Translation is not possible.
አግራሞቴን በብዕር
 
ከፍታን ለመውጣት መለወጥ
 
▪️ የመድሃኒት ታሪክ የሚያስተምረን ነገር አለ። መድሃኒት ሳይወሰድ፣ የፈውሱ ሂደት ወይም የእኛን የማገገም አቅም ማወቅ አይቻልም። መድሃኒቱን ስንወስድና ለሰውነታችን ስናስረክብ ብቻ ነው በፈጣሪያችን እዝነት ልንፈወስ የምንችለው። ልክ እንደዚሁ፣ የስኬት 'መድሃኒት' የሆነውን ለውጥ ካልወሰድን የእድገት አቅማችንን ልንረዳው አንችልም።
 
● ታዲያ አግራሞቴ ይህ ነው! ሰዎች እድሜ ልካቸውን ምንም ሳይሰሩና ቁጭ ብለው ሳሉ የሚመኙት ግን 360 ዲግሪ ከፍታ ያለውን የህይወት ፎቅ ነው። ይህ አይገርምም?! የመማሪያ መጽሐፍትን እየደረደርን፣ በየመድረኩ እየተመካከርን፣ ነገር ግን ምንም ለውጥ ሳናመጣ ከፍ ያለ ምኞትን ብቻ ማቀንቀን ምን ይጠቅማል?
 
▮ እድሜ ልካችንስ ሰውንም ሆነ ራሳችንን ሳንቀይር፣ ህልም በሆነና በማይሳካ ብልጭልጭ ጉዞ ውስጥ ሆነን እንዴት ታላቅ ከፍታን እንመኛለን?! ንግግር ከድርጊት ሲለይ፣ ምኞት ደግሞ የሕይወት መንገድ ይሆናል!
◈ እውነተኛ ከፍታና የስኬት-ማማ ላይ ለመድረስ፤ ማሰብ-ማሰላሰል፣ ማዘን-መተከዝ፣ መፃፍና ማንበብ እንዲሁም ዕውቀት ብቻውን በቂ አይደለም። እነዚህ የመሳሪያ ሳጥኑ አካል ናቸው እንጂ የመጨረሻው ውጤት አይደሉም። ዋናው ቁልፍ፡- ራስን መቀየር፣ ለውጥን አፈላልጎ ማግኘት፣ ራስን ማሻሻል እና ሌሎች እንዲሻሻሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ግድ ይለናል።
 
መቀየር ማለት፡- የድሮውን እኛነት መተው፣ አዳዲስ ልምዶችን ማዳበር እና ፍሬ-ቢስ የሆኑ ባህሪያትን ከሕይወታችን ማስወገድ ማለት ነው።
 
▮ ይህ ካልሆነ ግን፦ “ኬሴ ላይ ብር አለ፣ ምን እንደ ምሰራበትም አውቃለሁ፣ እውቀትና ብቃቱም አለኝ ነገር ግን ምንም እያረኩኝ አይደለሁም፤ ይሀው ዘመኔን ሙሉ ቁጭ እንዳልኩኝ ነኝ” እንደሚሉት ሰዎች መሆናችን እርግጥ ነው! ምኞታቸው በዕውቀታቸው እስር ቤት ውስጥ ለዘላለም ታስሮ ይቀራል።
 
↪️ ከብር፣ ከዕውቀት፣ ከጥረት፣ ከማሰብና ከማሰላሰል በተጨማሪ ራሳችንን መቀየር የግድ ነው። ለዚህ ስኬትን የፈለገ፣ ከፍታን የሻተ ሰው፡- ለውጥን በቃላት መናገር ሳይሆን፣ ሆኖ መኖር አለበት! መቀየር የሚጠቅመን መስሎ መኖር ሳይሆን፣ ሆኖ መኖር ነው! ለዚህም ነው "መቀየር" የሚያስፈልገን!!
 
▮ ለመቀየር አቅም አላነሰንም! የዕውቀት ማነስም አይደለም! የሚያስፈልገን ብቸኛው ነገር ምክንያት ብቻ ነው። የለውጥ ጥማት፣ ለልጆቻችንና ለሀገራችን የተሻለ ነገር የመፍጠር ግዴታ፣ ካለንበት የቆምንበት ደረጃ የመብቀል ፍላጎት! ይህን ምክንያ እኛ ራሳችን ቆርጠንም-ፈልጠንም፣ ቆፍረንም-ፈልፍለንም ቢሆን እናግኘው!
 
▮ የሚገርመው ደግሞ ስንቀየርና ስንጠነክር፤ ከጎናችን የሚሆኑ ብዙዎች ናቸው! ወደው ሳይሆን ተገደው የሚደግፉን ስፍር ቁጥር የላቸውም! ምክንያቱም የዓለም ህግ የሚደግፈው ለውጥን ያመጡ እና ስራ የሰሩ ሰዎችን ነው። ለውጣችን ለሌሎችም ብርሃን ይሆናል ማለት ነው!
 
● እኮ በቃ እኛው አይደለንም?! የለውጥ ምክንያቱን እንፈልገው፤ ከዚያም እንቀየራ!
 
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
════════════════
👇👇 share👇
 
Telegram: t.me/SharpSwords1
 
Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1
 
Instagram: Instagram.com/sharp_swords1
 
Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
 
LinkedIn: linkedin.com/in/reshad-muzemil-139b97320
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group