የበርሊን እና የፍልስጤማዊያን ደጋፊዎች ፍትግያ
__RN05__
የእስራኤልን እርምጃ ተቃዉሞ ማድረግ ከባድ ከሆነባቸው ቦታዎች አንዱ የጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አንዱ ነው፡፡
ምንም እንኳን በጀርመን ሃገር በተለያዩ ከተማዎች የእስራኤል እስራኤል ፍልስጤማዊያን ላይ እየወሰደች ያለችዉን እርምጃ የሚቃወሙ ሰልፎች በመጠኑም ቢሆን ቢስተዋሉም በዋና ከተማዋ በበርሊን ግን ተመሳሳይ ሰልፎችን ማድረግ አዳጋች እንደሆነ የአይን እማኞች ይናገራሉ፡፡
እንደ እማኞቹ ከሆነ በበርሊን ከተማ እስካሁን ድረስ ከአምስት ጊዜ በላይ ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ የተሞከሩ ሲሆን ከዛሬ በፊት የነበሩት ሰልፎች በፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እንዲበተኑ ተደርገዋል። የዛሬውም ኦክቶበር 21 2023 ሰልፍ በከበባና በወከባ ውስጥ ሆኖ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም እስካሁን በአጠቃላይ በጀርመን ሁለት ሺህ ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል።
በሌላ በኩል ከሁለት ቀን በፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፉ ወደ አመፅ ተቀይሮ ከሰልፈኞቹ ውስጥ ወደ አራት መኪኖችን ማቃጠላቸው ታውቋል።
ጀርመን ከእስራኤል ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላት ከመሆኑም በላይ ከዚህ ቀደም ከይሁዲዎች ጋር በተያያዘ በሃገሯ ናዚዎች በፈጸሙት ወንጀሎች ምክንያት እስራኤልን በተመለከተ የምታራምደው ፖሊሲ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆኑ ይታወቃል፡፡