▬▮እ ሥ ከ መ ቼ??▮▬
በጋዜጠኛ ዮናስ አብርሃም
🌍 ዓለም የይስሙላ ሕግ እንጂ -- ሚዛናዊ ፍትሕ እንደሌላት ካወቅን ቆይተናል። ተቋማቱም ጉልበተኞቹ ብቻ የሚጠቀሙባቸው፣ የጠሉትን የሚቀጡባቸው.... የግል ርስት ናቸው።
በተለይ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1990 በኋላ እንዳሻቸው የሚፈነጩበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው፣ የፈለጉትን ሲያደርጉ ኖረዋል። አብዛኞቹ የዓለማችን ሃገራትና ህዝቦቻቸው የተፈፀመባቸውን እጅግ የከፋ በደልና ጥፋት በልባቸው ይዘው የፍርድ እና የፍትሕ ቀን እንደሚጠብቁ ግልፅ ነው።
⚫️ የሠሞኑ ሁኔታ -- የፍልስጤማውያን ሰቆቃ -- ብዙ ነገሮችን ግልፅ አድርጓል። ዓለማችን በሕግና ሥርዓት ሣይሆን -- በጉልበተኞች ፍቃድ እንደምትመራ!!
◉ <የተባበሩት መንግሥታት> እና የአውሮፓ ህብረት ድርጅቶች በማን እንደሚዘወሩ ብቻ ሣይሆን ለማን እንደቆሙ መደበቅ እስኪሳናቸው ድረስ ተዝረክርከዋል።
◉ በኛም፣ በሌሎችም ሃገራት ላይ በአድማ በመቧደን፣ ገና በቅጡ ሳይሰበሰቡ ቅጣትና ማዕቀብ መጣላቸውን አንዘነጋም። ፍርደ ገምድል ውሣኔያቸውን ለማስፈፀም ይጣደፋሉ!!
❓❓❓
◉ ምክንያቱን ብናውቅም፣ መልሱ የተሠወረ ባይሆንም
ጥቂት ጥያቄዎችን ማሰላሰሉ ተገቢ ነው።
➞ የፍልሥጤማውያን መከራ ለምን እስከዛሬ ቆየ??
➞ አሁንስ....አሜሪካና አብዛኞቹ የአውሮፓ ሃገራት ሥለምን የተዛባ አቋም ያዙ??
➞ እኒያ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት በጣም ዘግይተው፣ ለእሥራኤል ፍላጎት ጊዜ ሰጥተው፣ በተፅዕኖና በግፊት ተወጥረው...."የተስማሙበትን" ልሙጥ ውሣኔ እንኳን ለማስፈፀም ለምን አቅም አጡ??
➞ ወደ 8 ቢሊየን የዓለም ህዝብ በማን ፍላጎትን ሤራ ነው የሚመራው??
➞ 10 ሚሊየን የማይሞሉ እሥራኤላውያን [በሃገሪቱ ብቻ ያሉት] ከሕግ በላይ የሆኑበት ሚሥጥር ምንድነው??
➞ አሁንም Ceasefire ቀርቶ pause ተብሎ እንኳን የኔታንያሁ መንግሥት አልሰማ ሲል፣ እኒያ ጉልበተኞች "ያ - ፈጣኑ ፍርዳቸው" የት ገባ??
➞ ሌላው ቢቀር....ፍልስጥኤማውያን የዓለም ህዝብ አካል አደሉምን??
◉ ጎበዝ - ይህ'ኮ በሰው ልጅነት እና በእውነተኛ ፍትህ የሚዳኙት እንጂ በእምነት የሚቧደኑበት ጉዳይ አይደለም!!
◉ እኒህ ተቋማትና <ኃያላን> ተብዬ መንግሥታት ከዚህ በኋላ...ሌሎች ሃገራትና ህዝቦች ላይ የተለመደ አድሏዊ ፍርዳቸውን ለመበየን ሞራል ይኖራቸው ይሆን???
▬ ታሪክ ፍርድ ይሠጣል!!! የሐቅንና የፍትሕን መልስ ለማየት ብዙ የምንዘገይ አይመሥለኝም!!
🌴 ሠላም ለዓለማችን!!