Translation is not possible.

#ራስን #መታገል (#ሙጃሃዳ)

#ክፍል_14

#ሐዲሥ 11 / 108

አቡ ሱፍያን ዐብደላህ ኢብኑ በሽር አል-አስለሚያ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕከተኛ (ሶ.ዐ.ወ)፦ “ከሰዎች ሁሉ በላጩ ዕድሜው የረዘመና ሥራውም መልካም የሆነለት ነው” ብለዋል። (ተርሚዚይ ዘግበውታል፤ “ሐሰን” ነውም ብለዋል)

ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

=› ዕድሜ መርዘሙ፥ በመልካም ሥራ ከደመቀ፥ ወደ አላህ ለመቃረብ የሚረዱ የመልካም ሥራዎች ስንቅ የሚካበትበት በመሆኑ፥ እጅግ የሚጓጉለት ነው። በአንጻሩ ክፋትን እንጅ ደግነትን የማከል ተስፋ ለሌለው የዕድሜው መርዘም ለበለጠ ጥፋት የሚያበቃ በመሆኑ አስፈላጊው አይደለም። ዕድሜው ረዝሞ ሥራው የከፋ ከሆነ ሰው የበለጠ መጥፎ የለም።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group