UMMA TOKEN INVESTOR

Abu Muslim shared a
Translation is not possible.

የለሊት ሶላት እና የአሰጋገድ ሁኔታው‼️

▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

✍ሶላት በእስልምና ዋነኛው

አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው።

||

የሌሊት ሶላት አንዱ የተረጋገጠ ሱና እና ትልቅ ፋይዳ ያለውና ከምርጥ ኢባዳዎች አንዱ ነው ከሌሊቱ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ሱብሒ ሶላት ድረስ ከመስገድ በፊት በመጨረሻው አንድ ሶስተኛው ላይ ቢገኝ ይመረጣል።

*

የለሊት ሶላት እና አሰጋገዱ:

✔️ በየሁለት ረከዓው እያሰላመቱ የቻሉትን የፈለጉትን ያክል ይሰግዱና መጨረሻ ላይ አንድ ረከዓ ብቻ በመጨመር በዊትር ያጠናቅቃሉ።

*

የ"ለይል" (ለሊት) ሶላት ተብሎ በውስጥ "ተነይቶ" (ታስቦ) ፋቲሓ ይቀራል።

ከፋቲሓ በኋላ የቻሉትን ሱራ ይቀራል። "ሓፊዝ የሆነ ስው በሒፍዙ አርዝሞ ይቀራል፤ "ሓፊዝ ያልሆነ ስው የሚችለውን ይደጋግማል ካልሆነ ደግሞ ቁርኣን ይዞ መቅራት ይችላል።

በዚህ መልኩ ሁለት ረከዓ ከሰገዱ በኋላ - እንደ "ቀብልያ"፣ "ባዕዲያ" ሱንና ሶላቶች ማለት ነው - አተሕያቱ ቀርተው ማሰላመት ነው።

°

✅ ከዛም በኋላ በዚሁ መስረት የቻሉትን ያክል ሁለት ሁለት ረከዓ እየሰገዱ አስርም ይሁን፣ አስራ ሁለትም፣ አስራ አራትም፣ አስራ ስድስትም፣ ሃያ እና ሃያ ሁለትም ሰግደው  መጨረሻ ላይ አንድ ነጠላ ቁጥር በመስገድ ዊትር አድርገው ማጠናቀቅ።

ዊትር ማለት ደግሞ ኢ—ተጋማሽ ቁጥሮች ማለት ነው (1፣3፣5፣7...) ማለትም 1 ረካዓ ሰግደው ተሽሁድን በመቅራት ሶላቱን ዊተር አድርገው ማጠናቀቅ ይችላሉ።

:

እንደው ጠቅለል ሲደረግ ሶላተል-ለይል ማለት ከኢሻ በኃላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ወቅት ውስጥ የሚሰገድ፣ ቁርአን በዛ ተደርጎ የሚቀራበት ትርፍ የሆነ የሌሊት ሶላት ሲሆን ይህ ሶላት ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።

:

ለዛም ነው የሌሊቱ መጀመሪያም ይሁን መካከል ይሁን መጨረሻ ላይ መስገድ ቢቻልም በላጩ ግን የሌሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ መስገድ በላጭ ነው።

*

ምክንያቱም በዚህ ወቅት በሀዲስ እንደተገለፀው አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የሚወርድበትና "ማን ነው የሚለምነኝ የምቀበለው⁉️ ማን ነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው⁉️  ማን ነው ማሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው⁉️" የሚልበት ሰአት በመሆኑና በርካታ ኡለሞች ዘንድ ከተኙ ቡኃላ ተነስቶ መስገድ በላጭ ስለሆነ ይህን ሱና ለማግኘት ሲባል ነው።

ﻳَﻨْﺰِﻝُ ﺭَﺑُّﻨﺎ ﺗَﺒﺎﺭَﻙَ ﻭﺗَﻌﺎﻟَﻰ ﻛُﻞَّ ﻟَﻴْﻠﺔٍ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺴَّﻤﺎﺀِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴﺎ ﺣِﻴﻦَ ﻳَﺒْﻘَﻰ ﺛُﻠُﺚُ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﺍﻵﺧِﺮُ، ﻳﻘﻮﻝُ : ﻣَﻦ ﻳَﺪْﻋُﻮﻧِﻲ، ﻓﺄﺳْﺘَﺠِﻴﺐَ ﻟﻪ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻨِﻲ ﻓﺄُﻋْﻄِﻴَﻪُ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴﺘَﻐْﻔِﺮُﻧﻲ ﻓﺄﻏْﻔِﺮَ ﻟﻪ؟

ﺍﻟﺮﺍﻭﻱ : ﺃﺑﻮ ﻫﺮﻳﺮﺓ - ﺍﻟﻤﺤﺪﺙ :

ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺻﺤﻴﺢ

📒ﻣﺴﻠم ‏(758)

በተጨማሪም ይህ የቁርአን አንቀፅ የሚያመለክተው ሁሉንም የሌሊት ሶላቶች ነው።

”وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا“

"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በርሱ (በቁርአን) ስገድ፣ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።"

📒ሱረቱል ኢስራእ [79]

*

በመጨረሻም እስከ ሌሊቱ አጋማሽ በሗላ (ማለትም ከ 7 ሰዐት በሗላ) እንቅልፍ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያቶች ሳትተኙ ከቀራችሁ ሁለት ረካዓና አንድ ውትር ወትራችሁ ሀጃም ያላችሁ ዱዓችሁን አድርጋችሁ ብትተኙ ለስኬታችሁ ቁልፍ፣ ለኢማናችሁ ትርፍ፣ ወንጀልን ለማርገፍ፣ ለጭንቃችሁ መውጫ እና ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር የተመረጠ ግዜ ነውና ተጠቀሙበት።

||

ይህንን ያነበባችሁ ወንድምና እህቶች በሙሉ:-

ሌሎች አንብበው ከሰገዱ የአጅሩ ተካፋይ ናችሁና፤ መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር አድርጉት‼️

||

የቴሌግራም ቻናል:

t.me/AbuHiba

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

_ إذا قلت لقد تعبت ؟

﴾وَ اصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا﴿

_ وكيف ذلك ؟

﴾لا تَدرى لَعَلَّ اللهَ يُحدِثُ بَعدَ ذَالِكَ أَمراً ﴿

_ إنه صعب يا الله

﴾إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا وَنَرَاهُ قَرِيبًا﴿

_ لا أستطيع التحمل !

﴾لا يُكلِف اللهُ نفسً إلآ وسّعها﴿

_ أريد أن أفرح !

﴾ولَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ﴿

_ هل ذلك ممكن حقاً ؟

﴾إنَّ ذلك على الله يسيرٌ﴿٠🤍

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#Free_Palestine🇵🇸🇵🇸🇵🇸

#muslim_world #gaza #نصر من الله وفتح فريب #إن_شاء_الله

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Abu Muslim shared a
Translation is not possible.

ከአፊያ (ከጤና) በላይ ምን አለ?!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يا عباسُ عمَّ النبيِّ ! أَكثِرْ من الدُّعاءِ بالعافيةِ﴾

“አንተ አባስ ሆይ! የነቢዩ አጎት! አብዛኛው ዱዓህን ስለ አፊያ (ጤንነት) አድርገው።”

📚 ሶሂህ አተርጊብ: 3390

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Abu Muslim Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group