Translation is not possible.
የጁምዓ መልዕክት
 
ዝንጉነት (ገፍላ) — የልብ በሽታና የመዳኛ መንገዶቹ
 
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአላህ ይሁን። ሰላትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ ﷺ ላይ ይውረድ።
 
◆ ዝንጉነት (ገፍላ) ማለት አንድ ሰው ለተፈጠረበት ታላቅ ዓላማ ግድየለሽ ሆኖ፣ በቅርቢቱ ዓለም (ዱንያ) ተታሎ፣ ዘላቂውን ዓለም (አኺራ) እና የፈጣሪውን ትእዛዛት መዘንጋት ነው። ይህ በሽታ በጊዜ ካልታከመ ልብን ያደርቃል፤ መጨረሻንም ያበላሻል።
 
1. የዝንጉነት (ገፍላ) ምልክቶችና አስከፊነቱ
አላህ (ሱ.ወ) በዝንጉነት የተሸፈኑ ሰዎችን ሁኔታ በቁርዓኑ እንዲህ ይገልጸዋል፦
"ለእነርሱም ልቦች አሏቸው፤ በእርሷም (ሐቅን) አያውቁም፡፡ ለእነርሱም ዓይኖች አሏቸው፤ በእርሷም አያዩም (አስተውለው አይመለከቱም)፡፡ ለእነርሱም ጆሮዎች አሏቸው፤ በእርሷም አይሰሙም፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፤ ይልቁንም እነርሱ ይበልጥ የጠፉ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ (ጋፊሉን) እነርሱ ናቸው፡፡" (ሱረቱል አል-አዕራፍ 7:179)
 
እነዚህ ሰዎች በምድር ላይ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ ልባቸው ስለሞተ የፈጣሪን ታምራትም ሆነ የሐቅን ጥሪ ማስተዋል አይችሉም።
 
2. የዝንጉነት ምንጭ፦ የዱንያ ፍቅር
ሰዎች ከአላህ ጋር መገናኘትን የማይፈልጉትና በኢባዳ ላይ የሚሰነፍቱት ለዱንያ ያላቸው ፍቅር ከመጠን በላይ ስለሆነ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
"እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈልጉ፣ በቅርቢቱ ሕይወትም የረኩባትና በእርሷም ያረፉ፣ እነዚያም ከታምራቶቻችን ዘንጊዎች የሆኑ፤ እነዚያ ይሠሩት በነበሩት (ክፉ ስራ) ምክንያት መኖሪያቸው እሳት ናት።" (ሱረቱ ዩኑስ 10:7-8)
 
3. የቆርቋሪቱ (አል-ቃሪዓህ) ቀን ማስጠንቀቂያ
ዝንጉነት በምድር ላይ ያለን የዝግጅት ጊዜ ያባክናል። በዕለተ ቂያማ (የቆርቋሪቱ ዕለት) ግን ሚዛን የሚደፋው ዛሬ በሰራነው ስራ ብቻ ነው።
"በዚያ ቀን ሰዎች እንደ ተበተነ ቢራቢሮ በሆኑ ጊዜ፤ ተራራዎችም እንደ ተነደፈ ግምጃ በሆኑ ጊዜ። ሚዛኖቹ (የመልካም ስራው) የከበዱለት ሰው እርሱ በወደዳት (በደስታ) ኑሮ ውስጥ ነው፡፡ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰውማ መኖሪያው ሀዊያህ (ጥልቅ እሳት) ናት።" (ሱረቱል አል-ቃሪዓህ 101:4-9)
 
4. የማይጠቅመው ፀፀት (የገረገራ ሰዓት)
ሰው በዝንጉነት ውስጥ እያለ ሞት በድንገት ይመጣል። በዚያ ሰዓት (በገረገራ ጊዜ) የሰው ልጅ ወደ ዱንያ ተመልሶ ጥቂት መልካም ስራ እንዲሰራ አጥብቆ ይመኛል። ነገር ግን አላህ እንዲህ ይላል፡-
"ከመካከላቸው ለአንዳቸው ሞት በመጣ ጊዜ እንዲህ ይላል፡- ‘ጌታዬ ሆይ! (ወደ ዱንያ) መልሱኝ፤ በተውኩት ዓለም መልካምን ሥራ እሠራ ዘንድ (እመኛለሁ)።’ (አላህም እንዲህ ይላል)፦ ‘አይደረግም! እርስዋ እርሱ የሚናገራት (ከንቱ) ቃል ናት።’" (ሱረቱል አል-ሙእሚኑን 23:99-100)
 
5. ለዝንጉነት መፍትሄው፦ ነብያዊ መድሃኒት
ይህንን የልብ ዝገት ለማከም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ታላቅ መፍትሄ አስተምረውናል።
 
ሐዲስ፦
ታላቁ ሰሃቢ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
"ልዘቶችን (ጣፋጭ ነገሮችን) አጥፊ የሆነውን ሞትን በብዛት አስታውሱ።" (ቲርሚዚ 2307 እና ነሳኢ 1824 ዘግበውታል - ሰሂህ ሐዲስ)
 
ሞትን ማስታወስ ማለት መጨቆን ሳይሆን፣ ለዘላቂው ህይወት በንቃት መዘጋጀትና የልብን ዝንጉነት በኢባዳ ማከም ማለት ነው።
 
✅ ማጠቃለያ፡ የዝንጉነት መፍትሄዎች
◆ ተውበት፦ ዛሬውኑ ወደ አላህ መመለስ።
◆ ቁርዓን፦ ቁርዓንን በትድብቡር (በማስተንተን) መቅራት።
◆ ኢባዳ፦ ሶላትን በወቅቱና በተመስጦ መስገድ።
◆ ዝክር፦ አላህን በማውሳት ልብን ማርጠብ።
"አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ!"
 
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
════════════════
 
📧 tiktok.com/@secretsof_truth
 
📧 Instagram.com/secretsof_truth
 
📧 t.me/Secretsof_Truth
 
📧 Fb.com/SecretsofTruth1
 
📧 ummalife.com/ReshadMuzemil
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group