Translation is not possible.

#ተውበት (#ጸጸት)

#ክፍል_4

#ሐዲሥ 12 / 16

አቡ ሙሳ ዐብደላህ ኢብኑ ቀይስ አል አሽዐሪይ እንዳስተላለፉት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦ \"አላህ በሌሊት እጁን ይዘረጋል፥ ቀን ጥፋት የፈፀመ ተውበት ያደርግ ዘንድ፤ በቀን እጁን ይዘረጋል፥ ሌሊት ጥፋት የፈፀመ ተውበት ያደርግ ዘንድ። ፀሐይ በመግቢያዋ እስክትወጣበት ዕለት ድረስ።\" (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አላህ ለባሮቹ ያለው እዝነትና ይቅር ባይነቱ ሁሉንም ዘመናት የሚያጠቃልል ነው። ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የተለየ አይደለም።

2/ በቀን ወይም በሌሊት ለተፈፀመ ጥፋት አፋጣኝ ተውበት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ይህ ዘገባ ያመለክታል።

3/ የተውበት በራፍ ክፍት እስከሆነ ድረስ ተውበት ምንጊዜም ተቀባይነት ይኖረዋል። የተውበት በራፍ የሚዘጋው ከቂያማ ታላላቅ ምልክቶች አንዱ የሆነው ፀሐይ በመግቢያዋ በኩል (በምዕራብ አቅጣጫ) የመውጣቷ ክስተት እውን ሲሆን ነው።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group