አግራሞቴን በብዕር
የማይገታው ሚሳኤል፡ ጥንካሬ፣ ስኬትና ትውስታ
◆ ደካሞችን በማትቀበል ዓለም እና ጠንካሮችን በማይወድ ማህበረሰብ መካከል መኖር ምንኛ ከባድ ፈተና ነው! ነገር ግን፣ ይህ ፈተና "ጠንካራ ላለመሆን" ምክንያት ሊሆነን በፍጹም አይገባም።
በስኬት ጉዞአችን ላይ ፍሬን እየያዝን የምንቆምበት ጊዜ የለም። ለስኬት የምናደርገው ተጋድሎ፣ ፍሬን እንዳለው መኪና ወይም አውቶቡስ መቆም እና መሄድ የለበትም። ይልቁንም ጉዞአችን ኢላማውን እስኪመታ የማይቆም፣ ወደ ፊት የሚተም ሙሉ ለሙሉ "ሚሳኤል" መሆን አለበት! ከስማችን ፊትና ኋላም "ጠንካራው" የሚለው መለያ ሊለየን አይገባም።
ነገር ግን አንድ እውነት እናስተውል፤ የጥንካሬ ትርጉም በባንክ አካውንት መወፈር ወይም መቅጠን፣ ሀብታም ወይም ድሃ በመሆን አይለካም። የጥንካሬ ትክክለኛ ትርጉሙ፣ ባለንበት ቦታ የተጋረጡብንን ከባባድ ፈተናዎች በድል መወጣት እና ችግሮቻችንን በጥበብ መቅረፍ ነው።
🎯 በስኬት ጉዞአችን ደስታን መሻታችን አይቀርም፤ ደስታ ግን ቤትና መኪና በመሰብሰብ ብቻ የሚገኝ ሸቀጥ አይደለም። እውነተኛ ደስታ ያለው በተራበ ሰው ጉሮሮ፣ በተሰበረ ልብ ጥገና ውስጥ ነው። የተራበን በማብላት፣ የያዘነን ሰው ሀዘን በመካፈል የሚገኝ ደስታ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሆኖ አይቀርም፤ ትውስታው ዘላለም አብሮን ይኖራል።
◆ አንዳንድ ጊዜ፣ የህይወት ታላቁ ጠላታችን የገዛ ትውስታችን ሊሆን ይችላል። ትውስታ እንደ ጥላ ነው፤ የመልካም ነገሮች ትውስታ የልብ ወዳጅ ሲሆን፣ የመጥፎ ነገሮች ትውስታ ደግሞ ከባድ ጠላት ነው።
ስለዚህ ወንድምና እህቶቼ... ኑ! ብዙ መልካም ነገሮችን እንሥራ። በሰዎች ልብ ውስጥ ተቀርጾ የሚኖር፣ ዘመን የማይሽረው "የመልካም ትውስታ ወዳጅ" እናፍራ!!
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
═══════════════👇👇 share👇
Telegram: t.me/SharpSwords1
Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1
Instagram: Instagram.com/sharp_swords1
Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
LinkedIn: linkedin.com/in/reshad-muzemil-139b97320