠጣሩት የግማሽ ምዕተ አመት ዕድሜ አንኳን አልሞላውም፡፡

የፍልስጤም ምድርም ሆነ በአጠቃለይ ሻም የሚባለው ሀገር የበርካታ የአሏህ ነቢያት መፍለቂያ ነው፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ ሻም የሚባለው ምድር ልብ ነው፡፡

ከአይሁዶች እጅ ነፃ የሚወጣበትን ቀን አሏህ ቅርብ ያርግልን!!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ ነገር አለ⁉️

========================

✍ የፈለስጢን (የጋዛ ሙስሊሞች) ጉዳይ በየቀኑ አሳዛኝነቱ ቀጥሏል። በየቀኑ የንጹሐን ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፣ በርካታ መሠረት ልማቶች እየወደሙ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት እስካሁን 5087 ሙስሊሞች በጽዮ'ናዊቷ ያላባራ የቦምብ ዝናብ ተገድ'ለዋል፣ ከነዚህ መካከል 2055 የሚሆኑት ህፃናት ሲሆኑ 1119 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። 217ቱ አዛውንቶች ነበሩ። 1500 የሚሆኑት በፍርስራሽ ስር እንደጠፉ ናቸው፤ ከመካከላቸው 800 የሚሆኑት ህፃናት አሉ። እስካሁን ድረስ ጀና'ዛቸው እንኳ አልተገኘም። 15,273 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አጠቃላይ የተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ አካባቢ ሲሆኑ፤ 685 ሺህ የሚሆኑት ከሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል፣ 565 ሺህ የሚሆኑት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞችና የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ (UNRWA) ጋር ግንኙነት ወዳላቸው ት/ቤቶች ተፈናቅለዋል፣ 101 ሺህ የሚሆኑት በመስጂዶች፣ በቤተ ክርስቲናትና በህዝባዊ ቦታዎች ተጠልለዋል፣ 70 የሚሆኑት በ67 ት/ቤቶች ተፈናቅለው ይገኛሉ።

ሆስፒታሎች፣ ት/ቤቶችና መጠለያ ካምፖች ሳይቀሩ ከእስራኤል የቦ'ምብ ጥ'ቃት ለማምለጥ ዋስ'ትና የላቸውም። ጽዮ'ናዊቷ የማገናዘብና የርኅራኄ ጭላንጭል ስለ'ሌላት በየመኖሪያ ቤቱ ያለውን ስት'ጨርስ ወደተጠለሉበት ቦታ መሸ'ጋገሯ የሚቀር አይመስልም። አንዳንድ አጀማመሯ ይህን ስለሚያሳይ። የምድር ጦር ልጀምር ነው እያለች በተደጋጋሚ ብትዝትም ወዳጆቿ እነ አሜሪካ ሳይቀሩ የጋዛ ሰርጥ መቀ'በሪያዋ እንዳይሆን ስለሰጉና ምን እንደተዘጋጀላቸው ማወቅ ስላልቻሉ እስካሁን ፈራ ተባ እያለች ነው።

የተለያዩ ሃገራት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት ያላትን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅማ የፈለስጢናዊያን ጭፍ'ጨፋ እንዲቀጥል አድርጋለች።

ምን ያክል የፈለስጢን ህፃናትና ሴቶች ተጨፍ'ጭፈው ሲያልቁ እንደምትረካ አይታወቅም።

ሌላውም ዓለም በሰልፍ ድጋፉ እያሳዬ ቢሆንም ከዚያ የዘለለ ማድረግ አልቻለም።

በጋዛ አሁንም ቢሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የምግብና የነዳጅ ማዕቀብ እንደተጣለ ነው። ባለፈ ብቻ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪኖች ገብተው ነበር። ግን ለ2+ ሚሊዮን ህዝብ ምንም ማለት አይደለም። የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመመከት በየቀኑ መቶ የጭነት መኪኖች መግባት አለባቸው።

አላህ በጥበቡ ከላይ ፈረጃውን አውርዶ ካሉበት በላእ ይገላግላቸው እንጂ እየተካሄደ ያለው ይፋዊ የዘር ማ'ጥፋት ወን'ጀል ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሰ'ቃቂ እልቂት ነው።

ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና ሁሌም ወንድሞቻችንን በዱአህ እንበርታ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
moha kur shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ዛሬ በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ለጋዛ ድጋፋቸውን አሳይተዋል

#palestina 🇵🇸💙👌#palestina 🇵🇸💙

image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.
Запись от 21.10.2023 20:37 | moha kur
ummalife.com

Запись от 21.10.2023 20:37 | moha kur

Muslim Social Web | Muslim Social Network
Send as a message
Share on my page
Share in the group