UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

✍️የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ‼️

===============

🔘ወደ ሰላት ከመገባቱ በፊት

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሙሉ የሆነ ውዱእ ይደረጋል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ወደ ቂብላ ይቀጣጫል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሰፍ ይስተካከላል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ማእሙኖች ኢማሙን ተከትለው ይቆማሉ።

🔘የሰላቱ አሰጋገድ

✍️የመጀመሪያው ተክቢራ ይባልና…

ሱረቱል ፋቲሃ ይቀራል።

{بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ}

{الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ

غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ}

ይህንን ሲጨርስ ሁለተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከሁለተኛው ተክቢራ በኋላ……

በነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳል።

«اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد»

ይልና ሶስተኛው ተክቢራ ይላል

✍️ከሶስተኛው ተክቢራ በኋላ……

ለሟቹ ዱዓ ያደርግለታል። ለምሳሌ ከመጡ ዱዓዎች መሃል……

«اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه،

وأكرم نزله، ووسع مدخله، واغسله بالماء والثلج والبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس،

اللهم أبدله دارًا خيرًا من داره، وأهلًا خيرًا من أهله،

اللهم أدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، ومن عذاب النار، ووسع له في قبره، ونور له فيه»

ከዚህም ውጪ ያሉ ዱዓዎች የቻለውን ያደርግለታል። ይህንን ሲጨርስ አራተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ…

ቲንሽ ዝም ይልና እዛው በቆመበት ወደ ቀኝና ወደ ግራው ያሰላምታል።

«السلام عليكم ورحمة الله,

السلام عليكم ورحمة الله»

ይላል።

🔘አንዳንድ ነጥቦች

💫ጀናዛው ከኢማሙ ፊት ይቀመጣል።

ጀናዛው የወንድ ከሆነ;

ኢማሙ ጭንቅላቱጋ ይቆማል።

ጀናዛው የሴት ከሆነ;

ኢማሙ ወገቧ አካባቢ ይቆማል።

💫ባለው የሰጋጆች ብዛት ረዥም ሰፍ ከመስራት ይልቅ ሰፎቹ መብዛታቸው ይመረጣል።

💫አራቱንም ተክቢራዎች ሲባሉ እጅ ማንሳቱ የተሻለ የተወደደ ነው።

💫አንድ ሰው ኢማሙ የተወሰነ ከሰገደ በኋላ ደርሶ ወደ ሰላቱ ቢገባ የሚጀምረው ኢማሙ ከደረሰበት ቦታ ሳይሆን ከመጀመሪያው ቦታ ነው።

ለምሳሌ፦

ኢማሙ የሁለተኛው ተክቢራ ሲያደርግ ቢደርስ እሱ የሚያደርገው ሰለዋት ማውረድ ሳይሆን ፋቲሃን መቅራት ነው; በመጨረሻ ኢማሙ ሲያሰላምት ቶሎ ቶሎ ብሎ ይጨርስና ያሰላምታል።

💫ጀናዛው የሆነ ቦታ ተሰግዶበት የተቀበረ ከሆነ ሌላ ቦታ "ሰላተል غይብ" ተብሎ አይሰገድበትም።

💫አንድ ሰው ሰላተል ጀናዛ ቢያመልጠውና መስገድ ቢፈልግ ጀናዛው ቢቀበር እንኳ ቀብሩ አጠገብ ሄዶ ይሰግድበታል።

🔘ማሳሰቢያ

✏️ቀላል ከመሆኑም ጋ ብዙሃኖች የሚከብድ መስሏቸው ብዙ ጊዜ ከመስገድ ሲቆጠቡ ይታያሉና ሼር አድርጉላቸው።

🤲አላህ መጨረሻችን አሳምሮ ይውሰደን🤲

✍ሐምዱ ቋንጤ

🕌ከፉርቃን ሰማይ ስር

👍 በ Umma Life ሚድያ የአል-ፉርቃን ገፅ ለመቀላቀል⤵️⤵️

📎 https://ummalife.com/AlFurqan_IslamicStudio

👍 በ Telegram ሚድያ የአል-ፉርቃን ገፅ ለመቀላቀል⤵️⤵️

🔗 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

... ጂሃድ ግዴታ ነው❗️ነገር ግን በሸርጥ (በቅድመ ሁኔታ) ነው !!!

👉 (ይህም ማለት) በምድር ላይ ፊትና እስከማይኖር ❗️ማለትም ፦ ከአላህ መንገድ የሚከለክል ነገር እስከማይኖር እንዲሁም የሙስሊም ጠላቶች ወደ ዕምነታቸውን መጣራት እስከማይችሉ ድረስና ዕምነት ሁሉ ለአላህ እስኪሆን ድረስ "ጂሃድ" ግዴታ ነው !!!

👉👉👉 ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው በቅድመ-ሁኔታ ነው‼️እሱም ፦ "ቁድራ" (መቻል አቅም) ሊኖረን ይገባል ማለት ነው‼️

❌ አሁን ላይ ለእኛ "ቁድራ" አቅም የለንም !!!!!!!

(ታላቁ ኢማም መሐመድ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን)

👍 በ Umma Life ሚድያ የአል-ፉርቃን ገፅ ለመቀላቀል⤵️⤵️

📎 https://ummalife.com/AlFurqan_IslamicStudio

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🇪🇹 Umma Life Amharic Ethiopian Muslim Media

🔗 https://ummalife.com/UmmaLife_Amharic

Send as a message
Share on my page
Share in the group
UmZubair UmZubair Changed her profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group