Ajaeb Ali Soraj Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Translation is not possible.

አይሁዳውያን

"አይሁዳውያን በመላው አውሮፓ የጥላቻ ሰለባ ሆነው የነበሩበት ለምን ነበር?ፍልስጤማውያን በገዛ አገራችው ለዘመናት ዋጋ የሚከፍሉትስ ለምን ይሁን?የዓለም አቀፉ ማህበረሰብስ ለምን መፍትሔ አጣ?

የአንድ አባት ልጆች ስለሆኑት ስለ ፍልስጤማውያንና እስራኤላውያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተፃፉ ታሪኮች መካከል ጎልቶ የሚነበበው ባላንጣነታቸው ነው።  የዳዊትና የጎልያድን  ግጥሚያ ሁላችንም እናስታውሳለን።

አይሁዳውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ961_922 በንጉስ ሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ይኖሩ እንደነበርና ቤተመቅደሳቸውንም  ንጉሥ ናቡከደነጾር እየሩሳሌምን በመውረር የሰሎሞንን ቤተመቅደስ ካፈራረሰ በኃላ የተወሰኑ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን ሲጋዙ የተቀሩት ወደ ተለያዩ ሀገራት ተበታትነዋል ።

አይሁዳውያን በስደት በቆዩባቸው ሀገራትም በንግድና በእጅ ሙያ ተሰማርተው የኢኮኖሚ አቅማቸውን መገንባት ችለው ነበር ።

አይሁዳውያን በመላው ዓለም ተበትነው መኖር ከጀመሩ በኋላ ቀስ ቀስ በሮማውያን፣በፋርሶች፣በዓረቦች፣በቱርኮችና በክርስቲያን መንግስታት የጥላቻ ሰለባ መሆን ጀመሩ ።

ለምን?

መጀመሪያ አይሁዳውያን የተጠሉበት ምክንያት ሃይማኖታዊ ነበር ።አይሁዳውያን የአንድ አምላክ አማኞችና የብሉይኪዳን ተከታዮች ስለነበሩ የኦሪት ህግን የሙጥኝ ብለው ያዙ ።በዚህም የክርስትና እምነትን መቃወም ጀመሩ።

ሌላው አይሁዳውያን ከእግዚአብሔር ቃልኪዳን የተቀበሉና የተመረጡ "ብቸኛ ህዝቦች"እነሱ በመሆናቸው ከሌላ ህዝብ ጋር መቀላቀልም ሆነ መነካካትን በፍፁም አልፈለጉም ።ይህ አስተሳሰባቸው ይበልጥ እንዲጠሉና የጥቃት ሰለባ እንዲሆኑ አደረጋቸው ።

አውሮፓ ውስጥ ከመጀመሪያ የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ12ኛው ክፍለ ዘመን በአይሁዳውያን ላይ በስፋት ጥቃት ይሰነዘር ጀመረ።

የመጀመሪያዎቹ የመስቀል ጦረኞች ወደ እየሩሳሌም ሲዘምቱ እግረ መንገዳቸውን ጀርመን ውስጥ በርካታ አይሁዳውያንን ገድለዋል ።በዘመናዊው ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነትም በጀርመን ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያን መገደላቸውም የምናስታውሰው ታሪክ ነው ።

በ19ኛው ክፍለዘመን ማብቂያ ላይ በአውሮፓ የሚኖሩ ታዋቂ አይሁዳውያን የፅዮናውያን ንቅናቄ በመጀመር ሀገር የመመስረት ፍላጎት መጠናከር ጀመረ ።

የፅዮናዊ ንቅናቄ መስራች አባት እንደሆነ የሚነገርለት በኦስትሪያ የቬና ከተማ ጋዜጠኛ የነበረው ቴዎዶር ሄርዘል በየካቲት 1896ዓ.ም "የአይሁድ መንግሥት "የተሰኘ መጽሐፍ ፃፈ ።

አሁን የአይሁዳውያን ሀገር የመመስረት ትልም መስመር እየያዘ ነው ።አይሁዳውያን ከተበተኑበት ከዓለም ክፍል ተሰባስበው በአንድ አከባቢ ሀገር መመስረት ።ለዚህም የተመረጡ አከባቢዎች አርጀንቲናና ፍልስጤም ነበሩ።

ባለራዕይው ሄርዜል አርጀንቲናን የመረጠበት ምክንያት ሰፊ ፣ለምና ብዙ ህዝብ የማይኖርባት አገር በመሆኗ ሲሆን ፍልስጤምን የመረጠበት ምክንያት ደግሞ ጥታዊና ታሪካዊ ቤታችን ናት ብለው ስለሚያምኑ ነው ።ለዚህም አይሁዳውያንን ለማስፈር ከአርጀንቲና ይልቅ ፍልስጤም ተመራጭ ሆነች ።

በወቅቱ ፍልስጤማውያን በሀገራቸው አምስት መቶ ሺህ ይደርሱ ነበር ።በመላው ዓለም የአይሁድ መንግሥት ለመመስረት ንቅናቄ ተጀመረ ።

ቴዎዶር ሄርዘል በቂ ደጋፊዎችን ማግኘቱን ካረጋገጠ በኃላ የመጀመሪያውን የፅዮናውያን ጉባኤ በነሐሴ 1897ዓ.ም ስዊዘርላንድ ባስል ከተማ አካሄደ ።

በዚህ ጉባኤያቸው የዓለም ፅዮናዊ ድርጅትን ፣ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማን፣ብሔራዊ መዝሙርን እና የአይሁድ ብሔራዊ ፈንድን ይፋ አደረጉ ።

ከ1882ዓ.ም ጀምሮ በርካታ አይሁዳውያን ወደ ፍልስጤም መፍለስ ጀመሩ ።

አይሁዳውያኑ ቱጃሮች ስለነበሩም ከፍልስጤማውያን ከፍተኛ ገንዘብ እየመደቡ መሬትን መግዛት ጀመሩ ።

በገዙት መሬት ላይም ከአውሮፓና ከተቀረው የዓለም ክፍል ተበታትነው የነበሩ አይሁዶችን እያመጡ ማስፈር ተያያዙ።የእርሻ ስራን በከፍተኛ ደረጃ አስፋፉ ።ትላልቅ ግንባታዎችን በማካሄድ ኢኮኖሚውን ተቆጣጠሩት ።

አሁን በፍልስጤም የአይሁዳውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣት ጀምሯል።

ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡትና በኢኮኖሚ እየፈረጠሙ የመጡት አይሁዳውያን የራሳቸውን የፓሊስ ኃይል በማደራጀት ፍልስጤማውያንን መበደልና ማፈናቀል ጀመሩ ።

ለአይሁዳውያን መስፋፋትና መንግስት መመስረት ዕቅድ ውስጥ አሜሪካና እንግሊዝ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ነበሩ ።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኃላ ህዳር 1947ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍልስጤምን ለሁለት የመክፈል ውሳኔ አሳለፈ ።

በውሳኔው መሰረት ፍልስጤም የአይሁድና የአረብ መንግስት ሲኖራት እየሩሳሌም ደግሞ አለም አቀፍ ህልውና እንዲኖራት ተደረገ ።

ህዳር 29,1947ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ጉባኤ 33 ሀገራት ፍልስጤምን የመክፈሉን የውሳኔ ሃሳብ ሲደግፉ 13 አገራት ተቃውመውታል ።አስር አገራት ደግም ድምፅ አልሰጡም ።

ኢትዮጵያ ድምፅ ካልሰጡ ሀገራት አንዷ ነበረች ።

በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ መሰረት 56.47% የሚሆነው የፍልስጤም ግዛት ለፅዮናውያን ሲሰጥ 43.53%ያህሉ ደግሞ ለፍልስጤማውያን ተሰጥቷል ።

በውሳኔው ፍልስጤማውያን እጅጉን በቁጣ ነደዱ ።

እስከአፍንጫቸው የታጠቁት አይሁዳውያን ፍልስጤማውያንን መጨፍጨፍ ጀመሩ ።ከመንደራቸውም ተባረሩ ።

ፍልስጤማውያን ለ2000 ዓመታት ከኖሩበት አገራቸውን ጥለው ጥቃቱን በመሸሽም ወደ ጎረቤት ሀገራት መሸሽ ጀመሩ።ይህም በመላው የዓረቡ ዓለም ቁጣን ቀሰቀሰ ።ግን የዓረቡ ዓለም በጦር ትጥቅና ስልት ደካማ ስለነበር ፍልስጤማውያንን መታደግ አልቻለም ።

አይሁዳዊው የቬናው ጋዜጠኛ ቴዎዶር ኤርዘል የፅዮናውያንን ድርጅት ከመሰረተ ሃምሳ ዓመት በኃላ ግንቦት 14,1948ዓ.ም የፅዮናውያን መሪ ዴቪድ ቤንጎሪዮን የእስራኤል መንግስትን መመስረትን ቴልአቪቭ ላይ አወጁ ።

ዩናይትድ ስቴትስም በዕለቱ አዲስ ለተመሰረተችው የእስራኤል መንግሥት ዕውቅናን በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች ።

ፍልስጤማውያን በአሜሪካና በእንግሊዝ ክህደት ተፈጽሞባቸው ከገዛ አገራቸው ተባረው ፣መሬታቸውን ተነጥቀው ከሀገር ሀገር ቢንከራተቱም የህልውናቸው ሀገር መሰረት ፍልስጤም አልጠፋችም ።

ፍልስጤማውያን መብታቸው ሲረገጥና ሀገራቸውን ሲነጠቁ አይሆንም በማለት ለመብታቸው ሲታገሉ አሜሪካ "አሸባሪ" የሚል ስም ታወጣላቸዋለች ።

ዛሬም ሌላ ጦርነት፤ ሌላ ግጭት።

የእስራኤልና የፍልስጤም ግጭት ከዘመን ዘመን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ዛሬ ላይ ደርሷል ።ነገም ይቀጥላል ።

የዚህ ጽሁፍ መነሻ ሀሳብ የፍልስጤም የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ የሚል የስለሺ ቱጂ መጽሐፍ ነው ።"

copied

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

We stand together and Allah will help us.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group